ኦሪት ዘዳግም 18
18
የካህናቱና የሌዋውያን ድርሻ
1 #
ዘኍ. 18፥8-9፤20-24፤ ኢያ. 13፥14፤ 18፥7፤ 2ዜ.መ. 31፥2-19፤ 1ቆሮ. 9፥13። “ሌዋውያን ካህናት፥ የሌዊ ነገድም ሁሉ ከእስራኤል ጋር የመሬት ድርሻ ወይም ርስት አይኖራቸውም፤ ድርሻቸው ነውና ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው መባ ይብሉ። 2#ዘኍ. 18፥20፤ ኢያ. 13፥33።በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ጌታ ርስታቸው ነው።
3“በሬ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፥ አገጩንናና ሆድ ዕቃውን ነው። 4#ዘዳ. 26፥1-11፤ ዘኍ. 18፥12፤ 2ዜ.መ. 31፥5፤ ነህ. 13፥10-13።የእህልህን፥ የአዲሱን ወይንህንና የዘይትህን በኵራት እንዲሁም ከበጎችህ በመጀመሪያ የተሸለተውን ጠጉር ትሰጣለህ፤ 5#ዘዳ. 10፥8፤ ኤር. 33፥18።በጌታ ስም ቆሞ ለዘለዓለም ያገለግል ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር ከነገዶችህ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል።
6“በእስራኤል ካሉት ከተሞችህ መካከል፥ አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በፍጹም ፈቃድ ጌታ ወደ መረጠው ስፍራ ቢመጣ፥ 7በጌታ ፊት ቆመው እንደ የሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ፥ እርሱም በአምላኩ በጌታ ስም ያገልግል። 8ከቤተሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳን ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።
ከአሕዛብ ልማድ ስለ መጠበቅ
9 #
ዘዳ. 12፥29-31፤ ዘሌ. 18፥24-30። “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር በምትገባበት ጊዜ፥ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተል። 10#ዘዳ. 12፥31፤ ዘፀ. 22፥18፤ ዘሌ. 18፥21፤ 19፥31፤ 20፥6፤ 27፤ 1ሳሙ. 28፥7-19፤ 2ነገ. 17፥17፤ 21፥6፤ 23፥10፤ 24፤ ኢሳ. 8፥19-20፤ ሕዝ. 21፥21።በመካከልህ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ ሟርተኛ፥ ወይም መተተኛ፥ ሞራ ገለጭ፥ ጠንቋይ 11ወይም በድግምት የሚጠነቁል፤ መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከልህ ከቶ አይገኝ። 12#ዘዳ. 9፥4።እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከእነዚህ አጸያፊ ልምዶች የተነሣም ጌታ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል። 13በአምላክህ በጌታ ፊት ነውር አልባ ሁን።”
እንደ ሙሴ ያለ ሌላ ነቢይ
14ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፥ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን ይህን እንድታደርግ ጌታ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም።
15 #
ማቴ. 17፥5፤ ማር. 9፥7፤ ሉቃ. 9፥35፤ ዮሐ. 1፥45፤ 6፥14፤ 7፥40፤ የሐዋ. 3፥22፤ 7፥37። “አምላክህ ጌታ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱን አድምጥ። 16#ዘፀ. 20፥19።በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት፥ ‘እንዳልሞት የጌታ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልስማ፤ እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግሜ አልይ’ ብለህ አምላክህን ጌታን የጠየቅኸው ይህን ነውና። 17ጌታ እንዲህ አለኝ፤ ‘የተናገሩት መልካም ነው፤ 18#ዘፀ. 4፥10-16፤ ኤር. 1፥9፤ 15፥19፤ ሕዝ. 3፥1-4።ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ፤ ቃሌን በአፉ አደርጋለሁ፤ የማዘውንም ሁሉ ይነግራቸዋል። 19#ኤር. 11፥21-23፤ አሞጽ 7፥10-17፤ የሐዋ. 3፥23።ማንም ሰው ነቢዩ በስሜ የሚናገረውን ቃሌን ባይሰማ፥ እኔ ራሴ በተጠያቂነት እይዘዋለሁ። 20#ዘዳ. 13፥2-6፤ 1ነገ. 22፥1-40፤ ኤር. 14፥13-16፤ 23፥9-40፤ 28፥1-17፤ ሕዝ. 13፥1-23።ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜ የሚናገርም ሆነ በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል።’ 21አንተም በልብህ፥ ‘በጌታ ያልተነገረውን መልእክት እንዴት ማወቅ እንችላለን?’ ብትል፥ 22ነቢዩ በጌታ ስም የተናገረው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገለጸ፥ መልእክቱ ጌታ የተናገረው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 18: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ