መጽሐፈ መዝሙር 81
81
የክብረ በዓል መዝሙር
1ለመከታችን ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ!
ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ!
2መዝሙር ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ፤
በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚያሰኝ ዜማ አሰሙ።
3ለበዓሉ ክብር መለከት ንፉ፤
አዲስ ጨረቃ ስትወጣና ሙሉ ጨረቃ ስትሆን ይህንኑ አድርጉ። #ዘኍ. 10፥10።
4ይህ ለእስራኤል የተደነገገ፥
የያዕቆብ አምላክ የሰጠው ሥርዓት ነው።
5እርሱ ይህን ትእዛዝ ለዮሴፍ ልጆች የሰጣቸው
ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ነው።
ያልታወቀ ድምፅ እንዲህ ሲል እሰማለሁ፤
6“እኔ ከትከሻችሁ ሸክምን አወረድኩላችሁ፤
የጡቡን ሸክም ከላያችሁ እንድትጥሉት አደረግሁ፤
7በመከራ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ ጠራችሁኝ፤
እኔም አዳንኳችሁ፤
ከመሰወሪያ ስፍራዬ፥ ከሞገድ ውስጥ ሰማኋችሁ፤
በክርክር ምንጮች አጠገብ ፈተንኳችሁ። #ዘፀ. 17፥7፤ ዘኍ. 20፥13።
8ሕዝቤ ሆይ! የማስጠንቀቂያ ንግግሬን ስማ!
እስራኤል ሆይ! ብታዳምጡኝ ምንኛ መልካም ነበር!
9ባዕድ አምላክ አይኑርህ፤
እርሱንም አታምልክ።
10ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፤
ጠይቅ እንጂ የሚያስፈልግህን ሁሉ እሰጥሃለሁ። #ዘፀ. 20፥2-3፤ ዘዳ. 5፥6-7።
11“ሕዝቤ ግን እኔን አልሰማኝም፤
እስራኤል አልታዘዘልኝም።
12ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥
የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው።
13ሕዝቤ እኔን ቢሰማኝ፥
እስራኤልም እኔን ቢታዘዘኝ ኖሮ፥
14እኔ እግዚአብሔር ጠላቶቹን በኀያል ሥልጣኔ
ድል በነሣሁለት ነበር።
15እኔን የሚጠሉ ሁሉ
በፍርሃት በእግሬ ሥር ይደፋሉ፤
ቅጣታቸውም ለዘለዓለም ይጸናል።
16እናንተን ግን ጥሩ ስንዴ እመግባችኋለሁ፤
ከአለት ከሚገኘው ማርም አጠግባችኋለሁ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 81: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 81
81
የክብረ በዓል መዝሙር
1ለመከታችን ለእግዚአብሔር በደስታ ዘምሩ!
ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ!
2መዝሙር ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ፤
በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚያሰኝ ዜማ አሰሙ።
3ለበዓሉ ክብር መለከት ንፉ፤
አዲስ ጨረቃ ስትወጣና ሙሉ ጨረቃ ስትሆን ይህንኑ አድርጉ። #ዘኍ. 10፥10።
4ይህ ለእስራኤል የተደነገገ፥
የያዕቆብ አምላክ የሰጠው ሥርዓት ነው።
5እርሱ ይህን ትእዛዝ ለዮሴፍ ልጆች የሰጣቸው
ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ነው።
ያልታወቀ ድምፅ እንዲህ ሲል እሰማለሁ፤
6“እኔ ከትከሻችሁ ሸክምን አወረድኩላችሁ፤
የጡቡን ሸክም ከላያችሁ እንድትጥሉት አደረግሁ፤
7በመከራ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ ጠራችሁኝ፤
እኔም አዳንኳችሁ፤
ከመሰወሪያ ስፍራዬ፥ ከሞገድ ውስጥ ሰማኋችሁ፤
በክርክር ምንጮች አጠገብ ፈተንኳችሁ። #ዘፀ. 17፥7፤ ዘኍ. 20፥13።
8ሕዝቤ ሆይ! የማስጠንቀቂያ ንግግሬን ስማ!
እስራኤል ሆይ! ብታዳምጡኝ ምንኛ መልካም ነበር!
9ባዕድ አምላክ አይኑርህ፤
እርሱንም አታምልክ።
10ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፤
ጠይቅ እንጂ የሚያስፈልግህን ሁሉ እሰጥሃለሁ። #ዘፀ. 20፥2-3፤ ዘዳ. 5፥6-7።
11“ሕዝቤ ግን እኔን አልሰማኝም፤
እስራኤል አልታዘዘልኝም።
12ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥
የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው።
13ሕዝቤ እኔን ቢሰማኝ፥
እስራኤልም እኔን ቢታዘዘኝ ኖሮ፥
14እኔ እግዚአብሔር ጠላቶቹን በኀያል ሥልጣኔ
ድል በነሣሁለት ነበር።
15እኔን የሚጠሉ ሁሉ
በፍርሃት በእግሬ ሥር ይደፋሉ፤
ቅጣታቸውም ለዘለዓለም ይጸናል።
16እናንተን ግን ጥሩ ስንዴ እመግባችኋለሁ፤
ከአለት ከሚገኘው ማርም አጠግባችኋለሁ።”
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997