ወደ ቈላስይስ ሰዎች 4
4
1 #
ኤፌ. 6፥9። ጌቶች ሆይ! እናንተ ደግሞ በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና ባርያዎቻችሁን በጽድቅና በቅንነት ተመልከቱአቸው።
ተጨማሪ ምክር
2ከማመስገን ጋር በጸሎት ውስጥ ነቅታችሁ ያለማቋረጥ ትጉ፤ 3የታሰርኩበት ምክንያት የሆነውን የክርስቶስን ምሥጢር ለማወጅ እግዚአብሔር ለቃሉ በር እንዲከፍትልን ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ፤ 4ቃሉንም መናገር እንደሚገባኝ ያህል ለመግለጥ እንድችል ጸልዩልኝ።
5 #
ኤፌ. 5፥16። ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ። 6#ጥበ. 8፥12።ለእያንዳንዱ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን።
የመጨረሻ ሰላምታ
7 #
የሐዋ. 20፥4፤ 2ጢሞ. 4፥12። #
ኤፌ. 6፥21፤22። የተወደደ ወንድምና የታመነ አገልጋይ በጌታም አብሮኝ ባርያ የሆነ ቲኪቆስ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉ ይነግራችኋል፤ 8እርሱን ወደ እናንተ የላክሁበት ዋነኛ ዓላማ እኛ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደምንገኝ እንዲያሳውቃችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው፤ 9#ፊልሞ. 1፥10-12።ቲቂቆስም ከእናንተ ወገን ከሆነውና ከታመነው ከተወደደውም ወንድም ከኦኔሲሞስ ጋር አብሮ ይመጣል። በእዚህም ሥፍራ ስላለው ሁኔታ ሁሉ ያስታውቋችኋል።
10 #
የሐዋ. 19፥29፤ 27፥2፤ ፊልሞ. 1፥24፤ የሐዋ. 12፥12፤25፤ 13፥13፤ 15፥37-39። “ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ተቀበሉት፤” የሚል ትእዛዝ የተቀበላችሁለት የበርናባስ የወንድሙ ልጅ ማርቆስ እንዳረገው እንዲሁ አብሮ ከእኔ ጋር የታሰረ አርስጥሮኮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። 11ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ከተገረዙትም ወገን የሆኑ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል። 12#ቈላ. 1፥7፤ ፊልሞ. 1፥23።ከእናንተ ወገን የሆነ የክርስቶስ ባርያ ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉ ተረድታችሁና ፍጹማን ሆናችሁ እንድትቆሙ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ በጸሎቱ ይተጋል። 13ስለ እናንተ በሎዶቅያም በኢያራ ከተማም ስላሉቱ እጅግ በሥራ እንደደከመ እመሰክርለታለሁና። 14#2ጢሞ. 4፥11፤ ፊልሞ. 1፥24፤ 2ጢሞ. 4፥10፤ ፊልሞ. 1፥24።የተወደደው ሐኪም ሉቃስ ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። 15በሎዶቅያ ላሉቱ ወንድሞችና ለንምፉን በቤትዋም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ። 16ይህም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበ በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንዲነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምታገኙትን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ። 17#ፊልሞ. 1፥2።ለአክሪጳም፦ “በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት እንድትፈጽሙው ተጠንቀቅ!” በሉልኝ።
18ይህን ሰላምታ እኔ ጳውሎስ በገዛ እጄ ጽፌዋለሁ። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
Currently Selected:
ወደ ቈላስይስ ሰዎች 4: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ