2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6
6
1እንግዲህ፥ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን፥ የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ እንለምናለን፤ 2እርሱ፥
#
ኢሳ. 49፥8። “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤
በመዳንም ቀን ረዳሁህ፤”
ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳንም ቀን አሁን ነው። 3አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በማናቸውም መንገድ አንዳች ዕንቅፋት አናኖርም። 4ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች በሁሉም መንገድ ራሳችንን እንሰጣለን፤ በታላቅ ጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ 5#የሐዋ. 16፥23።በመገረፍ፥ በመታሰር፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመራብ፥ 6በንጽሕና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ በእውነተኛ ፍቅር፥ 7በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝ እጅና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ 8በክብርና በውርደት፥ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል። አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ 9ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ 10ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድኾች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።
11የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ! በግልጽ ነግረናችኋል፥ ልባችንንም ለእናንተ ወለል አድርገን ከፍተንላችኋል። 12እኛ ፍቅራችንን አልቆጠብንባችሁም፥ እናንተ ግን ቆጥባችሁብናል። 13ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን ይህን እላችኋለሁ፤ እናንተም ደግሞ ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱልን።
ከማያምኑ ሰዎች መለየት እንደሚገባ
14ከማያምኑ ጋር አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዐመፅ ጋር ምን ድርሻ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? 15ክርስቶስስ ከቤልሆር#6፥15 ግሪኩ “ቤሌየር” ይለዋል። ጋር ምን ስምምነት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? 16#1ቆሮ. 3፥16፤ 6፥19፤ ዘሌ. 26፥12፤ ሕዝ. 37፥27።የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥
በእነርሱ እኖራለሁ፤
በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤
አምላካቸውም እሆናለሁ፤
እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
17 #
ኢሳ. 52፥11። #
2ሳሙ. 7፥14፤ 1ዜ.መ. 17፥13፤ ኢሳ. 43፥6፤ ኤር. 31፥9። ስለዚህም ጌታ
ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤
ርኩስንም አትንኩ፤
እኔም እቀበላችኋለሁ፥
18“ለእናንተም አባት እሆናለሁ፤
እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ፤”
ይላል ሁሉንም የሚገዛ ጌታ።
Currently Selected:
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ