መጽሐፈ መዝሙር 84
84
የእግዚአብሔርን ቤት መናፈቅ
1የሠራዊት አምላክ ሆይ!
ቤተ መቅደስህ ምንኛ ተወዳጅ ነው!
2የቤተ መቅደስህን አደባባይ በጣም እናፍቃለሁ፤
ለሕያው አምላክ በሙሉ ልቤ በደስታ እዘምራለሁ።
3ንጉሤና አምላኬ የሠራዊት ጌታ ሆይ!
ድንቢጦች ለመኖሪያቸው ጎጆ ሠርተዋል፤
ዋኖሶችም ጫጩቶቻቸውን የሚያኖሩበት
በመሠዊያዎችህ አጠገብ ቤት አላቸው።
4ዘወትር የምስጋና መዝሙር ለአንተ እያቀረቡ
በመቅደስህ የሚኖሩ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
5ወደ ጽዮን ተራራ መንፈሳዊ ጒዞ ለማድረግ የሚፈልጉና
የአንተን ርዳታ የሚያገኙ
እንዴት የተባረኩ ናቸው?
6ባካ በተባለው ደረቅ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ
እግዚአብሔር ምንጭን ያፈልቅላቸዋል፤
የበልግም ዝናብ ኩሬዎችን ይሞላቸዋል።
7በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤
የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል።
8የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ! አድምጠኝ።
9አምላክ ሆይ! መርጠህ የቀባኸውን ንጉሣችንን ባርከው፤
ጋሻችን ስለ ሆነም ተመልከተው።
10በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት
በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤
በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ
በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ።
11ጌታችንና አምላካችን ሆይ!
አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤
በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤
ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
12የሠራዊት አምላክ ሆይ!
በአንተ የሚታመኑ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 84: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
መጽሐፈ መዝሙር 84
84
የእግዚአብሔርን ቤት መናፈቅ
1የሠራዊት አምላክ ሆይ!
ቤተ መቅደስህ ምንኛ ተወዳጅ ነው!
2የቤተ መቅደስህን አደባባይ በጣም እናፍቃለሁ፤
ለሕያው አምላክ በሙሉ ልቤ በደስታ እዘምራለሁ።
3ንጉሤና አምላኬ የሠራዊት ጌታ ሆይ!
ድንቢጦች ለመኖሪያቸው ጎጆ ሠርተዋል፤
ዋኖሶችም ጫጩቶቻቸውን የሚያኖሩበት
በመሠዊያዎችህ አጠገብ ቤት አላቸው።
4ዘወትር የምስጋና መዝሙር ለአንተ እያቀረቡ
በመቅደስህ የሚኖሩ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
5ወደ ጽዮን ተራራ መንፈሳዊ ጒዞ ለማድረግ የሚፈልጉና
የአንተን ርዳታ የሚያገኙ
እንዴት የተባረኩ ናቸው?
6ባካ በተባለው ደረቅ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ
እግዚአብሔር ምንጭን ያፈልቅላቸዋል፤
የበልግም ዝናብ ኩሬዎችን ይሞላቸዋል።
7በመጓዝ ላይ ሳሉ ብዙ ብርታትን ያገኛሉ፤
የአማልክትንም አምላክ በጽዮን ያዩታል።
8የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ፤
የያዕቆብ አምላክ ሆይ! አድምጠኝ።
9አምላክ ሆይ! መርጠህ የቀባኸውን ንጉሣችንን ባርከው፤
ጋሻችን ስለ ሆነም ተመልከተው።
10በሌላ ስፍራ አንድ ሺህ ቀን ከመቈየት
በመቅደስህ አንድ ቀን መዋል የተሻለ ነው፤
በክፉዎች ቤት ከምኖር ይልቅ
በእግዚአብሔር ቤት ዘበኛ ሆኜ መኖርን እመርጣለሁ።
11ጌታችንና አምላካችን ሆይ!
አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤
በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤
ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
12የሠራዊት አምላክ ሆይ!
በአንተ የሚታመኑ እንዴት የተባረኩ ናቸው!
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997