ወደ ሮም ሰዎች 4
4
አብርሃም በእምነት መጽደቁ
1እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም አገኘ የምንለው ምንድን ነው? 2አብርሃም የጸደቀው በሥራ ቢሆን ኖሮ፥ የሚመካበት ነገር ባገኘ ነበር፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ፊት መመካት አይችልም። 3ቅዱስ መጽሐፍ “አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” ይላል። #ዘፍ. 15፥6፤ ገላ. 3፥6። 4የሚሠራ ሰው የሚያገኘው ደመወዝ ተገቢ የጒልበቱን ዋጋ ነው እንጂ ስጦታ አይደለም። 5ሰው መልካም ሥራ ባይኖረው እንኳ ኃጢአተኞችን በሚያጸድቅ አምላክ ካመነ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል። 6ዳዊትም በበኩሉ እግዚአብሔር ያለ መልካም ሥራ የሚያጸድቀው ሰው ምን ያኽል የተባረከ መሆኑን ሲገልጥ እንዲህ ብሎአል፦
7“በደላቸው ይቅር የተባለላቸውና
ኃጢአታቸው የተደመሰሰላቸው ሰዎች
የተባረኩ ናቸው!
8ጌታ ኃጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው
የተባረከ ነው!” #መዝ. 32፥1-2።
9ታዲያ፥ ዳዊት የተናገረው ይህ በረከት ለተገረዙት ብቻ ነውን? ወይስ ላልተገረዙትም? ላልተገረዙትም ነው፤ “አብርሃም በእግዚአብሔር ስላመነ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” ብለናል።
10እንግዲህ አብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ የተቈጠረለት መቼ ነው? ከመገረዙ በፊት ነውን ወይስ ከተገረዘ በኋላ? ከመገረዙ በፊት ነው እንጂ ከተገረዘ በኋላ አይደለም። 11አብርሃም ገና ከመገረዙ በፊት እምነቱ ጽድቅ ሆኖ እንደ ተቈጠረለት ማረጋገጫ ምልክት እንዲሆነው ተገረዘ፤ ስለዚህ አብርሃም፥ ሳይገረዙ ለሚያምኑና እምነታቸው ጽድቅ ሆኖ ለሚቈጠርላቸው ሁሉ አባት ነው። #ዘፍ. 17፥10። 12እንዲሁም አብርሃም ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት አባት የሆነበትም ምክንያት በመገረዛቸው ብቻ ሳይሆን እርሱ ከመገረዙ በፊት የነበረውን እምነት በመከተላቸውም ጭምር ነው።
ስለ እምነት የተሰጠ ተስፋ
13ለአብርሃምና ለዘሩ ዓለምን እንደሚወርስ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠው በእምነት ስላገኘው ጽድቅ ነው እንጂ ሕግን በመፈጸሙ አይደለም። #ዘፍ. 17፥4-6፤ 22፥17-18፤ ገላ. 3፥29። 14የተስፋው ወራሾች ሕግን የሚፈጽሙ ሰዎች ከሆኑማ እምነት ዋጋ አይኖረውም፤ ተስፋም ከንቱ መሆኑ ነው። #ገላ. 3፥18። 15ሕግ የሚያመጣው የእግዚአብሔርን ቊጣ ነው፤ ሕግ ከሌለ ግን ሕግን የመተላለፍ በደል አይኖርም።
16ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና። #ገላ. 3፥7። 17ስለ አብርሃም፦ “የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም የተሰጠው እርሱ የሞቱትን በሚያስነሣውና የሌለውን እንዲኖር በሚያደርገው አምላክ ስለ አመነ ነበር። #ዘፍ. 17፥5። 18አብርሃም ዘርህ እጅግ ይበዛል ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ሕዝብ አባት እንደሚሆን ያመነውና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ በማይጣልበት ነገር ነው። #ዘፍ. 15፥5። 19ዕድሜው መቶ ዓመት ያኽል ስለ ነበረ በሥጋው መድከም እንደ ሞተ በመሆን ምክንያት መውለድ እንደማይችልና ሣራም መኻንና ያረጀች በመሆንዋ መውለድ እንደማትችል ቢያውቅም በእምነቱ ደካማ አልሆነም። #ዘፍ. 17፥17። 20በእምነቱ ብርቱ ሆኖ ለእግዚአብሔር ክብር ሰጠ እንጂ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ባለማመን ከቶ አልተጠራጠረም። 21እግዚአብሔር የሰጠውንም ተስፋ የሚፈጽም መሆኑን በሙሉ ልብ ያምን ነበር። 22ስለዚህ ነው ለአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ የተቈጠረለት። 23ነገር ግን “ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” የሚለው ቃል የተጻፈው ለአብርሃም ብቻ ሳይሆን 24ለእኛም ጭምር ነው፤ ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ባስነሣው አምላክ ለምናምን ለእኛም እምነታችን ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርልናል። 25ይህ ጌታችን ኢየሱስም ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ የተሰጠውና እኛንም ለማጽደቅ ከሞት የተነሣው ነው። #ኢሳ. 53፥4-5።
Currently Selected:
ወደ ሮም ሰዎች 4: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997