1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:9-11

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:9-11 መቅካእኤ

በዚህም የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል እንድንኖር እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና። ፍቅር በዚህ ነው፥ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን ነገር ግን እርሱ እንደ ወደደን እና ለኃጢአታችንም ማስተስሪያ እንዲሆን ልጁን ስለላከልን ነው። ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፥ እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።