ኦሪት ዘፀአት 31
31
ባስልኤልና ኤልያብ
1ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 2“እይ! ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሑር ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠርቼዋለሁ። 3በጥበብ፥ በማስተዋል፥ በእውቀትና ሥራ ሁሉ እንዲሠራ የእዚአብሔርን መንፈስ ሞላሁበት፥ 4ልዩ ማስተዋል እንዲኖረው፥ በወርቅ፥ በብርና በነሐስ እንዲሠራ፥ 5ለፈርጥ የሚሆነውን ድንጋይ እንዲቀርጽ፥ እንጨት እንዲጠርብ፥ ሁሉንም ሥራ እንዲሠራ ሞላሁበት። 6እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሆነውን የአሒሳማክን ልጅ ኤልያብን#31፥6 ዕብራይስጡ አሆሊኣብ ይለዋል። ሰጥቼዋለሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ እንዲያደርጉ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ላይ ጥበብን አኑሬአለሁ። 7የመገናኛውን ድንኳን፥ የምስክሩን ታቦት፥ በእርሱም ላይ ያለውን የስርየት መክደኛውን፥ የድንኳኑን ዕቃ በሙሉ፥ 8ገበታውና ዕቃው ሁሉ፥ ንጹሑን መቅረዝና ዕቃውን፥ የዕጣን መሠዊያውን፥ 9የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያ ሳሕንና መቀመጫውን፥ 10በብልሃት የተሠራውን ልብስ፥ በክህነት እኔን የሚያገለግሉበትን የካህኑ የአሮን የተቀደሱ ልብሶች የልጆቹ ልብሶች፥ 11የቅባቱን ዘይት፥ ለመቅደሱ የሚሆን መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን እንዳዘዝሁህ ሁሉ እንዲሁ ያድርጉ።”
የሰንበት ሕግ
12ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ 13“አንተ ግን ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ፥ ይህ የምቀድሳችሁ ጌታ እኔ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ለትውልዶቻችሁ ምልክት ነውና። 14ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ፤ የሚያረክሰው ፈጽሞ ይገደል፥ በእርሷ ሥራን የሚሠራ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። 15#ዘፀ. 20፥8-11፤ 23፥12፤ 34፥21፤ 35፥2፤ ዘሌ. 23፥3፤ ዘዳ. 5፥12-14።ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል። 16የእስራኤል ልጆች ሰንበትን ይጠብቁ፤ ሰንበትን መጠበቅ ለትውልዳቸው የዘለዓለም ቃል ኪዳን ያድርጉት። 17#ዘፀ. 20፥11።በእኔና በእስራኤል ልጆች መካከል የዘለዓለም ምልክት ነው፤ ጌታ ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ፈጥሮአልና፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው አርፎአልና፥ ተነቃቅቶአልና።’”
ሁለቱ የኪዳን ጽላቶች
18በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች የሆኑ ሁለት የምስክር ጽላቶችን ሰጠው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 31: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ