መጽሐፈ መዝሙር 80
80
ስለ እስራኤል መንግሥት እንደገና መቋቋም የቀረበ ጸሎት
1የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ!
በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥
ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ። #ዘፀ. 25፥22።
2ለኤፍሬም፥ ለብንያምና ለምናሴ
ራስህን ግለጥ፤ ኀይልህን አነሣሥተህ
መጥተህ አድነን።
3አምላክ ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን፤
እንድንድን ምሕረትህን አሳየን!
4የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ!
የሕዝብህን ጸሎት ባለመቀበል ቊጣህን
የምትገልጠው እስከ መቼ ነው?
5ሐዘንን እንደ ምግብ፥ እንባንም እንደ መጠጥ
በብዛት ሰጠሃቸው።
6በዙሪያችን ያሉ መንግሥታት መሬታችንን ለመውሰድ
እርስ በእርሳቸው እንዲዋጉ አደረግህ፤
ጠላቶቻችን ሁሉ ይሳለቁብናል።
7የሠራዊት አምላክ ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን!
እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።
8የወይን ሐረግን ከግብጽ አመጣህ፤
ሌሎች ሕዝቦችን አስወግደህ
በምድራቸው እርስዋን ተከልክ።
9የምታድግበትን ቦታ መነጠርህላት፤
ሥሮችዋ በመሬት ውስጥ ጠልቀው መሠረት ያዙ፤
በምድሩም ላይ ተንሰራፋች።
10ጥላዋ ተራራዎችን
የቅርንጫፎችዋም ጥላ የሊባኖስ ዛፎችን ሸፈነ።
11ቅርንጫፎችዋን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና
እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ዘረጋች።
12ታዲያ፥ በዙሪያዋ የነበረውን አጥር ስለምን አፈረስህ?
እነሆ፥ ከዚህ የተነሣ በአጠገብዋ የሚያልፍ
ሰው ሁሉ ፍሬዋን ይቀጥፋል።
13የዱር እርያዎች ይረጋግጡአታል፤
የበረሓ አራዊትም ይመገቡአታል።
14የሠራዊት አምላክ ሆይ! ፊትህን ወደ እኛ መልስ!
ከሰማይ ወደ እኛ ወደ ታች ተመልከት፤ እይም፤
ይህን የወይን ግንድህን ጠብቅ!
15ይህችን አንተ የተከልካትን
ተንከባክበህም ያሳደግኻትን የወይን ግንድ ጠብቃት!
16ጠላቶች ቈራርጠው በእሳት አቃጥለዋታል፤
በቊጣህ ተመልከታቸው፤ አጥፋቸውም!
17በቀኝህ ያለውንና ለክብርህ ብርቱ ያደረግኸውን ጠብቀህ
በሰላም አኑረው።
18ከእንግዲህ ወዲህ ከአንተ አንርቅም፤
በሕይወት ጠብቀን፤ እኛም እናመሰግንሃለን።
19የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ!
ከተሰደድንበት መልሰን፤
እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 80: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 80
80
ስለ እስራኤል መንግሥት እንደገና መቋቋም የቀረበ ጸሎት
1የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ!
በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥
ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ። #ዘፀ. 25፥22።
2ለኤፍሬም፥ ለብንያምና ለምናሴ
ራስህን ግለጥ፤ ኀይልህን አነሣሥተህ
መጥተህ አድነን።
3አምላክ ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን፤
እንድንድን ምሕረትህን አሳየን!
4የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ!
የሕዝብህን ጸሎት ባለመቀበል ቊጣህን
የምትገልጠው እስከ መቼ ነው?
5ሐዘንን እንደ ምግብ፥ እንባንም እንደ መጠጥ
በብዛት ሰጠሃቸው።
6በዙሪያችን ያሉ መንግሥታት መሬታችንን ለመውሰድ
እርስ በእርሳቸው እንዲዋጉ አደረግህ፤
ጠላቶቻችን ሁሉ ይሳለቁብናል።
7የሠራዊት አምላክ ሆይ! ከተሰደድንበት መልሰን!
እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።
8የወይን ሐረግን ከግብጽ አመጣህ፤
ሌሎች ሕዝቦችን አስወግደህ
በምድራቸው እርስዋን ተከልክ።
9የምታድግበትን ቦታ መነጠርህላት፤
ሥሮችዋ በመሬት ውስጥ ጠልቀው መሠረት ያዙ፤
በምድሩም ላይ ተንሰራፋች።
10ጥላዋ ተራራዎችን
የቅርንጫፎችዋም ጥላ የሊባኖስ ዛፎችን ሸፈነ።
11ቅርንጫፎችዋን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና
እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ዘረጋች።
12ታዲያ፥ በዙሪያዋ የነበረውን አጥር ስለምን አፈረስህ?
እነሆ፥ ከዚህ የተነሣ በአጠገብዋ የሚያልፍ
ሰው ሁሉ ፍሬዋን ይቀጥፋል።
13የዱር እርያዎች ይረጋግጡአታል፤
የበረሓ አራዊትም ይመገቡአታል።
14የሠራዊት አምላክ ሆይ! ፊትህን ወደ እኛ መልስ!
ከሰማይ ወደ እኛ ወደ ታች ተመልከት፤ እይም፤
ይህን የወይን ግንድህን ጠብቅ!
15ይህችን አንተ የተከልካትን
ተንከባክበህም ያሳደግኻትን የወይን ግንድ ጠብቃት!
16ጠላቶች ቈራርጠው በእሳት አቃጥለዋታል፤
በቊጣህ ተመልከታቸው፤ አጥፋቸውም!
17በቀኝህ ያለውንና ለክብርህ ብርቱ ያደረግኸውን ጠብቀህ
በሰላም አኑረው።
18ከእንግዲህ ወዲህ ከአንተ አንርቅም፤
በሕይወት ጠብቀን፤ እኛም እናመሰግንሃለን።
19የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ!
ከተሰደድንበት መልሰን፤
እንድንድን ምሕረትህን አሳየን።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997