መጽሐፈ መዝሙር 79
79
ስለ ሕዝብ ሰላም የሚቀርብ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! አሕዛብ ወደ ምድርህ መጡ፤
ቤተ መቅደስህን አረከሱ፤ ኢየሩሳሌምንም አፈራረሱአት። #2ነገ. 25፥8-10፤ 2ዜ.መ. 36፥17-19፤ ኤር. 52፥12-14።
2የሕዝብህን ሬሳ ለሰማይ ወፎችና
የታማኞችህን ሥጋ ለአራዊት ምግብ አድርገው ሰጡ።
3ደማቸውንም እንደ ውሃ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ አፈሰሱ፤
የሞቱትንም የሚቀብር አንድ ሰው እንኳ አልነበረም።
4ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ፥
በዙሪያችን ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ ሆነናል።
5እግዚአብሔር ሆይ!
በእኛ ላይ የምትቈጣው እስከ መቼ ድረስ ነው?
ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?
6ቊጣህን አንተን በአምላክነትህ ወደማያውቁና ወደ አንተ
ወደማይጸልዩ ሕዝቦችና መንግሥታት ላይ መልስ።
7ይህንንም የምታደርገው እነርሱ ሕዝቦችህን ስለ ገደሉና
ርስታቸውን ስለ አወደሙ ነው።
8እኛ በጣም ስለ ተዋረድን
በአባቶቻችን ኃጢአት ምክንያት አትቅጣን
ፈጥነህም ምሕረት አድርግልን።
9አዳኛችን አምላክ ሆይ! እርዳን፤
ስለ ራስህ ክብር ስትል ተቤዠን፤
ኃጢአታችንንም ይቅር በልልን።
10ለምን አሕዛብ “አምላካቸው የት አለ?” ብለው ይጠይቁ?
የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም እንደምትበቀል በፊታችን ለአሕዛብ አሳውቅ።
11የእስረኞች መቃተት ወደ አንተ እንዲደርስ አድርግ፤
ሞት የተፈረደባቸውንም በታላቁ ኀይልህ አድናቸው።
12ጌታ ሆይ! ጐረቤቶቻችን በአንተ ላይ ስለ ተዘባበቱ
በሰባት እጥፍ ተበቀላቸው።
13በዚያን ጊዜ የመንጋህ በጎች የሆንን ሕዝቦችህ
ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤
ለተከታዩ ትውልድ ሁሉ ምስጋናህን እንናገራለን።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 79: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 79
79
ስለ ሕዝብ ሰላም የሚቀርብ ጸሎት
1አምላክ ሆይ! አሕዛብ ወደ ምድርህ መጡ፤
ቤተ መቅደስህን አረከሱ፤ ኢየሩሳሌምንም አፈራረሱአት። #2ነገ. 25፥8-10፤ 2ዜ.መ. 36፥17-19፤ ኤር. 52፥12-14።
2የሕዝብህን ሬሳ ለሰማይ ወፎችና
የታማኞችህን ሥጋ ለአራዊት ምግብ አድርገው ሰጡ።
3ደማቸውንም እንደ ውሃ በኢየሩሳሌምም ዙሪያ አፈሰሱ፤
የሞቱትንም የሚቀብር አንድ ሰው እንኳ አልነበረም።
4ለጐረቤቶቻችን መዘባበቻ፥
በዙሪያችን ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ ሆነናል።
5እግዚአብሔር ሆይ!
በእኛ ላይ የምትቈጣው እስከ መቼ ድረስ ነው?
ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?
6ቊጣህን አንተን በአምላክነትህ ወደማያውቁና ወደ አንተ
ወደማይጸልዩ ሕዝቦችና መንግሥታት ላይ መልስ።
7ይህንንም የምታደርገው እነርሱ ሕዝቦችህን ስለ ገደሉና
ርስታቸውን ስለ አወደሙ ነው።
8እኛ በጣም ስለ ተዋረድን
በአባቶቻችን ኃጢአት ምክንያት አትቅጣን
ፈጥነህም ምሕረት አድርግልን።
9አዳኛችን አምላክ ሆይ! እርዳን፤
ስለ ራስህ ክብር ስትል ተቤዠን፤
ኃጢአታችንንም ይቅር በልልን።
10ለምን አሕዛብ “አምላካቸው የት አለ?” ብለው ይጠይቁ?
የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም እንደምትበቀል በፊታችን ለአሕዛብ አሳውቅ።
11የእስረኞች መቃተት ወደ አንተ እንዲደርስ አድርግ፤
ሞት የተፈረደባቸውንም በታላቁ ኀይልህ አድናቸው።
12ጌታ ሆይ! ጐረቤቶቻችን በአንተ ላይ ስለ ተዘባበቱ
በሰባት እጥፍ ተበቀላቸው።
13በዚያን ጊዜ የመንጋህ በጎች የሆንን ሕዝቦችህ
ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፤
ለተከታዩ ትውልድ ሁሉ ምስጋናህን እንናገራለን።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997