ኦሪት ዘፀአት 35
35
የሰንበት አከባበር ሥርዓት
1ሙሴ የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ እንድትፈጽሙት ያዘዘው ቃል ይህ ነው፤ 2#ዘፀ. 20፥8-11፤ 23፥12፤ 31፥15፤ 34፥21፤ ዘሌ. 23፥3፤ ዘዳ. 5፥12-14።ስድስት ቀን ሥራህን ትሠራለህ፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ የዕረፍት፥ ለእናንተ የተቀደሰ ሰንበት አለለችሁ፥ በዚህ ቀን የሚሠራበትም ሁሉ ይገደል። 3በሰንበት ቀን በመኖሪያዎቻችሁ ሁሉ እሳትን አታንድዱ።”
ድንኳኑን ለመሥራት የሚያስፈልግ ዝግጅት
4ሙሴ ለእስራኤል ልጆች ማህበር ሁሉ እንዲህ አለ፦ “ጌታ ያዘዘው ነገር ይህ ነው፥ እንዲህ በማለት፥ 5ለጌታ ከእናንተ ዘንድ መባን አቅርቡ፤ የልብ መነሣሣት ያለው ሁሉ ለጌታ መባ ያምጣ፤ ወርቅ፥ ብር፥ ነሐስ፥ 6ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥ 7ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት፥ የግራር እንጨት፤ 8ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን የሚሆን ቅመም፥ 9መረግድ፥ ለኤፉድና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ ያምጣ።
10“በእናንተ መካከል ያሉ በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ መጥተው ጌታ ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ። 11ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቃዎቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፤ 12ታቦቱንና መሎጊያዎቹን፥ የስርየት መክደኛውን፥ መሸፈኛ መጋረጃ፥ 13ገበታውና መሎጊያዎቹን፥ ዕቃውንም ሁሉ፥ ኅብስተ ገጹን፥ 14መብራት የሚያበሩበትን መቅረዝና ዕቃውን፥ ቀንዲሉን፥ የመብራቱን ዘይት፤ 15የዕጣኑን መሠዊያና መሎጊያዎቹን፥ የቅባቱን ዘይት፥ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን፥ የድንኳኑን ደጃፍ መጋረጃ፤ 16የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያና የነሐሱን መከታ፥ መሎጊያዎቹንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሳሕንና ማስቀመጫውን፤ 17የአደባባዩን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቹንና እግሮቻቸውን፥ የአደባባዩን ደጃፍ መጋረጃ፤ 18የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩን ካስማዎችና አውታሮቻቸውን፤ 19በመቅደስ ውስጥ ለማገልገል በብልሃት የተሠሩትን ልብሶች፥ በክህነት እንዲያገለግሉበት የተቀደሱትን የካህኑን የአሮን ልብሶችና የልጆቹን ልብሶች።”
ለድንኳኑ መሥሪያ የመጣ ስጦታ
20የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጡ። 21ልቡ ያነሣሣውና መንፈሱ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ሰው ሁሉ ለመገናኛው ድንኳን ሥራና ለአገልግሎቱ ሁሉ ለተቀደሰውም ልብስ የሚሆን ለጌታ ስጦታ አመጡ። 22ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ። 23ሰማያዊ፥ ሐምራዊ፥ ቀይ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታ፥ የፍየል ጠጉር፥ ቀይ የአውራ በግ ቁርበት፥ የአቆስጣ ቁርበት ያላቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ። 24የብርና የነሐስ ስጦታ መስጠት የሚችል ሁሉ ለጌታ ስጦታ አቀረበ፤ የግራር እንጨት ያለው ሁሉ ለማንኛውም ሥራ አገልግሎት እንዲውል አመጣ። 25በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶች ሁሉ በእጃቸው ፈተሉ፥ የፈተሉትንም ሰማያዊውን፥ ሐምራዊውን፥ ቀይ ግምጃውንና ጥሩውን በፍታ አመጡ። 26ልባቸው በጥበብ ያነሣሣቸው ሴቶች ሁሉ የፍየልን ጠጉር ፈተሉ። 27አለቆችም የመረግድ ድንጋይ፥ በኤፉድና በደረት ኪስ የሚገቡ ፈርጦችን፥ 28ቅመማቅመም፥ ለመብራት የሚሆን ዘይት፥ ለቅባት የሚሆን ዘይት፥ ለጣፋጭ ሽታ ዕጣንን አመጡ። 29ከእስራኤል ልጆች ልባቸው ያነሣሣቸው ወንዶችና ሴቶች ሁሉ ጌታ በሙሴ እጅ እንዲሠራ ላዘዘው ሥራ ሁሉ የሚሆን ስጦታ በፈቃዳቸው ለጌታ አመጡ።
ባስልኤልና ኤልያብ
30ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ አላቸው፦ “ተመልከቱ፥ ጌታ ከይሁዳ ነገድ የሆነውን የሑር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠራው። 31በእግዚአብሔር መንፈስ፥ በጥበብ፥ በማስተዋል፥ በእውቀት በሥራ ሁሉ ብልሃት ሞላው፤ 32በወርቅ፥ በብርና በነሐስ በጥበብ እንዲሠራ፥ 33ፈርጥ የሚሆንን የዕንቁ ድንጋይ በመቅረጽ፥ እንጨት በመጥረብ፥ የብልሃት ሥራ ሁሉ እንዲሠራ ችሎታ ሰጠው። 34እርሱና የዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ ኤልያብ እንዲያስተምሩ በልባቸው አሳደረባቸው። 35በአንጥረኝነት፥ በንድፍ፥ በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ በመጥለፍ፥ ሸማኔ በሚሠራው ሥራ፥ በማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ እንዲያደርጉ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 35: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ