ኦሪት ዘዳግም 15
15
ዕዳ የሚሰረዝበት ዓመት
1 #
ዘዳ. 31፥10፤ ዘሌ. 25፥1-55፤ ነህ. 10፥31። “በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ታደርጋለህ። 2አፈጻጸሙም የሚከተለው ነው፦ አበዳሪ ሁሉ ለባልጀራውም ያበደረውን ይተዋል፥ ጌታ የዕዳ ምሕረት አውጆአልና፥ ያበደረውን ከባልንጀራው ወይም ከወንድሙ ዕዳውን እንዲከፍለው አይጠይቀው። 3#ዘዳ. 23፥20።ለባዕድ ያበደርከውን መጠየቅ ትችላለህ፤ ወንድምህ ከአንተ የተበደረውን ማናቸውንም ዕዳ ግን ተወው።
4 #
ዘዳ. 7፥12-14፤ 28፥1-14። “ነገር ግን አምላክህ ጌታ ትወርሳት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርክህ፥ በመካከልህ ድኻ አይኖርም። 5ይህ የሚሆነውም ለጌታ ለእግዚአብሔር ፈጽመህ ስትታዘዝና ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ብትጠነቀቅ ነው። 6#ዘዳ. 28፥12።አምላክህ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ይባርክሃል፥ አንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ ከማንም ግን አትበደርም፤ ብዙ አሕዛብን ትገዛለህ ማንም ግን አንተን አይገዛህም።
7 #
ዘፀ. 22፥25። “አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፥ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አትጨክንበት፤ ወይም እጅህን አትሰብስብበት። 8#ዘዳ. 24፥19፤ ዘሌ. 25፥35፤ መዝ. 37፥21-22፤ ምሳ. 19፥17፤ ሲራ. 29፥1-2፤ ማቴ. 5፥42።ይልቅስ እጅህን ፍታለት፤ የሚያስፈልገውንም ሁሉ አበድረው። 9#ዘዳ. 24፥15፤ ዘፀ. 22፥23-24፤ 27።‘ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ አድሮብህ፥ በችግረኛ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፥ እርሱም በአንተ ላይ ወደ ጌታ ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ! 10ይልቅስ ያለ ቅሬታ በለጋስነት በልግስና ስጠው፤ ከዚህም የተነሣ ጌታ አምላክህ በሥራህ ሁሉና እጅህ ባረፈበት በማናቸውም ነገር ይባርክሃል። 11#ዘዳ. 15፥8፤ ማቴ. 26፥11።መቼም ቢሆን በምድር ላይ ችግረኛና ድኻ መኖሩ ስለማይቀር፤ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞችህ፥ ለድኾችና ለችግረኖች እጅህን እንድትዘረጋ አዝሃለሁ።
ለአገልጋዮች የተገባ አያያዝ
12 #
ዘፀ. 21፥2-11፤ ኤር. 34፥8-22። “ወንድምህን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግሉህ፥ በሰባተኛው ዓመት ነጻ አውጣው። 13#ዘፀ. 3፥21-22፤ 12፥35-36።ነጻ በምታወጣው ጊዜ ባዶ እጁን አትስደደው። 14ከመንጋህ፥ ከአውድማህና ከወይን መጭመቂያህ በልግስና ስጠው፤ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ባረከህ መጠን ትሰጠዋለህ። 15#ዘዳ. 5፥15፤ 10፥19፤ 16፥12፤ 24፥18፤ 22።አንተም ራስህ በግብጽ ባርያ እንደ ነበርክና ጌታ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝሃለሁ።
16 #
ዘፀ. 21፥5-6። “ነገር ግን አገልጋይህ፥ አንተንና ቤተሰብህን ከመውደዱና ከአንተም ጋር ደስተኛ ከመሆኑ የተነሣ፥ ከአንተ መለየት አልፈልግም ቢልህ፥ 17ጆሮውን ከቤትህ መዝጊያ ላይ በማስደገፍ በወስፌ ትበሳዋለህ፤ ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋይህ ይሆናል። በሴት አገልጋይህም ላይ እንደዚሁ አድርግ። 18የአገልጋይህን የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፥ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና፤ እርሱን ነጻ ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ። ጌታ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።
የእንስሳት በኲራት
19 #
ዘፀ. 13፥2፤11-16፤ 22፥29-30፤ 34፥19-20፤ ዘሌ. 22፥27፤ 27፥26፤ ዘኍ. 18፥15-18። “የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኩር ሁሉ ለጌታ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ። የበሬህን በኩር አትሥራበት፤ የበግህንም በኩር አትሸልት፤ 20#ዘዳ. 12፥6-7፤17-18፤ 14፥23።እርሱ በሚመርጠው ስፍራ አንተና ቤተሰብህ በየዓመቱ በአምላክህ በጌታ ፊት ትበሉታላችሁ። 21#ዘዳ. 12፥15-16፤22-24፤ 17፥1፤ ዘሌ. 22፥17-25፤ ሚል. 1፥8።አንድ እንስሳ እንከን ያለው፥ አንካሳ ወይም ዕውር፥ ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ ለጌታ ለእግዚአብሔር አትሠዋው፤ 22በየከተሞችህም ትበላዋለህ፤ ንጹሕ ሰው ንጹሕም ያልሆነ ሚዳቋና ዋላ እንደሚበሉ ይበላዋል። 23ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 15: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ