2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 16
16
ዳዊትና ጺባ
1 #
2ሳሙ. 4፥4፤ 9፥1-13፤ 19፥18፤25። ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት እልፍ ብሎ እንደ ሄደ፥ ጺባ የተባለው የመፊቦሼት አገልጋይ፥ ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ ጥፍጥፍ ዘቢብ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች እየነዳ ሊያገኘው መጣ። 2ንጉሡም ጺባን፥ “ይህን ያመጣኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም “አህዮቹን የንጉሡ ቤተሰቦች እንዲቀመጡባቸው፥ ዳቦውንና ፍራፍሬውን ወጣቶቹ እንዲበሉት፥ የወይን ጠጁን ደግሞ በምድረ በዳ የደከሙት እንዲጠጡት ነው” አለው። 3#2ሳሙ. 19፥26-27።ከዚያም ንጉሡ፥ “የጌታህ ልጅ የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም፥ “ ‘የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል’ ብሎ ስለሚያስብ፥ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” አለው። 4#2ሳሙ. 19፥30።ከዚያም ንጉሡ ጺባን፥ “የመፊቦሼት የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ ያንተ ነው” አለው። ጺባም፥ “እጅ እነሣለሁ፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው።
የሺምዒ ንጉሥ ዳዊትን መርገም
5 #
2ሳሙ. 3፥16፤ 19፥17፤22-23፤ 1ነገ. 2፥8። ንጉሥ ዳዊት ወደ ባሑሪም ሲደርስ፥ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ወጣ፤ ስሙ ሺምዒ ሲሆን የጌራ ልጅ ነው፤ እየተራገመም ወደ እርሱ ይመጣ ነበር። 6በንጉሡም ቀኝና ግራ ሕዝቡ ሁሉና ኀያላኑ ሁሉ ቢኖሩም እንኳ፥ ወደ ዳዊትና ወደ ንጉሥ ዳዊት አገልጋዮችም ድንጋይ ይወረውር ነበር፤ 7ሺምዒ እንዲህ ብሎ ይራገም ነበር፤ “ውጣ! ከዚህ ውጣ! አንተ የደም ሰው፤ አንተ ምናምንቴ፤ 8መንግሥቱን የወሰድክበትን የሳኦልን ቤተሰቡ ደም ሁሉ ጌታ ወደ አንተው እየመለሰው ነው። ጌታ መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አንተ የደም ሰው ስለሆንህ እነሆ፥ መጥፊያህ ደርሶአል።” 9#2ሳሙ. 19፥22፤ 1ሳሙ. 24፥15፤ 26፥6።ከዚያም የጽሩያ ልጅ አቢሳ ንጉሡን፤ “ይህ የሞተ ውሻ፥ ንጉሥ ጌታዬን እንዴት ይራገማል? ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ። 10#2ሳሙ. 15፥25-26፤ 19፥23።ንጉሡ ግን፥ “እናንት የጽሩያ ልጆች እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ጌታ፥ ‘ዳዊትን ርገመው’ ብሎት የሚረግመኝ ከሆነ፥ ‘ይህን ለምን አደረግህ’ ብሎ ማን ሊጠይቀው ይችላል?” አለው። 11#2ሳሙ. 12፥11።ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “ከአብራኬ የወጣ ልጅ ሕይወቴን ሊያጠፋት ከፈለገ፥ ይህ ብንያማዊ ቢያደርገው ምን ያስደንቃል? ስለዚህ ተዉት፤ ጌታ በል ብሎት ነውና ይራገም፤ 12ጌታ ምናልባት በዚህ ቀን መከራዬን አይቶ ስለ እርግማኑ መልካም ይመልስልኛል” አላቸው። 13#2ሳሙ. 19፥19-24።ስለዚህም ዳዊትና ሰዎቹ መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሺምዒ በተራራው አጠገብ በእርሱ ትይዩ እየሄደ ይራገም ድንጋይም ይወረውር፥ ዐፈርም ይበትን ነበር። 14ንጉሡና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ።
የኩሲና የአኪጦፌል ምክር
15በዚህን ጊዜ አቤሴሎምና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ አኪጦፌልም አብሮት ነበር። 16#2ሳሙ. 15፥32-37።የዳዊት ወዳጅ አርካዊው ሑሻይም ወደ አቤሴሎም መጥቶ “ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ፤ ንጉሥ ሆይ፤ ለዘለዓለም ንገሥ” አለው። 17አቤሴሎምም፥ ሑሻይን፥ “ለወዳጅህ ያለህ ታማኝነት እስከዚህ ድረስ ነው? ለምን ከወዳጅህ ጋር አልሄድህም?” ሲል ጠየቀው። 18ሑሻይም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም! እኔ በጌታ፥ በዚህ ሕዝብና በእስራኤል ሰዎች ሁሉ ለተመረጠው ለእርሱ እሆናለሁ፤ አብሬውም እኖራለሁ፤ 19#2ሳሙ. 15፥34።እንግዲህ ልጁን ካላገለገልሁ ማንን ላገለግል ነው? አባትህን እንዳገለገልሁ ሁሉ፤ አንተንም አገለግላለሁ።” 20አቤሴሎምም አኪጦፌልን፤ “እስቲ ምክር አምጣ፤ ምን እናድርግ?” አለው። 21#2ሳሙ. 15፥16፤ 20፥3።አኪጦፌልም መልሶ፥ “ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ አባትህ ከተዋቸው ዕቁባቶቹ ጋር ግባና ተኛ፤ ከዚያም አንተ፥ አባትህን እጅግ የጠላህ መሆንህን መላው እስራኤል ይሰማና አብሮህ ያለው ሁሉ ክንዱ ይበረታል” አለው። 22#2ሳሙ. 12፥11-12።ስለዚህ ለአቤሴሎም በሰገነቱ ላይ ድንኳን ተከሉለት፤ እዚያም መላው እስራኤል እያየው ከአባቱ ዕቁባቶች ጋር ተኛ። 23#2ሳሙ. 15፥12፤31፤ 17፥23።በዚያም ጊዜ አኪጦፌል የሚሰጠው ምክር ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጠየቅ ይቆጠር ነበር፤ በዳዊትም ሆነ በአቤሴሎም የአኪጦፌል ምክር ይከበር ነበር።
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 16: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ