ወደ ሮም ሰዎች 3
3
የአይሁድ አለማመን
1እንግዲህ አይሁዳዊ ከአሕዛብ የሚበልጠው በምንድን ነው? የመገረዝስ ጥቅሙ ምንድን ነው? 2በእርግጥ አይሁዳዊ መሆን በብዙ መንገድ ብልጫ አለው፤ ዋናው ነገር እግዚአብሔር ቃሉን ለአይሁድ ዐደራ መስጠቱ ነው። 3ታዲያ፥ ከአይሁድ አንዳንዶቹ ታማኞች ሆነው ባይገኙ፥ የእነርሱ ታማኞች አለመሆን የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን? 4ከቶ አያስቀርም!
“ከቃልህ የተነሣ እውነተኛ ትሆናለህ፤
ባላጋራህንም በፍርድ ትረታለህ”
ተብሎ እንደ ተጻፈው ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም እግዚአብሔር እውነተኛ ነው። #መዝ. 51፥4።
5ነገር ግን የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያሳይ ከሆነ እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ስለ ኃጢአታችን ቢቀጣን ትክክለኛ ፈራጅ አይደለም ማለት ነውን? እዚህ ላይ የምናገረው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነው። 6ፈጽሞ አይደለም! እንዲህ ከሆነማ እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዴት ይፈርዳል?
7ነገር ግን የእኔ ሐሰተኛነት የእግዚአብሔርን እውነት በመግለጥ፥ የክብሩን ብዛት የሚያሳይ ከሆነ ታዲያ፥ እኔ እንደ ኃጢአተኛ የሚፈረድብኝ ስለ ምንድን ነው? 8አንዳንድ ሰዎች “መልካም ነገር እንድናገኝ ክፉ ነገር እናድርግ” እያልኩ የማስተምር አስመስለው ይከሱኛል፤ ስለዚህ እንዲህ ባሉት ላይ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።
ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑ
9ታዲያ፥ እኛ አይሁድ ከአሕዛብ እንበልጣለን ማለት ነውን? ከቶ አይደለም! ሰዎች ሁሉ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ቀደም ብዬ አስረድቻለሁ። 10እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦
“አንድ እንኳ ጻድቅ ሰው የለም፤ አንድ እንኳን የለም፤
11አስተዋይም የለም፤
እግዚአብሔርንም የሚፈልግ አንድም የለም።
12ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤
በአንድነት ሆነው ተሳስተዋል።
ደግ ሥራ የሚሠራ አንድ ሰው እንኳ የለም። #መዝ. 14፥1-3፤ 53፥1-3።
13ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር
አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤
በምላሳቸው ያታልላሉ፤
የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤ #መዝ. 5፥9፤ 140፥3።
14አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል። #መዝ. 10፥7።
15እግራቸው ሰውን ለመግደል የፈጠነ ነው፤
16በመንገዳቸው የሚገኘው ጥፋትና ጒስቊልና ነው።
17የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ #ኢሳ. 59፥7-8።
18እግዚአብሔርን ከቶ አይፈሩም።” #መዝ. 36፥1።
19የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል። 20ስለዚህ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት፥ ሕግን በመፈጸም አይጸድቅም፤ ሕግ የሚያሳየው ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ መሆኑን ነው። #መዝ. 36፥1።
ጽድቅ በእምነት
21አሁን ግን እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያጸድቅበት መንገድ ያለ ሕግ መሆኑ ተገልጦአል፤ ይህም በሙሴ ሕግና በነቢያት ተመስክሮአል። 22ስለዚህ እግዚአብሔር ምንም ልዩነት ሳያደርግ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ ሁሉ ጽድቅን ይሰጣል። #ገላ. 2፥16። 23ሰዎች ሁሉ ኃጢአት ሠርተዋል፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውንም ክብር አጥተዋል። 24ስለዚህ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው በአዳኝነት ሥራ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ይጸድቃሉ። 25እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ በደሙ የኃጢአታቸውን ስርየት እንዲያገኙ ነው፤ እግዚአብሔር ይህን ማድረጉ በትዕግሥቱ የቀድሞውን ኃጢአት እንዳልነበረ በማድረግ የራሱን ትክክለኛ ፍርድ ለመግለጥ ነው። 26በአሁኑም ዘመን እግዚአብሔር ራሱ ጻድቅ መሆኑን የሚያሳየው በኢየሱስ የሚያምኑትን ሁሉ በማጽደቅ ነው።
27እንግዲህ የምንመካበት ነገር ምን አለ? በምንም አንመካም! የማንመካበትስ ምክንያት ምንድን ነው? ሕግን ስለምንፈጽም ነውን? አይደለም፤ ነገር ግን በእምነት ነው። 28ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን የሚያጸድቀው፥ ሰው የሕግን ሥራ በመፈጸሙ ሳይሆን በእምነት መሆኑን እንገነዘባለን። 29ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? በእርግጥ የአሕዛብም አምላክ ነው። 30እግዚአብሔር አንድ ነው፤ አይሁድንም ሆነ አሕዛብን በእምነት የሚያጸድቅ እርሱ ነው። #ዘዳ. 26፥4፤ ገላ. 3፥20። 31ታዲያ፥ በእምነት ምክንያት ሕግን እንሽራለን ማለት ነውን? አይደለም፤ ይልቅስ ሕግን አጥብቀን እንይዛለን።
Currently Selected:
ወደ ሮም ሰዎች 3: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997