ኦሪት ዘፀአት 30
30
የዕጣን መሠዊያ
1የዕጣን መሠዊያ ሥራ፤ ከግራር እንጨት አድርገው። 2ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ ይሁን፥ አራት ማዕዘን ይሁን፤ ቁመቱ ሁለት ክንድ ይሁን፤ ቀንዶቹ ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ። 3ላዩን፥ የጎኖቹን ዙሪያ ሁሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ ዙሪያው የወርቅ አክሊል ታደርግለታለህ። 4ከአክሊሉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ በእነርሱ እንዲሸከሙም የመሎጊያዎቹ ማስገቢያ ይሁኑ። 5መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው። 6በምስክሩ ታቦት አጠገብ ካለው መጋረጃ ፊት ታኖረዋለህ፥ ለአንተ በምገለጥበት ከምስክሩ በላይ ባለው በስርየት መክደኛ ፊት ታኖረዋለህ። 7አሮንም መልካም መዓዛ ያለው እጣን ማለዳ ማለዳ ይጠንበት፤ መብራቶቹን ሲያዘጋጅ ይጠነው። 8አሮን በማታ ጊዜ መብራቶቹን ሲያበራ ይጠነው፥ ይህንም በትውልዳችሁ ሁሉ በጌታ ፊት ዘወትር የሚቀርብ ዕጣን ነው። 9በእርሱ ላይ ያልተገባ ዕጣን፥ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል ቁርባን አታቀርብበትም፤ የመጠጥ ቁርባንም አታፈስስበትም። 10አሮን በዓመት አንድ ጊዜ በቀንዶቹ ላይ ማስተስረያ ያደርጋል፤ በዓመት አንድ ጊዜ ለትውልዳችሁ ማስተስረያ በሚሆን በኃጢአት መሥዋዕት ደም ማስተስረያ ያደርግበታል። ለጌታ እጅግ የተቀደሰ ነው።
የቤዛነት ክፍያ
11ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 12“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ በቆጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቆጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ። 13#ዘፀ. 38፥25፤26፤ ማቴ. 17፥24።በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው። 14በዚህ ቆጠራ የሚያልፍ፥ ሃያ ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሁሉ፥ ይህንን ስጦታ ለጌታ ይስጥ። 15ለነፍሳችሁ ማስተስረያ የጌታን ስጦታ ስትሰጡ፥ ከግማሽ ሰቅሉ ባለ ጠጋው አይጨምር፥ ደሃውም አያጉድል። 16የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤል ልጆች ወስደህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስጠው፤ ለእስራኤል ልጆች ለነፍሳችሁ ቤዛ እንዲሆን በጌታ ፊት መታሰቢያ ይሆናል።”
ከነሐስ የተሠራ ሳሕን
17ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 18#ዘፀ. 38፥8።“የመታጠቢያ ሳሕንና መቀመጫውን ከነሐስ ሥራ፤ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል ታኖረዋለህ፥ ውኃም ትጨምርበታለህ። 19አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በእርሱ ይታጠባሉ። 20ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም ለጌታ የእሳት መሥዋዕት ሊያቃጥሉ ወደ መሠዊያው ለማገልገል በሚቀርቡበት ጊዜ እንዳይሞቱ በውኃ ይታጠቡ። 21እንዳይሞቱ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠቡ፤ ይህም ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆንላቸዋል።”
የቅባት ዘይትና ዕጣን
22 #
ዘፀ. 37፥29። ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ 23“ምርጥ የሆኑትን ቅመሞች ለራስህ ውሰድ፤ ፈሳሽ ከርቤ አምስት መቶ ሰቅል፥ ግማሽ ይኸውም ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል የቀረፋ ቅመም፥ የጠጅ ሣርም እንዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፥ 24ብርጉድ አምስት መቶ ሰቅል በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ አንድ የኢን መሥፈሪያ የወይራ ዘይት፥ 25በቀማሚ እንደሚቀመም ቅመም የተቀደሰ የቅባት ዘይት ታደርገዋለህ፤ የተቀደሰ የቅባት ዘይትም ይሆናል። 26የመገናኛውን ድንኳንና የምስክሩን ታቦት በእርሱ ትቀባለህ፥ 27ገበታውንና ዕቃውን ሁሉ፥ መቅረዙንና ዕቃውን፥ የዕጣን መሠዊያውን፥ 28የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕኑንና ማስቀመጫውን ትቀባለህ። 29ቀድሳቸው ፍጹም የተቀደሱ ይሆናሉ፤ የሚነካቸውም ሁሉ ቅዱስ ይሆናል። 30አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፥ ካህነት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ቀድሳቸው። 31የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ለእኔ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ነው። 32በሰው ሥጋ ላይ አይፍሰስ፤ እንደ እርሱ የተሠራ ሌላ ቅባት አትስሩ፤ ቅዱስ ነው፥ ለእናንተም ቅዱስ ይሁን። 33እንደ እርሱ ዓይነት የሚቀምም ሰው ወይም ከእርሱ በሌላው ላይ የሚያፈስስ ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።’” 34ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “መልካም መዓዛ ያለው ቅመም፥ የሚንጠባጠብ ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ንጹሕ እጣን ለራስህ ውሰድ፥ ሁሉም እኩል መጠን ይኑራቸው፤ 35ቀማሚ እንደሚቀምመው፥ በጨው የተቀመመ፥ ንጹሕና ቅዱስ አድርገህ ዕጣን አዘጋጅ። 36ከእርሱም ጥቂት ትወቅጣለህ፥ ታደቀዋለህም፥ ከእርሱም ወስደህ አንተን በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በምስክሩ ፊት ታኖረዋለህ። ለእናንተም ፍጹም ቅዱስ ይሆንላችኋል። 37የሠራኸውን ዓይነት ዕጣን ለራሳችሁ አታድርጉ፤ በእናንተ ዘንድ ለጌታ የተቀደሰ ይሁን። 38ለሽቶነት ፈልጎ እንደ እርሱ የሚሠራ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 30: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ