የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳግም 13:1-3

ኦሪት ዘዳግም 13:1-3 መቅካእኤ

“ከመካከልህ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ተነሥቶ ምልክት ወይም ድንቅ አደርጋለሁ ቢልህ፥ የተናገረው ምልክት ወይም ድንቅ ቢፈጸም፥ ‘አንተ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት እናምልካቸው’ ቢልህ፥ አምላካችሁን ጌታ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ትወዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ አምላካችሁ ጌታ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ሕልም አላሚውን አትስሙ።