ኦሪት ዘፀአት 20
20
ዐሥሩ ትእዛዞች
1እግዚአብሔርም እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ 2“ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ።
3“ከእኔ በቀር#20፥3 ዕብራይስጡ ከእኔ በፊት ወይም በፊቴ ሌሎች አማልክት አይኑሩህ ይላል። ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። 4#ዘፀ. 34፥17፤ ዘሌ. 19፥4፤ 26፥1፤ ዘዳ. 4፥15-18፤ 27፥15።በላይ በሰማያት ካለው፥ በታች በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም አምሳል፥ የተቀረጸ ምስል ለአንተ አታድርግ። 5#ዘፀ. 34፥6፤7፤ ዘኍ. 14፥18፤ ዘዳ. 7፥9፤10።አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ 6ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ ነኝ።
7 #
ዘሌ. 19፥12። “የጌታ የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አያልፍም።
8 #
ዘፀ. 16፥23-30፤ 31፥12-14። “እንድትቀድሰው የሰንበትን ቀን አስታውስ። 9#ዘፀ. 23፥12፤ 31፥15፤ 34፥21፤ 35፥2፤ ዘሌ. 23፥3።ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፥ ተግባርህንም ሁሉ ፈጽም፤ 10ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህ፥ ሴት ልጅህ፥ ወንድ ሠራተኛህ፥ ሴት ሠራተኛህ፥ ከብትህ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ ሁሉ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤ 11#ዘፍ. 2፥1-3፤ ዘፀ. 31፥17።ጌታ በስድስት ቀናት ሰማያትንና ምድርን፥ ባሕርን፥ እና በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ ጌታ የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።
12 #
ዘዳ. 27፥16፤ ማቴ. 15፥4፤ 19፥19፤ ማር. 7፥10፤ 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ኤፌ. 6፥2፤ ኤፌ. 6፥3። “ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።
13 #
ዘፍ. 9፥6፤ ዘሌ. 24፥17፤ ማቴ. 5፥21፤ 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ሮሜ 13፥9፤ ያዕ. 2፥11። “አትግደል።
14 #
ዘሌ. 20፥10፤ ማቴ. 5፥27፤ 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ሮሜ 13፥9፤ ያዕ. 2፥11። “አታመንዝር።
15 #
ዘሌ. 19፥11፤ ማቴ. 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20፤ ሮሜ 13፥9። “አትስረቅ።
16 #
ዘፀ. 23፥1፤ ማቴ. 19፥18፤ ማር. 10፥19፤ ሉቃ. 18፥20። “በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
17 #
ሮሜ 7፥7፤ 13፥9። “የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፥ ወንድ ሠራተኛውን፥ ሴት ሠራተኛውን፥ በሬውን፥ አህያውን፥ የባልንጀራህ የሆነውን ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።”
18 #
ዕብ. 12፥18፤19። ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ፈሩ ተንቀጠቀጡም፥ ርቀውም ቆሙ። 19ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ ነገር ግን እንዳንሞት እግዚአብሔር አይናገረን።” 20ሙሴም ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ ሊፈትናችሁ፥ ኃጢአትንም እንዳትሠሩ እርሱን መፍራት በልባችሁ እንዲሆን እግዚአብሔር መጥቷልና።” 21ሙሴ እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ሲቀርብ ሕዝቡ ግን ርቀው ቆሙ።
ስለ መሠዊያው የተሰጠ ሕግ
22ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ ‘እኔ ከሰማይ ከእናንተ ጋር እንደተነጋገርሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። 23ከእኔ ጋር የብር አማልክትን አትሥሩ፥ የወርቅ አማልክትንም ለእናንተ አትሥሩ። 24ከአፈርም መሠዊያ ሥራልኝ፥ የሚቃጠለውንና የሰላም መሥዋዕትህን በጎችህንም በሬዎችህንም ሠዋበት፤ ስሜን በማሳስብበት ስፍራ ሁሉ ወደ አንተ መጥቼ እባርክሃለሁ። 25#ዘዳ. 27፥5-7፤ ኢያ. 8፥31።የድንጋይም መሠዊያ ብታደርግልኝ በተጠረበ ድንጋይ አትሥራው፤ በመሣሪያ ብትነካው ታረክሰዋለህና። 26ኃፍረተ ሥጋህ በእርሱ ላይ እንዳይገለጥ ወደ መሠዊያዬ በደረጃ አትውጣ።’”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 20: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ