መጽሐፈ መዝሙር 73
73
የእግዚአብሔር ፍትሕ
1ልባቸው ንጹሕ ለሆነ እስራኤላውያን
እግዚአብሔር ቸር ነው።
2በእኔ በኩል ግን እርምጃዎቼ እየተንገዳገዱ፥
እግሮቼም ሊንሸራተቱ ተቃርበዋል።
3ይህም የሆነው ትዕቢተኞችና ክፉዎች ሰዎች ሲበለጽጉ በማየቴ
ቅናት አድሮብኝ ነው።
4እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፥
ሰውነታቸው ጤናማና ወዛም ነው።
5እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም፤
በሌሎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ በእነርሱ ላይ አይደርስም።
6ስለዚህ ትዕቢትን እንደ ድሪ አጥልቀዋል፤
ዐመፅንም እንደ ልብስ ለብሰዋል።
7አእምሮአቸው ክፉ ሐሳብን እያፈለቀ
ከዐይነ ስባቸው የሚወጡት ዐይኖቻቸው አፍጥጠው ይመለከታሉ።
8በሌሎች ሰዎች ላይ እያፌዙ የተንኰል ንግግርን ይናገራሉ፤
በትዕቢታቸውም የመጨቈን ዛቻን ይዝታሉ።
9በእግዚአብሔር ላይ መናገርን ይዳፈራሉ፤
በምድር ላይ ከመናገርም አያቆሙም።
10የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ወደ እነርሱ ያዘነብላሉ፤
የሚነግሩአቸውንም ሁሉ ይቀበላሉ።
11እነርሱም “በውኑ እግዚአብሔር ያውቃልን?
ልዑል እግዚአብሔርስ ዕውቀት አለውን?” ይላሉ።
12እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤
ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው።
ዘወትርም ተጨማሪ ሀብት ያገኛሉ።
13ሐሳቤን በቅንነት መጠበቄና
በደልንም ከመሥራት መቈጠቤ ምን ጠቀመኝ?
14ቀኑን ሙሉ ተሠቃየሁ፤
በየማለዳውም ተቀጣሁ።
15እነርሱ እንደሚናገሩት ለመናገር ባስብ ኖሮ
ለሕዝብህ ታማኝ ባልሆንኩም ነበር፤
16ይህን ለመረዳት ኅሊናዬን አነቃሁ፤
ነገር ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኘሁት።
17ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ
ምንም ማወቅ አልቻልኩም፤
ወደ መቅደስህ በገባሁ ጊዜ ግን
በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ።
18በሚያዳልጥ ስፍራ ታኖራቸዋለህ፤
ወድቀው እንዲጠፉም ታደርጋቸዋለህ።
19በቅጽበት ተደመሰሱ፤
መጨረሻቸውም አስደንጋጭ ሆነ።
20እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስትነሣ እነርሱ በማለዳ
እንደሚረሳ ሕልም ይጠፋሉ።
21ኅሊናዬን በጣም መረረው፤
ልቤም ተሰበረ።
22ጌታ ሆይ! እኔ ለአንተ ከእንስሶች የማልሻል፥
ምንም የማይገባኝ አላዋቂ ነበርኩ።
23ነገር ግን ዘወትር ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤
አንተም ቀኝ እጄን ትይዛለህ።
24በምክርህ ትመራኛለህ፤
በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ።
25በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ?
በምድርስ አንተን ካገኘሁ ሌላ ምን እሻለሁ?
26አእምሮዬና ጒልበቴ ሊደክሙ ይችላሉ፤
እግዚአብሔር ግን እስከ ዘለዓለም ብርታቴና አለኝታዬ ነው።
27እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ፤
አንተን የሚክዱህን ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።
28ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረቤ መልካም ነው፤
የአንተን ሥራ ሁሉ ለማብሠር እንድችል
አንተን ጌታ አምላኬን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 73: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 73
73
የእግዚአብሔር ፍትሕ
1ልባቸው ንጹሕ ለሆነ እስራኤላውያን
እግዚአብሔር ቸር ነው።
2በእኔ በኩል ግን እርምጃዎቼ እየተንገዳገዱ፥
እግሮቼም ሊንሸራተቱ ተቃርበዋል።
3ይህም የሆነው ትዕቢተኞችና ክፉዎች ሰዎች ሲበለጽጉ በማየቴ
ቅናት አድሮብኝ ነው።
4እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፥
ሰውነታቸው ጤናማና ወዛም ነው።
5እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም፤
በሌሎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይ በእነርሱ ላይ አይደርስም።
6ስለዚህ ትዕቢትን እንደ ድሪ አጥልቀዋል፤
ዐመፅንም እንደ ልብስ ለብሰዋል።
7አእምሮአቸው ክፉ ሐሳብን እያፈለቀ
ከዐይነ ስባቸው የሚወጡት ዐይኖቻቸው አፍጥጠው ይመለከታሉ።
8በሌሎች ሰዎች ላይ እያፌዙ የተንኰል ንግግርን ይናገራሉ፤
በትዕቢታቸውም የመጨቈን ዛቻን ይዝታሉ።
9በእግዚአብሔር ላይ መናገርን ይዳፈራሉ፤
በምድር ላይ ከመናገርም አያቆሙም።
10የእግዚአብሔር ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ወደ እነርሱ ያዘነብላሉ፤
የሚነግሩአቸውንም ሁሉ ይቀበላሉ።
11እነርሱም “በውኑ እግዚአብሔር ያውቃልን?
ልዑል እግዚአብሔርስ ዕውቀት አለውን?” ይላሉ።
12እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤
ሁልጊዜ እንደ ተዝናኑ ናቸው።
ዘወትርም ተጨማሪ ሀብት ያገኛሉ።
13ሐሳቤን በቅንነት መጠበቄና
በደልንም ከመሥራት መቈጠቤ ምን ጠቀመኝ?
14ቀኑን ሙሉ ተሠቃየሁ፤
በየማለዳውም ተቀጣሁ።
15እነርሱ እንደሚናገሩት ለመናገር ባስብ ኖሮ
ለሕዝብህ ታማኝ ባልሆንኩም ነበር፤
16ይህን ለመረዳት ኅሊናዬን አነቃሁ፤
ነገር ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኘሁት።
17ወደ መቅደስህ እስክገባ ድረስ
ምንም ማወቅ አልቻልኩም፤
ወደ መቅደስህ በገባሁ ጊዜ ግን
በክፉዎች ላይ ምን እንደሚደርስባቸው ተረዳሁ።
18በሚያዳልጥ ስፍራ ታኖራቸዋለህ፤
ወድቀው እንዲጠፉም ታደርጋቸዋለህ።
19በቅጽበት ተደመሰሱ፤
መጨረሻቸውም አስደንጋጭ ሆነ።
20እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስትነሣ እነርሱ በማለዳ
እንደሚረሳ ሕልም ይጠፋሉ።
21ኅሊናዬን በጣም መረረው፤
ልቤም ተሰበረ።
22ጌታ ሆይ! እኔ ለአንተ ከእንስሶች የማልሻል፥
ምንም የማይገባኝ አላዋቂ ነበርኩ።
23ነገር ግን ዘወትር ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤
አንተም ቀኝ እጄን ትይዛለህ።
24በምክርህ ትመራኛለህ፤
በመጨረሻም በክብር ትቀበለኛለህ።
25በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ?
በምድርስ አንተን ካገኘሁ ሌላ ምን እሻለሁ?
26አእምሮዬና ጒልበቴ ሊደክሙ ይችላሉ፤
እግዚአብሔር ግን እስከ ዘለዓለም ብርታቴና አለኝታዬ ነው።
27እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ፤
አንተን የሚክዱህን ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።
28ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረቤ መልካም ነው፤
የአንተን ሥራ ሁሉ ለማብሠር እንድችል
አንተን ጌታ አምላኬን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997