ትንቢተ ሕዝቅኤል 13
13
የሐሰተኛ ነብያት መቀጣት
1የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት በሚናገሩ በእስራኤል ነቢያት ላይ ትንቢት ተናገር፥ ከገዛ ልባቸውም ትንቢት የሚናገሩትን እንዲህ በላቸው፦ የጌታን ቃል ስሙ፤ 3ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ምንም ሳያዩ የገዛ መንፈሳቸውን የሚከተሉ ሞኞች ነቢያት ወዮላቸው! 4እስራኤል ሆይ፥ ነቢያትህ በፍርስራሽ መካከል እንደሚኖሩ ቀበሮች ናቸው። 5በጌታ ቀን ጦርነቱን መቋቋም እንዲችል ወደ ተሰበረው ቅጥር አልወጣችሁም፥ ወይም ለእስራኤል ቤት ቅጥር አልጠገናችሁም። 6ጌታ ሳይልካቸው፦ ጌታ ይላል የሚሉ ሰዎች ከንቱ ነገርንና ውሸተኛ ሟርትን አይተዋል፥ ሆኖም ቃላቸው እንዲፈጸም ይጠብቃሉ። 7እኔ ሳልናገር፦ ጌታ እንዲህ ብሏል ስትሉ፥ ከንቱ ራእይን አላያችሁምን፥ ውሸተኛንም ምዋርት አልተናገራችሁምን?
8ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ፥ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 9እጄ ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ በውሸትም በሚያምዋርቱ ነቢያት ላይ ትሆናለች፥ እነርሱም በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤል ቤት መዝገብ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። 10#ኤር. 6፥14፤ 8፥11።ምክንያቱም ሰላም ሳይኖር ሰላም እያሉ ሕዝቤን አታልለዋልና፥ አንድ ሰው ቅጥር ሲሠራ፥ እነሆ በኖራ ይቀቡታል፤ 11በኖራ የሚቀቡትን እንዲህ በላቸው፦ ይወድቃል፤ ዶፍ ዝናብ ይዘንባል፥ ታላቅም የበረዶ ድንጋዮች ይወድቃሉ፥ ዐውሎ ነፋስም ይሰነጣጥቀዋል። 12እነሆ ግንቡ በሚፈርስበት ጊዜ፦ የቀባችሁት ኖራ የት አለ? አይሉአችሁምን? 13ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፥ በቁጣዬም ዶፍ ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ ሊያጠፋው ይወርዳል። 14ኖራ የቀባችሁትን ቅጥር አፈርሳለሁ፥ ወደ ምድርም እጥለዋለሁ፥ መሠረቱም ይታያል። እርሱም ይወድቃል፥ እናንተም በውስጧ ትጠፋላችሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። 15ቁጣዬንም በግንቡ ላይና ኖራ በቀቡት ላይ እፈጽማለሁ፥ ቅጥሩና ቅጥሩን የቀቡት የሉም እላችኋለሁ። 16እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የተናገሩ፥ ሰላም ሳይኖር የሰላምን ራእይ ያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
17አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ከልባቸው#13፥17 ከራሳቸው። ትንቢት ወደሚናገሩት ወደ ሕዝብህ ሴቶች ልጆች አድርግ፥ ትንቢትም ተናገርባቸው፤ 18እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ ለእጅ ድጋፍ መከዳ ለሚሰፉ ለሰውም ሁሉ ራስ እንደየቁመቱ ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን? 19እፍኝ ገብስና ቁራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ፥ ውሸት ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ፥ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት በመግደል፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን ነፍሳት በሕይወት በማትረፍ በሕዝቤ ፊት አርክሳችሁኛል።
20ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት በመከዳችሁ ላይ ነኝ፥ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀድዳታለሁ፥ እንደ ወፍም የምታጠምዱአቸውን ነፍሳት እለቅቃለሁ። 21መሸፈኛዎቻችሁን ደግሞ እቀድዳለሁ፥ ሕዝቤንም ከእጃችሁ አድናለሁ፥ ከዚህ ወዲያ በእጃችሁ ለመታደን አይሆኑም፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። 22ምክንያቱም እኔ ያላሳዘንሁትን የጻድቁን ልብ በውሸት አሳዝናችኋልና፥ ከክፉ መንገዱ ተመልሶ በሕይወትም እንዳይኖር የኃጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤ 23ስለዚህ ከዚህ በኋላ ከንቱ ራእይን አታዩም፥ ምዋርትም አታሟርቱም፥ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 13: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ