መጽሐፈ መዝሙር 72
72
ስለ ንጉሥ የቀረበ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ለንጉሡ ትክክለኛ ፈራጅነትን
ለንጉሡም ልጅ ጽድቅህን ስጥ።
2በዚህ ዐይነት ሕዝብህን በትትክል ያስተዳድራል፤
ለጭቊኖችህም በትክክል ይፈርዳል።
3ተራራዎች ብልጽግናን፥ ኰረብቶችም የጽድቅ ፍሬን
ለሕዝብ ያስገኙ።
4በሕዝቡ መካከል ለተጨቈኑት ፍርድን ይስጥ፤
ችግረኞችንም ይርዳ፤
ጨቋኝንም ይደምስስ
5በዘመናት ሁሉ የፀሐይና የጨረቃን ያኽል
ረጅም ዘመናት ይኑር።
6ንጉሡ ሣሩ በታጨደ መስክ ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፥
በምድርም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሁን።
7በእርሱ ዘመን የጽድቅ ሥራ ይጠናከር፤
ጨረቃ ብርሃንዋን በምትሰጥበት ጊዜ ሁሉ ብልጽግና ይበርክት።
8ግዛቱ ከባሕር እስከ ባሕር፥
ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይድረስ። #ዘካ. 9፥10።
9በምድረ በዳ የሚኖሩ በፊቱ ይስገዱ፤
ጠላቶቹም ወደ መሬት ወድቀው ትቢያ ይላሱ። #72፥9 በምድረ በዳ የሚኖሩ በፊቱ ይስገዱ፦ በሰባዎቹ ትርጒም በፊቱ ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ ይላል።
10የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርቡለት፤
የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያምጡለት።
11ነገሥታት ሁሉ ይስገዱለት፤
ሕዝቦች ሁሉ ያገልግሉት።
12ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች፥
ችግረኞችንና የተጨቈኑትን ሰዎች ነጻ ያወጣል።
13ለድኾችና ለደካሞች ይራራል፤
በችግር ላይ ያሉትንም ሰዎች ከሞት ያድናል።
14የእነርሱ ሕይወት በእርሱ ዘንድ ውድ ስለ ሆነ
ከጭቈናና ከዐመፅ ያድናቸዋል።
15ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር!
ከሳባ ወርቅ ይምጣለት፤
ስለ እርሱም ዘወትር ጸሎት ይደረግ፤
የእግዚአብሔርም በረከት ዘወትር ከእርሱ ጋር ይሁን!
16በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኑር፤
ተራራዎች በሰብል ይሸፈኑ፤
እንደ ሊባኖስ ተራራዎችም ፍሬያማ ይሁኑ፤
የእህሉም ነዶ እንደ ሣር የበዛ ይሁን።
17የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤
ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤
ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤
እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።
18እርሱ ብቻ ተአምራትን የሚያደርገው፥
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
19ክቡር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
ክብሩ በምድር ሁሉ ይሙላ!
አሜን! አሜን!
20የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት
እዚህ ላይ ተፈጸመ።
ክፍል ሦስት
(መዝ. 73—89)
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 72: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 72
72
ስለ ንጉሥ የቀረበ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! ለንጉሡ ትክክለኛ ፈራጅነትን
ለንጉሡም ልጅ ጽድቅህን ስጥ።
2በዚህ ዐይነት ሕዝብህን በትትክል ያስተዳድራል፤
ለጭቊኖችህም በትክክል ይፈርዳል።
3ተራራዎች ብልጽግናን፥ ኰረብቶችም የጽድቅ ፍሬን
ለሕዝብ ያስገኙ።
4በሕዝቡ መካከል ለተጨቈኑት ፍርድን ይስጥ፤
ችግረኞችንም ይርዳ፤
ጨቋኝንም ይደምስስ
5በዘመናት ሁሉ የፀሐይና የጨረቃን ያኽል
ረጅም ዘመናት ይኑር።
6ንጉሡ ሣሩ በታጨደ መስክ ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፥
በምድርም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሁን።
7በእርሱ ዘመን የጽድቅ ሥራ ይጠናከር፤
ጨረቃ ብርሃንዋን በምትሰጥበት ጊዜ ሁሉ ብልጽግና ይበርክት።
8ግዛቱ ከባሕር እስከ ባሕር፥
ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይድረስ። #ዘካ. 9፥10።
9በምድረ በዳ የሚኖሩ በፊቱ ይስገዱ፤
ጠላቶቹም ወደ መሬት ወድቀው ትቢያ ይላሱ። #72፥9 በምድረ በዳ የሚኖሩ በፊቱ ይስገዱ፦ በሰባዎቹ ትርጒም በፊቱ ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ ይላል።
10የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርቡለት፤
የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያምጡለት።
11ነገሥታት ሁሉ ይስገዱለት፤
ሕዝቦች ሁሉ ያገልግሉት።
12ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች፥
ችግረኞችንና የተጨቈኑትን ሰዎች ነጻ ያወጣል።
13ለድኾችና ለደካሞች ይራራል፤
በችግር ላይ ያሉትንም ሰዎች ከሞት ያድናል።
14የእነርሱ ሕይወት በእርሱ ዘንድ ውድ ስለ ሆነ
ከጭቈናና ከዐመፅ ያድናቸዋል።
15ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር!
ከሳባ ወርቅ ይምጣለት፤
ስለ እርሱም ዘወትር ጸሎት ይደረግ፤
የእግዚአብሔርም በረከት ዘወትር ከእርሱ ጋር ይሁን!
16በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኑር፤
ተራራዎች በሰብል ይሸፈኑ፤
እንደ ሊባኖስ ተራራዎችም ፍሬያማ ይሁኑ፤
የእህሉም ነዶ እንደ ሣር የበዛ ይሁን።
17የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤
ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤
ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤
እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።
18እርሱ ብቻ ተአምራትን የሚያደርገው፥
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
19ክቡር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
ክብሩ በምድር ሁሉ ይሙላ!
አሜን! አሜን!
20የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት
እዚህ ላይ ተፈጸመ።
ክፍል ሦስት
(መዝ. 73—89)
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997