ኦሪት ዘፀአት 28
28
የክህነት ልብስ አሠራር
1ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይተህ ካህናት እንዲሆኑልኝ ወደ አንተ አቅርብ፤ አሮንን የአሮንንም ልጆች፥ ናዳብን፥ አቢሁን፥ አልዓዛርንና ኢታማርን አቅርብ። 2ለክብርና ለውበት እንዲሆን ለወንድምህ ለአሮን የተቀደሰ ልብስ ሥራለት። 3ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ የተለየ እንዲሆን ለአሮን ልብስ እንዲሠሩለት የጥበብ መንፈስ ለሞላሁባቸው በልባቸው ጥበበኞች ለሆኑት ሁሉ ተናገር። 4የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ፥ ኤፉድ፥ ቀሚስ፥ የተጠለፈ እጀ ጠባብ፥ መጠምጠሚያና መታጠቂያ፤ ካህን እንዲሆንልኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ የተቀደሰ ልብስ ይሥሩላቸው። 5ወርቅ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይም ግምጃና ጥሩ በፍታም ይውሰዱ።
ኤፉዱ
6“ኤፉዱንም በወርቅ፥ በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም በብልሃት የተሠራ ይሁን። 7ሁለቱ ወገን አንድ ሆኖ እንዲጋጠም በሁለቱ ትከሻ ላይ የሚጋጠም ይሁን። 8በላዩ ያለው በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ መታጠቂያ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ ይሁን። 9ሁለት የመረግድ ድንጋይ ወስደህ የእስራኤልን ልጆች ስም ቅረጽባቸው፤ 10እንደ የልደታቸው ቅደም ተከተል ስድስት ስም በአንድ ድንጋይ ላይ፥ የቀረውንም ስድስቱን ስም በሌላኛው ድንጋይ ቅረጽ። 11በቅርጽ ሠራተኛ ሥራ እንደ ማኅተም ቅርጽ አድርገህ የእስራኤልን ልጆች ስም በሁለት ድንጋዮች ቅረጽ በወርቅ ፈርጥ ሥራቸው። 12የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች እንዲሆኑ ሁለቱን ዕንቁዎች በኤፉዱ ትከሻዎች ላይ ታደርጋለህ፤ አሮንም በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ ለመታሰቢያ እንዲሆን ስማቸውን በጌታ ፊት ይሸከማል። 13ፈርጦችን ከወርቅ ሥራ፤ 14እንደ ተጎነጎነ ገመድ አድርገህ ሁለት ድሪዎች ከንጹሕ ወርቅ ሥራ፤ የተጎነጎኑትንም ድሪዎች ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው።
የደረት ኪስ አሠራር
15“የፍርዱን የደረት ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራው ሥራው፤ እንደ ኤፉዱ አሠራር ሥራው፤ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ ሥራው። 16ርዝመቱ ስንዝር ስፋቱም ስንዝር ሆኖ አራት መዕዘንና ድርብ ይሁን። 17አራት ረድፍ የሆነ የዕንቁ ፈርጥ አድርግበት፤ በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮንና የሚያብረቀርቅ ዕንቁ፤ 18በሁለተኛው ረድፍ በሉር፥ ሰንፔርና አልማዝ፤ 19በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፥ ኬልቄዶን፥ አሜቴስጦኖስ፤ 20በአራተኛው ረድፍ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፤ በወርቅ ፈርጥ ይቀመጣሉ። 21የዕንቁ ድንጋዮች እንደ እስራኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆናሉ፤ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ማኅተም እንደሚቀረጽ በየስማቸው ይቀረጹ። 22ለደረት ኪሱም የተጎነጎኑትን ድሪዎች እንደ ገመድ አድርገህ ከንጹሕ ወርቅ ሥራቸው። 23ለደረት ኪሱም ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራ፥ ሁለቱንም ቀለበቶች በደረት ኪሱ በሁለቱ ጫፎች አድርጋቸው። 24ሁለቱ የተጎነጎኑ የወርቅ ድሪዎችን በደረቱ ኪስ ጫፎች ወዳሉት ወደ ሁለቱ ቀለበቶች ታስገባቸዋለህ። 25የሁለቱን ድሪዎች ጫፎች በሁለቱ ፈርጦች ውስጥ አግብተህ በኤፉዱ ትከሻ በፊት ለፊት ታደርጋቸዋለህ። 26ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ በኤፉዱ ፊት ለፊት ባለው በደረት ኪሱ በሁለቱ ጫፎች ላይ ታደርጋቸዋለህ። 27በተጨማሪም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ በኤፉዱም ፊት ለፊት ከትከሻዎቹ በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ በመያዣው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ። 28የደረት ኪሱም በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ በላይ እንዲሆን ከኤፉዱም እንዳይለይ፥ የደረት ኪሱን ከቀለበቶቹ ወደ ኤፉዱ ቀለበቶች በሰማያዊ ፈትል ያያይዙታል። 29አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ ዘወትር መታሰቢያ እንዲሆን በጌታ ፊት የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ ደረት ኪስ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም። 30#ዘኍ. 27፥21፤ ዘዳ. 33፥8፤ ዕዝ. 2፥63፤ ነህ. 7፥65።በፍርዱ በደረት ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፥ በጌታ ፊት በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በጌታ ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።
ሌሎች የክህነት ልብሶች
31“የኤፉዱን መደረቢያ ሙሉ ሰማያዊ አድርገው። 32መሃሉ ላይ ራስ ማስገቢያ አንገትጌ ይኑረው፤ እንዳይቀደድም የአንገትጌው ዙሪያ የተጠለፈ ይሁን። 33#ሲራ. 45፥9።በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃ ሮማኖች አድርግ፤ በዚያም መካከል በዙሪያው የወርቅ ሻኩራዎች አድርግ፤ 34የወርቅ ሻኩራና ሮማን፥ የወርቅ ሻኩራና ሮማን በቀሚሱ ዘርፍ ዙሪያውን ይሆናሉ። 35በአገልግሎት ጊዜ በአሮን ላይ ይሆናል፤ እርሱም እንዳይሞት ወደ መቅደሱ በጌታ ፊት ሲገባና ሲወጣ ድምፁ ይሰማል። 36ከንጹህ ወርቅ ቅጠል ሥራ፥ በእርሱም ላይ እንደ ማኅተም ቅርጽ ‘ለጌታ የተቀደሰ’ የሚል ቅረጽበት። 37በመጠምጠሚያው ፊት በሰማያዊ ፈትል በመጠምጠሚያው ላይ ስፋው። 38በአሮን ግምባር ላይ ይሆናል፥ አሮንም የእስራኤል ልጆች በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱስ ስጦታቸው ሁሉ ላይ ያለውን ኃጢአት ይሸከም፤ በጌታ ፊት ሞገስ እንዲሆንላቸው ቅጠሉ ሁልጊዜ በግምባሩ ላይ ይሁን። 39እጀ ጠባቡን ከጥሩ በፍታ፥ መጠምጠሚያውን ከበፍታ ትሠራለህ፥ በጥልፍ የተጠለፈ መታጠቂያ ትሠራለህ። 40ለአሮን ልጆች እጀ ጠባቦችን፥ መታጠቂያዎችንና ቆቦችን ለክብርና ለጌጥ ትሠራላቸዋለህ። 41ወንድምህን አሮንንና ከእርሱም ጋር ልጆቹን እነዚህን#28፥41 ልብሶቹን ለማመልከት ነው። አልብሳቸው፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፥ እጆቻቸውንም ታነጻለህ፥ ትቀድሳቸዋለህም። 42ኀፍረተ ሥጋቸውን እንዲሸፍኑበት ከወገባቸው እስከ ጭናቸው የሚደርስ የበፍታ ሱሪ ታደርግላቸዋለህ፤ 43ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 28: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ