1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:1-7

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13:1-7 መቅካእኤ

በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር፥ ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ ናስ ወይም እንደሚንሿሿ ጸናጽል ነኝ። ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ያለኝን ሁሉ ለድኾች ባካፍል፥ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ለእሳት አሳልፌ ብሰጥ፥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሳል፤ ቸርነትንም ያደርጋል። ፍቅር አይቀናም፤ አይመካም፤ አይታበይም፤ ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም። ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም። ፍቅር ሁሉን ይታገሣል፤ ሁሉን ያምናል፤ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፤ በሁሉ ነገር ይጸናል።