1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8
8
ንጉሥ ስለ ማንገሥ የሕዝቡ ጥያቄ
1 #
1ዜ.መ. 6፥13። ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን ፈራጆች አድርጎ በእስራኤል ላይ ሾማቸው። 2የበኩር ልጁ ስም ኢዩኤል ሲሆን፥ የሁለተኛው ልጁ ስም አቢያ ነበረ፤ እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር። 3#1ሳሙ. 2፥12-17፤ ዘፀ. 23፥8፤ ዘዳ. 16፥19፤ ምሳ. 17፥23።ልጆቹ ግን የአባታቸውን ፈለግ አልተከተሉም፤ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከመንገዱ ወጡ፤ ጉቦ ተቀበሉ፤ ፍርድም አጣመሙ።
4ስለዚህ የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ተሰብስበው ሳሙኤል ወዳለበት ወደ ራማ መጡ። 5#ዘዳ. 17፥14-15፤ ሆሴዕ 13፥10፤ የሐዋ. 13፥21።እነርሱም፥ “አንተ አርጅተሃል፤ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም፤ ስለዚህ ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሁሉ የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” አሉት። 6ነገር ግን፥ “የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን” ማለታቸው ሳሙኤልን አላስደሰተውም፤ ስለዚህ ወደ ጌታ ጸለየ። 7#1ሳሙ. 12፥1፤12-13፤ መሳ. 8፥22-23፤ 10፥13፤ 1ነገ. 9፥9።ጌታም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ንጉሣቸው እንዳልሆን የናቁት እኔን እንጂ አንተን አይደለምና ሕዝቡ የሚሉህን ሁሉ አድምጥ። 8ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ቀን አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን በማምለክ ያደረጉትን ሁሉ በአንተም ላይ እያደረጉ ነው። 9አሁንም የሚሉህን ስማ፤ ግን በላያቸው የሚነግሠው ንጉሥ ምን እንደሚፈጽምባቸውም አሳውቃቸው፤ በብርቱም አስጠንቅቃቸው።”
10ሳሙኤልም የጌታን ቃል ሁሉ፥ ንጉሥ እንዲነግሥላቸው ለጠየቁት ሕዝብ ተናገረ። 11#1ሳሙ. 10፥25፤ ዘዳ. 17፥14-20፤ 1ነገ. 12።እንዲም አለ፤ “በላያችሁ የሚነግሠው ንጉሥ የሚያደርግባችሁ ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሠረገሎቹም ፊት ይሮጣሉ። 12#2ሳሙ. 15፥1፤ 1ነገ. 1፥5።አንዳንዶቹን ሻለቆችና አምሳ አለቆች ያደርጋቸዋል፤ ሌሎቹን መሬቱን እንዲያርሱና እህሉን እንዲያጭዱ፥ ሌሎቹን ደግሞ የጦር መሣሪያና ለሠረገላ የሚሆኑትን ዕቃዎች እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል። 13ሴቶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሽቶ ቀማሚ፥ ወጥ ሠሪዎችና እንጀራ ጋጋሪዎች ያደርጋቸዋል። 14#ዘዳ. 14፥22-23።ከእርሻችሁ፥ ከወይንና ከወይራ ተክል ቦታዎቻችሁ ምርጥ ምርጡን ወስዶ ለባለሟሎቹ ይሰጣቸዋል። 15#1ሳሙ. 22፥7፤ 1ነገ. 21፥1-24፤ ሕዝ. 46፥18።ከእህላችሁና ከወይናችሁ ከዐሥር አንዱን ወስዶ ለሹማምቱና ለባለሟሎቹ ይሰጣቸዋል። 16ወንድና ሴት አሽከሮቻችሁን እንዲሁም ምርጥ ከብቶቻችሁንና አህዮቻችሁን ለራሱ ወስዶ ያሠራቸዋል። 17#1ነገ. 12፥4።ከበግና ከፍየል መንጎቻችሁ አንድ ዐሥረኛውን ለራሱ ይወስዳል፤ እናንተም ባርያዎቹ ትሆናላችሁ። 18ያም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ከመረጣችሁት ንጉሥ የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ ነገር ግን በዚያ ቀን ጌታ አይመልስላችሁም።” 19#1ሳሙ. 10፥19።ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን መስማት እምቢ በማለት፥ እንዲህ አሉ፦ “አይሆንም፤ ንጉሥ እንዲነግሥልን እንፈልጋለን። 20እኛም እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች የሚመራንና ከፊታችን የሚሄድ፥ ጦርነታችንንም የሚዋጋልን ንጉሥ ያለን ሕዝቦች እንሆናለን።” 21ሳሙኤልም ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ሰማ፤ ያንኑ ለጌታ ተናገረ። 22ጌታም፥ “አድምጣቸው፤ ንጉሥም አንግሥላቸው” አለው። ከዚያም ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዳችሁ ወደ ከተማችሁ ተመለሱ” አላቸው።
Currently Selected:
1ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ