የዮሐንስ ራእይ 10
10
መልአኩና ትንሽቱ የብራና ጥቅል መጽሐፍ
1ከዚህ በኋላ ደመና የለበሰ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱ ዙሪያ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ፥ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ 2የተከፈተች ትንሽ የብራና ጥቅል መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፥ ግራ እግሩንም በምድር ላይ አኖረ፤ 3የሚያገሣ የአንበሳን ድምፅ በመሰለ ታላቅ ድምፅም ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን አሰሙ። 4ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ እኔ ልጽፍ አሰብኩ፤ ነገር ግን “ሰባቱ ነጐድጓዶች የተናገሩትን አሽገህ በምሥጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው!” የሚል ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ።
5ከዚህ በኋላ በባሕርና በምድር ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሣና 6ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚኖረው፥ ሰማይንና በእርሱ ውስጥ ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋ ውስጥ ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ውስጥ ያሉትን በፈጠረው አምላክ ስም ምሎ እንዲህ አለ፦ “ከእንግዲህ ወዲህ አይዘገይም! 7ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ እምቢልታውን በሚያሰማባቸው ቀኖች ለአገልጋዮቹ ለነቢያት ባስታወቃቸው መሠረት የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል።” #ዘፀ. 20፥11፤ ዘዳ. 32፥40፤ ዳን. 12፥7፤ አሞጽ 3፥7። 8ከዚያ በኋላ ከሰማይ የሰማሁት ድምፅ “በባሕርና በምድር ላይ በቆመው መልአክ እጅ ላይ ያለውንና የተከፈተውን ጥቅል መጽሐፍ ሂድና ውሰድ” ሲል እንደገና ተናገረኝ።
9ወደ መልአኩም ሄጄ “ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ስጠኝ” አልኩት፤ እርሱም “ውሰድና ብላት፤ በሆድህ መራራ ትሆናለች፤ በአፍህ ግን እንደ ማር. ትጣፍጣለች” አለኝ።
10እኔም ትንሽቱን የብራና ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላኋት፤ በአፌም እንደ ማር. ጣፈጠች፤ ከበላኋት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ። #ዕዝ. 2፥8-33። 11ከዚህ በኋላ “ስለ ብዙ ወገኖች፥ ሕዝቦች፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ስለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ” ተብሎ ተነገረኝ።
Currently Selected:
የዮሐንስ ራእይ 10: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997