ኦሪት ዘፀአት 37
37
የቃል ኪዳኑ ታቦት አሠራር
1ባስልኤል ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 2ውስጡንና ውጪውን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገለት። 3በአራቱ እግሮቹ ላይ አራት የወርቅ ቀለበቶችን አደረገለት፤ በአንድ በኩል ሁለት ቀለበቶችን፥ በሌላው በኩል ሁለት ቀለበቶች ሆኑ። 4መሎጊያዎችን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 5ታቦቱንም ለመሸከም በታቦቱ ጎንና ጎን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አስገባ። 6ከንጹሕ ወርቅ የስርየት መክደኛ ሠራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር። 7ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሁለት ኪሩቤል ሠራ፤ በስርየት መክደኛው ላይ በሁለቱ ጫፎች አደረጋቸው። 8አንዱን ኪሩብ በዚህኛው በኩል፥ አንዱን ኪሩብ በዚያኛው በኩል አደረጋቸው፥ በሁለቱ ጫፎች ከስርየት መክደኛው ሠራቸው። 9ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ የዘረጉ ነበሩ፥ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ሸፈኑ፥ እርስ በርሳቸውም ትይዩ ነበሩ፥ የኪሩቤል ፊቶቻቸው ወደ መክደኛው ይመለከት ነበር።
ለፊቱ ሕብስት የሚሆን ገበታ አሠራር
10ርዝመቱ ሁለት ክንድ፥ ወርዱ አንድ ክንድ፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ገበታ ከግራር እንጨት ሠራ። 11በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፥ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገለት። 12በዙሪያው አንድ ስንዝር የሚያህል ክፈፍ አደረገለት፤ የወርቅ አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አደረገለት። 13አራት የወርቅ ቀለበቶችን አደረገለት፤ ቀለበቶቹንም አራቱ እግሮች ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች አደረገ። 14ገበታውንም ለመሸከም መሎጊያዎቹ እንዲሰኩባቸው ቀለበቶች በክፈፉ አጠገብ ነበሩ። 15ገበታውን እንዲሸከሙባቸው መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው። 16በገበታው ላይ የሚኖሩትን ዕቃዎች፥ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎችን፥ ጽዋዎችንና ለማፍሰሻ የሚሆኑ መቅጃዎችን፥ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
የመቅረዙ አሠራር
17መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ። 18በጎኑም ስድስት ቅርንጫፎች ወጡለት፤ ሦስቱ የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ በኩል፥ ሦስቱም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ በኩል። 19በአንደኛው ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ እንቡጥ፥ ቀንበጥ ያለው የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች፥ እንዲሁም ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች አደረገ። 20በመቅረዙም ጉብጉቦቹንና አበቦቹን አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች አደረገ። 21ከመቅረዙ ለወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ፥ ከሁለትም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጉብጉብ ነበረ። 22ጉብጉቦቹና ቅርንጫፎቹ ከእርሱ ጋር አንድ ነበሩ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠርቶ ነበር። 23ሰባቱን መብራቶቹን፥ መኰስተሪያዎቹንና የኩስታሪ ማድረጊያዎቹን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ። 24መቅረዙንና ዕቃዎቹን ሁሉ ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠራ።
የዕጣን መሠዊያው አሠራር
25የዕጣን መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ ርዝመቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ፥ አራት ማዕዘን ነበረ፤ ከፍታውም ሁለት ክንድ ነበረ፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ። 26ላዩን፥ የጎኑን ዙሪያ በሙሉና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አደረገበት። 27ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አደረገበት፥ በሁለቱም ጎን በሁለቱም ማዕዘን አደረጋቸው፥ ለመሸከምም የመሎጊያዎቹ ስፍራ ነበሩ። 28መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠራ፥ በወርቅም ለበጣቸው።
የቅባቱ ዘይትና የዕጣኑ አዘገጃጀት
29 #
ዘፀ. 30፥22-38። የተቀደሰ የቅባት ዘይት፥ ንጹሕና መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን ቀማሚ እንደሚሠራው አደረገ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 37: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ