ኦሪት ዘዳግም 26
26
በኲራትና አሥራት
1 #
ዘዳ. 14፥22-29፤ 16፥1-17፤ ዘፀ. 22፥29፤ ዘሌ. 23፥9-21፤ ዘኍ. 28፥26-31። “ጌታ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ ስትወርሳትና ስትኖርባት፥ 2#ዘዳ. 12፥5፤ 11፤ 18፥4፤ ዘፀ. 23፥19፤ 34፥26፤ ጦቢ. 1፥6-7።ጌታ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል በኲራቱን ሁሉ ውሰድ፤ በቅርጫትም ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ጌታ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ። 3#ዘዳ. 1፥8፤20-21።በዚያም ወቅት ለሚያገለግለው ካህን፥ ‘ጌታ ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደገባሁ ዛሬ በጌታ እግዚአብሔር ፊት እናገራለሁ’ በለው።
4“ካህኑም ቅርጫቱን ከእጅህ ተቀብሎ በጌታ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል። 5#ዘፍ. 46፥5-7፤26-27፤ ዘፀ. 1፥7፤ 9፤ የሐዋ. 7፥14-15።አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ። 6#ዘፀ. 1፥8-22፤ 2፥23-25፤ 3፥7-10፤ 6፥9፤ ዘኍ. 20፥15-16፤ 1ነገ. 12፥4።ግብፃውያን ግን አንገላቱን፤ አሠቃዩንም፤ በባርነት የጭካኔ ቀንበር ጫኑብን። 7ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ ወደ ሆነው ወደ ጌታ ጮኽን፤ ጌታም ጩኸታችንን ሰማ። ጉስቁልናችንን፥ ድካማችንንና መጨቆናችንን ተመለከተ። 8#ዘዳ. 4፥34፤ 6፥21-22፤ ዘፀ. 12፥51።ከዚያም በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅ ድንጋጤ፥ በተአምራትና በድንቅም ጌታ ከግብጽ አወጣን። 9#ዘፀ. 3፥8።ወደዚህም ስፍራም አስገብቶን ወተትና ማር የምታፈስሰውንም ይህችን ምድር ሰጠን። 10እነሆም፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት አቅርቤአለሁ።’ አንተም በአምላክህ በጌታ ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በጌታ ፊት ስገድ። 11#ዘዳ. 12፥7፤ 12።አንተም በመካከልህም ያለ ሌዋዊና መጻተኛ ጌታ እግዚአብሔር ለአንተና ለቤትህ በሰጠው ቸርነት ሁሉ ደስ ይበላችሁ።
12 #
ዘዳ. 14፥28-29። “አሥራት በምታወጣት በሦስተኛው ዓመት ከምርትህ አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፥ 13ከዚያ በኋላ ለጌታህ እግዚአብሔር እንዲህ በል፦ ‘ከቤቴ የተቀደሰውን ድርሻ ወስጄ በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም። 14#ዘዳ. 14፥1፤ ዘሌ. 11፥24-25፤ 22፥3፤ ኤር. 16፥7።በኀዘኔም ጊዜ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም፤ ወይም ንጹህ ባልነበርኩ ጊዜ ያነሣሁትም ሆነ ለሙታን ያቀረብሁት መባ የለም፤ ለአምላኬ ጌታ ድምጽ ታዝዣለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ። 15#1ነገ. 8፥39፤43፤49፤ መዝ. 102፥19።ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ለአባቶቻችን በቃልህ እንደገባኸው መሓላ መሠረት ባርክ።’
ለእግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ
16 #
ዘዳ. 7፥6፤ 8፥6፤ 10፥12-13፤ 11፥22፤ 14፥2፤ 27፥9፤ 28፥1፤ 9፤ 29፥12-13፤ ዘፀ. 6፥7፤ 19፥5-6፤ 24፥7፤ ዘሌ. 26፥12፤ 2ሳሙ. 7፥24፤ ኤር. 7፥23፤ 31፥33፤ ሕዝ. 11፥20፤ ሆሴዕ 2፥23። “አምላክህ ጌታ ይህን ሥርዓትና ሕግ እንድትጠብቅ ዛሬ ያዝሃል፤ ስለዚህ አንተም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ለመፈጸም ተጠንቀቅ። 17ጌታ አምላክህ እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄድ፥ ሥርዓቱን፥ ትእዛዙንና ሕጉን እንደ ምትጠብቅና እንደምትታዘዝለት ተናግረሃል። 18ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፥ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ ዛሬ ተናግሮአል፤ 19ከፈጠራቸውም አሕዛብ ሁሉ በምስጋናና በስም፥ በክብር ከፍ እንደሚያደርግህና እርሱም እንደ ተናገረ ለጌታ እግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ አደረገህ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 26: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ