ኦሪት ዘዳግም 17
17
1 #
ዘሌ. 22፥20። “በአምላክህ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከበሬ ወይም ከበግ ነውር ወይም ጉድለት ያለበትን ለአምላክህ ለጌታ አትሠዋ።
2“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች በአንዲቱ አብሮህ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፥#ኢያ. 7፥11፤ 15፤ 23፥16፤ መሳ. 2፥20፤ 2ነገ. 18፥12፤ ኤር. 34፥18፤ ሆሴዕ 6፥7፤ 8፥1። 3#ዘዳ. 4፥19፤ 2ነገ. 17፥16፤ 21፥3፤ 23፥5፤ ኤር. 8፥2፤ ሕዝ. 8፥16።ትእዛዜንም በመተላለፍ ባዕዳን አማልክትን ያመለከ፥ ለእርሱም ማለትም ለፀሓይ ወይም ለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ፥ 4አንተም ይህ መደረጉን ብትሰማ፥ ነገሩን በጥንቃቄ መርምር፤ የተባለውም እውነት ከሆነና እንዲህ ያለው አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ዘንድ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፥ 5ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፥ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። 6#ዘዳ. 19፥15፤ ዘኍ. 35፥30፤ ዮሐ. 8፥17፤ 2ቆሮ. 13፥1።ሞት የሚገባው ሰው፥ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፤ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል። 7#ዘዳ. 13፥6፤ 10።ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ፥ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ።
በካህናትና ዳኞች የሚሰጡ የፍርድ ውሳኔዎች
8 #
ዘፀ. 18፥13-26። “በአንድ የነፍስ ግድያ ዓይነትና በሌላ፥ በአንድ ዓይነት ሕጋዊ ክርክርና በሌላ፥ ወይም በአንድ የክስ ዓይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጉዳይ ቢነሣ፥ ከአቅምህ በላይ የሆነ ጉዳይ በከተሞችህ ውስጥ ቢያጋጥምህ፥ ተነሥተህ አምላክህ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ውጣ፤ 9#ዘዳ. 21፥5፤ 2ዜ.መ. 19፥8፤ ዕዝ. 7፥25።ወደ ሌዋውያን ካህናት በዚያም ዘመን ወደ ተሾመው ፈራጅ መጥተህ ትጠይቃለህ፥ እነርሱም የፍርዱን ነገር ይነግሩሃል። 10አንተም ጌታ በመረጠው ስፍራ እነርሱ በሚሰጡህ ውሳኔ መሠረት ፈጽም፤ ለመፈጸም የሚሰጡህን መመሪያ ሁሉ በጥንቃቄ አድርግ። 11በሚያስተምሩህ ሕግና በሚሰጡህ መመሪያዎች መሠረት ፈጽም። ከሚነግሩህ ቀኝም ግራም አትበል። 12አምላክህን ጌታን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ባለመታዘዝ የሚዳፈር፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም መካከል ክፋትን አስወግድ፥ 13#ዘዳ. 13፥12።ሕዝቡም ሁሉ ሰምቶ ይፈራል፥ ከዚያም ወዲያ አይዳፈርም።
የንጉሥ የሥልጣን ገደብ
14 #
1ሳሙ. 10—25። “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፥ ‘በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል፥#ዘዳ. 26፥1፤ 1ሳሙ. 8፥5፤19-20። 15#1ሳሙ. 9፥16፤ 10፥24፤ 16፥1-13፤ 1ነገ. 19፥15-16፤ 2ነገ. 9፥1-13።ጌታ እግዚአብሔር የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ልታነግሥ ትችላለህ፤ የምታነግሠውም ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ፥ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ። 16#ዘዳ. 28፥68፤ 1ሳሙ. 8፥10-12፤ ኢሳ. 2፥7።ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና። 17#1ነገ. 10፥10-25፤ 11፥1-8፤ ነህ. 13፥26፤ ኢሳ. 2፥7።ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፤ ብዙ ብርና ወርቅም አያግበስብስ።
18 #
ዘዳ. 31፥9፤24-26፤ ኢያ. 8፥32። “በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ የዚህን ሕግ ቅጅ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ በጥቅል መጽሐፍ ለራሱ ይጻፍ። 19#ዘዳ. 5፥32—6፥3፤ 2ሳሙ. 7፥12-16፤ 1ነገ. 2፥4፤ መዝ. 132፥11-18።አምላኩን ጌታን ማክበር ይማር ዘንድ፥ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዓት በጥንቃቄ እንዲከተል ከእርሱ ጋር ይሁን፤ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ያንብበው፤ 20እርሱና ዘሮቹ በእስራኤል ላይ ረጅም ዘመን እንዲገዙ፥ ከሕጉ ቀኝም ግራም አይበል፤ ራሱን ከሌሎች ወንድሞቹ በላይ የተሻለ አድርጎ አይኩራ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 17: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ