ኦሪት ዘፀአት 21
21
ስለ ባርያዎች የተሰጠ ሕግ
1“በፊታቸው የምታኖረው ሥርዓት ይህ ነው። 2#ዘሌ. 25፥39-46።ዕብራዊ ባርያ የገዛህ እንደሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፥ በሰባተኛው ዓመት ግን እንዲሁ ነፃ ይውጣ። 3ብቻውን መጥቶ እንደሆነ ብቻውን ይውጣ ከሚስቱ ጋር መጥቶ እንደሆነ ሚስቱ ከእርሱ ጋር ትውጣ። 4ጌታው ሚስት ሰጥቶት ከሆነ እና ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆች ብትወልድለት፥ ሚስቱና ልጆችዋ ለጌታዋ ይሁኑ፥ እርሱ ብቻውን ይውጣ። 5ባርያውም፦ ጌታዬን፥ ሚስቴንና ልጆቼን እወድዳለሁ፥ ነፃ አልወጣም ብሎ ቢናገር፥ 6ጌታው ወደ እግዚአብሔር ያቅርበው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ያገልግለው።
7“አንድ ሰው ሴት ልጁን ለባርነት ቢሸጥ ወንድ ባርያዎች እንደሚወጡ አትውጣ። 8ጌታዋን ደስ ባታሰኘው እንድትዋጅ#21፥8 ሌላ ሰው እንዲገዛት ይስጣት። ይስጣት፤ በድሎአታልና ለባዕድ ሕዝብ ሊሸጣት መብት የለውም። 9ለልጁም ሊድራት ቢፈልግ፥ ለሴት ልጆች የሚገባውን ያድርግላት። 10ሌላይቱን ቢያገባ፥ ምግብዋን፥ ልብስዋንና የጋብቻ መብቷን አይቀንስባት። 11እነዚህንም ሦስት ነገሮች ባያደርግላት፥ ያለ ገንዘብ ትውጣ#21፥11 በነጻ ትውጣ።።
ስለ ዐመፅ የተሰጠ ሕግ
12 #
ዘሌ. 24፥17። “ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ ፈጽሞ ይሙት#21፥12 ዕብራይስጡ ቃል በቃል “ሞትን ይሙት” ይላል።። 13#ዘኍ. 35፥10-34፤ ዘዳ. 19፥1-13፤ ኢያ. 20፥1-9።ሳይሸምቅበት፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ድንገት በእጁ ቢጥለው፥ የሚሸሽበት ስፍራ እኔ አዘጋጅልሃለሁ። 14ሰው ግን ቢደፍር፥ ባልጀራውንም በተንኮል ቢገድለው፥ እንዲገደል ከመሠዊያዬ አውጥተህ ውሰደው። 15አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ፈጽሞ ይሙት። 16#ዘሌ. 20፥9፤ ማቴ. 15፥4፤ ማር. 7፥10።ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ ፈጽሞ ይሙት። 17#ዘዳ. 24፥7።አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ ፈጽሞ ይሙት።
18“ሰዎች ቢጣሉ፥ አንዱም ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፥ ባይሞት ነገር ግን በአልጋ ላይ ቢውል፥ 19ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ውጭ ቢወጣ፥ ሥራ ስላስፈታው ገንዘብ ከመክፈልና፥ እስኪፈወስም ድረስ ከማሳከም በቀር የመታው ሰው ከወንጀል ነጻ ነው። 20አንድ ሰው ወንድ ባርያውን ወይም ሴት ባርያውን በበትር ቢመታ፥ በእጁም ቢሞትበት፥ ያው ቅጣት ይቀጣ። 21ነገር ግን የተመታው አንድ ወይም ሁለት ቀን ቢቆይ ገንዘቡ ነውና አይቀጣ። 22ሰዎች ሲጣሉ፥ ያረገዘችን ሴት ቢመቱ ቢያስወርዳት ነገር ግን እርስ ባትጎዳ፥ የሴቲቱ ባል የጣለበትን ያህል ካሳ ይክፈል፤ ይህም በዳኞቹ ይሰጥ። 23ጉዳት ቢደርስባት ግን ሕይወት ስለ ሕይወት፥ 24#ዘሌ. 24፥19፤20፤ ዘዳ. 19፥21፤ ማቴ. 5፥38።ዐይን ስለ ዐይን፥ ጥርስ ሰለ ጥርስ፥ እጅ ስለ እጅ፥ እግር ስለ እግር፥ 25መቃጠል ስለ መቃጠል፥ ቁስል ስለ ቁስል፥ ግርፋት ስለ ግርፋት ይክፈል። 26አንድ ሰው የባርያውን ወይም የባርያይቱን ዐይን ቢመታ ቢያጠፋውም፥ ስለ ዓይኑ በነጻ ይልቀቀው። 27የባርያውን ወይም የባርያይቱን ጥርስ ቢያወልቅ፥ ስለ ጥርሱ ነጻ ይልቀቀው።
ስለ ንብረት የተሰጠ ትእዛዝ
28“በሬ ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ፥ በሬው ይወገር፥ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው። 29ነገር ግን በሬው አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ለባለቤቱ አስጠንቅቀውት ባይጠብቀውና ወንድን ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል። 30ካሳ እንዲከፍል ቢወሰንበት ግን፥ የነፍሱን ካሳ የወሰኑበትን ያህል ይስጥ። 31ወንድን ልጅ ቢወጋ ወይም ሴትን ልጅ ቢወጋ፥ ይህንኑ ፍርድ ያድርጉበት። 32በሬው ወንድ ባርያ ወይም ሴት ባርያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታው ይስጥ፥ በሬው ግን ይወገር። 33አንድ ሰው ጉድጓድ ቢከፍት፥ ወይም ጉድጓድ ቢቆፍር ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ቢወድቅበት፥ 34የጉድጓዱ ባለቤት ዋጋውን ለባለቤቱ ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን። 35የአንድ ሰው በሬ የሌላውን በሬ ቢወጋ፥ ቢሞትም፥ በሕይወት ያለውን በሬ ይሽጡ፥ ዋጋውንም እኩል ይካፈሉት፤ የሞተውንም ደግሞ እኩል ይካፈሉ። 36በሬው አስቀድሞ ተዋጊ መሆኑ ቢታወቅ፥ ባለቤቱም ባይጠብቀው፥ በሬውን በበሬው ፈንታ ይስጥ፥ የሞተውም ለእርሱ ይሁነው።
37“አንድ ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በበሬው ፈንታ አምስት በሬዎች፥ በበጉም ፈንታ አራት በጎች ይክፈል።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 21: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ