ኦሪት ዘፀአት 38
38
የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ አሠራር
1የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ እርሱም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ ነበር፥ አራት ማዕዘንም ነበረ፥ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ። 2በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አደረገበት፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ በነሐስም ለበጠው። 3የመሠዊያውን ዕቃዎች በሙሉ፥ ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹን፥ ሜንጦቹን፥ ማንደጃዎቹን ሠራ፤ ዕቃዎቹን በሙሉ ከነሐስ ሠራ። 4ለመሠዊያውም መረብ የሚመስል የነሐስ መከታ ከጠርዙ በታች እስከ መሠዊያው ግማሽ ድረስ ሠራለት። 5ለነሐሱ መከታ አራቱ ማዕዘኖች ለመሎጊያዎቹ ማስገቢያ እንዲሆኑ አራት ቀለበቶችን አደረገ። 6መሎጊያዎቹን ከግራር እንጨት ሠራ፥ በነሐስም ለበጣቸው። 7እንዲሸከሙትም መሎጊያዎቹን በመሠዊያው ጎን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ ክፍትም አድርጎ ከሳንቃዎች ሠራው።
8 #
ዘፀ. 30፥18። የነሐሱ የመታጠቢያ ሳሕንና የነሐሱ ማስቀመጫውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች መስተዋት ሠራ።
የድንኳኑ አደባባይ አሠራር
9አደባባዩንም ሠራ፤ በደቡብ በኩል የአደባባዩ መጋረጃዎች ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ፥ ከጥሩ በፍታ የተፈተለ ነበር። 10ምሰሶዎቻቸው ሃያ፥ የነሐስ እግሮቻቸውም ሃያ ነበሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። 11በሰሜን በኩል መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸውን መጋረጃዎች፥ ምሰሶዎቻቸው ሃያ የነሐስ እግሮቻቸውም ሃያ ነበሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። 12በምዕራብ በኩል አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ነበሩ፤ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር የነሐስ እግሮች ነበሩት፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሰሩ ነበሩ። 13በምሥራቅም በኩል አምሳ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች#38፥13 በዕብራይስጡ መጋረጃዎች የሚለው ቃል የለም። ነበሩ። 14በአንድ በኩል የመጋረጃዎቹ ርዝመት ዐሥራ አምስት ክንድ ነበረ፥ ሦስት ምሰሶዎች እና ሦስት እግሮች ነበሩ። 15በሁለተኛው በኩል በአደባባዩ መግቢያ በዚህና በዚያ ዐሥራ አምስት ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ሦስት ምሰሶዎች እና ሦስት እግሮች ነበሩ። 16በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች በሙሉ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ ነበሩ። 17የምሰሶዎቹ እግሮች ከነሐስ የተሠሩ፥ የምሰሶዎቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ የምሰሶዎቹ ጉልላቶች በብር ተለብጠው ነበር፤ በአደባባዩ ያሉ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሩአቸው። 18የአደባባዩ መግቢያ መጋረጃ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከጥሩ በፍታ የተጠለፈ ነበረ፤ ርዝመቱ ሀያ ክንድ፥ ቁመቱ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች አምስት ክንድ ነበረ፤ 19ምሰሶዎቹ አራት ነበሩ፤ ከነሐስ የተሠሩ እግሮች አራት፥ ኩላቦቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ፥ ጉልላቶቻቸውና ዘንጎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር። 20የማደሪያውና በዙሪያው ያለ የአደባባዩ ካስማዎች ሁሉ ከነሐስ የተሠሩ ነበሩ።
ለድንኳኑ አገልግሎት የሚሆኑ ዕቃዎች
21በሙሴ ትእዛዝ መሠረት የሌዋውያን አገልግሎት ሊሆን በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር እጅ የተቆጠረው የማደሪያው፥ የምስክሩ ማደሪያ፥ ዕቃ ድምር ይህ ነው። 22ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሑር ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል ጌታ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። 23ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም ቀራጭ፥ ንድፍ አውጪ፥ እንዲሁም በሰማያዊ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ የሚጠልፍ ነበረ።
24ለመቅደሱ ሥራ የተደረገው ወርቅ ሁሉ፥ የተሰጠው ወርቅ በሙሉ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ሀያ ዘጠኝ መክሊት ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ። 25#ዘፀ. 30፥11-16።ከተቆጠረው ማኅበር የተገኘው ብር፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት መቶ መክሊትና አንድ ሺህ ሰባት መቶ ከሰባ አምስት ሰቅል ነበረ። 26#ማቴ. 17፥24።በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ የሰቅል ግማሽ ከተቆጠረው ከእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ነው፤ ይህም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያ በላይ የተቆጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበሩ። 27መቶው የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶ መክሊት መቶ እግሮች ተሠሩ ይኸውም ለአንድ እግር አንድ መክሊት ማለት ነው። 28ከሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሰቅል የምሰሶዎቹን ኩላቦችና ዘንጎች ሠራ፥ የምሰሶዎቹንም ጉልላቶች ለበጠ። 29የተሰጠውም ነሐስ ሰባ መክሊትና ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ። 30ከእርሱም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ እግሮች፥ የነሐሱን መሠዊያ፥ ለእርሱም የሚያገለግለውን የነሐሱን መከታ፥ የመሠዊያውንም ዕቃ ሁሉ ሠራ 31በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩን መግቢያ እግሮች፥ የማደሪያውን ካስማዎች ሁሉና በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን ካስማዎች ሁሉ ሠራ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 38: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ