የዮሐንስ ራእይ 9
9
1አምስተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እነሆ፥ ከሰማይ ወደ ምድር የወደቀ አንድ ኮከብ አየሁ፤ የጥልቁ ጒድጓድ መክፈቻ ተሰጠው። 2እርሱ የጥልቁን ጒድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጥልቁ ጒድጓድ ወጣ፤ ከጒድጓዱ በወጣው ጢስ ምክንያት ፀሐይና አየር ጨለሙ፤ #ዘፍ. 19፥28። 3ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤ የምድር ጊንጦችን ኀይል የመሰለ ኀይል ተሰጣቸው፤ #ዘፀ. 10፥12-15። 4የምድርን ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ነገር ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጐዱ ተነገራቸው፤ መጒዳት ያለባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማኅተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነበር። #ሕዝ. 9፥4። 5እነርሱንም ቢሆን አምስት ወር ለማሠቃየት እንጂ ለመግደል ፈቃድ አልተሰጣቸውም፤ አንበጣዎቹ የደረሰባቸው ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚሰማው ዐይነት ያለ ነው። 6በእነዚያ ቀኖች ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን አያገኙትም፤ ለመሞትም ይመኛሉ፤ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል። #ኢዮብ 3፥21፤ ኤር. 8፥3።
7አንበጣዎቹ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶችን ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር፤ #ኢዩ. 2፥4። 8የሴት ጠጒር የመሰለ ጠጒር ነበራቸው፤ ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር፤ #ኢዩ. 1፥16። 9የብረት ጥሩር የሚመስል ጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸው ድምፅ ወደ ጦርነት የሚጋልቡ ብዙ ፈረሶችና ሠረገላዎች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር። #ኢዩ. 2፥5። 10እንደ ጊንጥ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ በጅራታቸው ውስጥ ሰዎችን ለአምስት ወር የሚጐዱበት ኀይል ነበራቸው። 11ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱ የጥልቁ ጒድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን፥ በግሪክ አጶልዮን ይባላል፤ #9፥11 አባዶን፦ ደምሳሽ ማለት ነው።
12የመጀመሪያው ወዮ አልፎአል፥ እነሆ ከዚህ በኋላ ሌላ ሁለት ወዮ ገና ይመጣል።
13ስድስተኛው መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ካለው በወርቅ ከተሠራው ከመሠዊያው ቀንዶች ድምፅ ሲወጣ ሰማሁ። #ዘፀ. 30፥1-3። 14ድምፁም እምቢልታ የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ፥ “በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው!” አለው። 15ለዚህ ሰዓትና ለዚህ ቀን፥ ለዚህ ወርና ለዚህ ዓመት የተዘጋጁት አራቱ መላእክት የሰውን ዘር አንድ ሦስተኛ እንዲገድሉ ተፈቱ። 16የፈረሰኞቹ ሠራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን መሆኑን ሰማሁ። 17ፈረሶቹንና በፈረሶቹ ላይ የተቀመጡትን ሰዎች በራእይ ያየኋቸው እንደሚከተለው ነበር፦ በደረታቸው ላይ የነበረው ጥሩር እንደ እሳት ፍም ቀይ፥ እንደ ያክንት ጥቊር ሰማያዊ፥ እንደ ዲን ቢጫ ይመስል ነበር፤ የፈረሶቹም ራስ የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር፤ ከአፋቸው እሳትና ጢስ ዲንም ይወጣ ነበር፤ 18ከአፋቸው ባወጡት እሳት፥ ጢስና ዲን በእነዚህ በሦስቱ መቅሠፍቶች የሰው ዘር አንድ ሦስተኛ ተገደለ። 19የፈረሶቹ ኀይል በአፋቸውና በጅራታቸው ነበር፤ ጅራታቸው እባብ ይመስላል፤ የእባብ ራስም አለው፤ ሰውንም የሚጐዱት በእርሱ ነበር።
20በእነዚህ መቅሠፍቶች ከሞት የተረፉት የሰው ዘር ከእጃቸው ሥራ ተመልሰው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወርቅ፥ ከብር፥ ከናስ፥ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ ማየት ወይም መስማት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖቶች ማምለክንም አልተዉም። #መዝ. 115፥4-7፤ 135፥15-17፤ ዳን. 5፥23። 21እንዲሁም ከነፍሰ ገዳይነታቸው፥ ከሟርታቸው፥ ከሴሰኛነታቸው፥ ከሌብነታቸውም ንስሓ አልገቡም።
Currently Selected:
የዮሐንስ ራእይ 9: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997