ኦሪት ዘፀአት 25
25
ለእግዚአብሔር ቤት የሚቀርብ መባ
1ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2“መባ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፤ በፈቃዱ ሊሰጠኝ ልቡ ከተነሣሣ ሰው ሁሉ መባዬን ተቀበሉ። 3ከእነርሱም የምትቀበሉት መባ ይህ ነው፦ ወርቅ፥ ብርና ናሐስ፥ 4ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታና የፍየል ጠጉር፥ 5ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአስቆጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፥ 6ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን የሚሆን ቅመም፥ 7መረግድ፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ። 8በመካከላቸው እንድኖር መቅደስ ይሥሩልኝ። 9እኔ እንዳሳየሁህ ሁሉ፥ እንደ ድንኳኑ ምሳሌ፥ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።
የቃል ኪዳኑ ታቦት
10“ከግራር እንጨት ታቦትን ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። 11ውስጡንና ውጪውም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በላዩ ላይ ዙሪያውን ሁሉ የወርቅ አክሊል አድርግለት። 12አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፥ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላው ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ። 13ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሥራ፥ በወርቅም ለብጣቸው። 14ታቦቱን በእነርሱ ለመሸከም በታቦቱ ጎን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አስገባ። 15መሎጊያዎቹ በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይኑሩ፥ ከዚያም አይውጡ። 16እኔ የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ አኑር። 17#ዕብ. 9፥5።ከንጹሕ ወርቅ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሥራ። 18ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፥ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። 19አንዱን ኪሩብ በአንድ በኩል፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው በኩል አኑር፥ በስርየት መክደኛው ላይ ኪሩቤል በሁለት በኩል ላይ ታደርጋቸዋለህ። 20ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፥ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይመለከታሉ። 21የስርየት መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ እኔ የምሰጥህንም ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። 22በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች እንድታዝዝ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።
ለፊቱ ኅብስት የሚሆን ገበታ
23“ርዝመቱ ሁለት ክንድ፥ ወርዱ አንድ ክንድ፥ ቁመቱ አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ገበታ ከግራር እንጨት ሥራ። 24በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት፤ 25በዙሪያውም አንድ ጋት የሚያህል ክፈፍ አድርግለት፤ የወርቅም አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አድርግለት። 26አራት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮቹ ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች ላይ አድርጋቸው። 27ገበታውንም ለመሸከም መሎጊያዎቹ እንዲሰኩባቸው ቀለበቶቹ በክፈፉ አቅራቢያ ይሁኑ። 28ገበታውን እንዲሸከሙባቸው መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። 29ለማፍሰሻም እንዲሆኑ ወጭቶችዋን ጭልፋዎችዋንም መቅጃዎችዋንም ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው። 30#ዘሌ. 24፥5-8።በገበታው ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።
መቅረዙ
31“ከንጹሕ ወርቅ መቅረዝ ሥራ፤ መቅረዙ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ እግሩና ከአገዳው ጋር ጽዋዎቹም ጉብጉቦቹም አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት። 32በስተጎኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፤ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ። 33በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች አድርግ፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አድርግ። 34በመቅረዙም እንቡጥና ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ አራት ጽዋዎች ይኑሩት። 35ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ እንቡጥ፥ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ እንቡጥ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ እንቡጥ ይሁን። 36እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ከእርሱ ይሁኑ፤ ሁሉም ወጥ ሆኖ ከተቀጠቀጠ ከንጹሕ ወርቅ ይሠሩ። 37ሰባቱንም መብራቶች ሥራ፤ በፊት ለፊት እንዲያበሩ መብራቶቹን ከፍ አድርገህ አስቀምጣቸው። 38መኮስተሪያዎችዋንና የኩስታሪ ማስቀመጫዎችዋን ከንጹሕ ወርቅ ሥራ። 39እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ይሠሩ። 40#የሐዋ. 7፥44፤ ዕብ. 8፥5።በተራራው ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ለመስራት ጥንቃቄ አድርግ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 25: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ