ኦሪት ዘፀአት 27
27
የመሠዊያው አሠራር
1“ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር እንጨት ሥራ፤ መሠዊያው አራት ማዕዘን ይሁን፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ይሁን። 2በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አድርግለት፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ፤ በነሐስም ለብጠው። 3አመድ የሚጠራቀምባቸውን ምንቸቶች፥ መጫሪያዎቹን፥ ድስቶቹን፥ ሜንጦቹንና ማንደጃዎቹን ታደርጋለህ፤ ዕቃዎቹ ሁሉ ከነሐስ ሥራ። 4እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የነሐስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የነሐስ ቀለበት በአራቱም ማዕዘን አድርግለት። 5መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ እንዲደርስ ከመሠዊያው እርከን በታች አድርገው። 6ለመሠዊያው ከግራር እንጨት መሎጊያዎችን ሥራ፥ በነሐስም ለብጣቸው። 7መሎጊያዎቹ በቀለበቶቹ ውስጥ ይግቡ፥ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎቹ በሁለቱ ጎኖች ይሁኑ። 8ከሳንቃዎች ሠርተህ ባዶ አድርገው፤ በተራራው እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንዲሁ ይሥሩት።
አደባባዩና መጋረጃዎቹ
9“የማደሪያውን አደባባይ ሥራ፤ በደቡብ በኩል ከጥሩ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ይሁኑ፥ የአንዱ ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤ 10ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ። 11እንዲሁም በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከነሐስ የተሠሩ ሀያ ምሰሶዎች እና ሀያ እግሮች ይሁኑ፥ ለምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። 12በምዕራብ በኩል ላለው ለአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር እግሮች ይሁኑ። 13በምሥራቅ በኩል ያለው የአደባባዩ ስፋት አምሳ ክንድ ይሁን። 14በአንድ በኩል ያለው የመጋረጃዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ፥ ምሰሶዎቹ ሦስት፥ እግሮቹ ሦስት ይሁን። 15በሌላውም በኩል የመጋረዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ፥ ምሰሶዎቹ ሦስት፥ እግሮቹም ሦስት ይሁን። 16ለአደባባዩም መግቢያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ የተጠለፈ ሀያ ክንድ መጋረጃ ይሁን፤ ምሰሶዎቹ አራት፥ እግሮቹም አራት ይሁኑ። 17በአደባባዩም ዙሪያ ያሉት ምሰሶዎች ሁሉ በብር ይያያዙ፥ ኩላቦቻቸው ከብር እግሮቻቸው ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። 18የአደባባዩ ርዝመት መቶ ክንድ፥ ስፋቱ አምሳ ክንድ ይሁን፥ ከፍታው አምስት ክንድ ይሁን፥ መጋረጃውም ከጥሩ በፍታ፥ እግሮቹም ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ። 19ለአገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የማደሪያው ዕቃ ሁሉ፥ ካስማዎቹ ሁሉ የአደባባዩም ካስማዎች ሁሉ፥ የነሐስ ይሁኑ።
የመብራቱ ዘይት
20“መብራቱ ሁልጊዜ እንዲበራ ለመብራት የሚሆን ተጨምቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ የእስራኤልን ልጆች እዘዛቸው። 21ከመጋረጃው ውጭ ባለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ታቦት ፊት አሮንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በጌታ ፊት ያሰናዱት፤ በእስራኤል ልጆች ዘንድ በትውልዳቸው የዘለዓለም ሥርዓት ይሁን።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 27: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ