ትንቢተ ሕዝቅኤል 14
14
የእግዚአብሔር ፍርድ ተገቢነት
1ከእስራኤልም ሽማግሌዎች አንዳንዶች ወደ እኔ መጥተው በፊቴ ተቀመጡ። 2የጌታም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 3የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል። የበደላቸውንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊታቸው አስቀምጠዋል፥ ታዲያ እንዲጠይቁኝ ልፍቀድላቸው? 4ስለዚህ ተናገራቸው፥ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማንም ሰው ከእስራኤል ቤት ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ወደ ነቢዩም የሚመጣ፥ እኔ ጌታ እንደ ጣዖታቱ ብዛት እመልስለታለሁ። 5ይህም የእስራኤልን ቤት ለመያዝ ነው፤ ሁሉም በጣዖቶቻቸው ምክንያት በልባቸው ከእኔ ተለይተዋልና፤
6ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመለሱ፥ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ። 7ማንም ከእስራኤልም ቤት፥ በእስራኤልም የሚቀመጥ መጻተኛ፥ ራሱን ከእኔ የሚለይ፥ ጣዖቶቹን በልቡ የሚያኖር፥ የበደሉንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊቱ የሚያቆም፥ ስለ እኔም ለመጠየቅ ወደ ነቢዩ የሚመጣ፥ እኔ ጌታ ራሴ እመልስለታለሁ፥ 8ፊቴን በዚያ ሰው ላይ አደርጋለሁ ምልክትና ምሳሌም አደርገዋለሁ፥ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። 9ነቢዩ ቢታለል፥ ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ ያታለልሁ እኔ ጌታ ነኝ፥ በእርሱም ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከሕዝቤ ከእስራኤል መካከልም አጠፋዋለሁ። 10በደላቸውን ይሸከማሉ፥ እንደ ጠያቂው በደል የነቢዩም በደል እንዲሁ ይሆናል። 11ይኸውም የእስራኤል ቤት ደግመው ከእኔ ርቀው እንዳይጠፉ፥ በመተላለፋቸውም ሁሉ እንዳይረክሱ ነው፥ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
12የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 13የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር ባለመታመን በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እጄን እዘረጋባታለሁ፥ የምግቧንም በትር እሰብራለሁ፥ ራብን እሰድድባታለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ አጠፋለሁ፤ 14ኖኅ ዳንኤልና ኢዮብ እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ በውስጧ ቢኖሩ እንኳ በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 15ክፉ አውሬ በምድሪቱ እንዲያልፍ ባደርግ፥ ልጅ አልባ ቢያደርጋት፥ በአውሬው ምክንያት ማንም እንዳያልፍባት ባድማ ብትሆን፥ 16እነዚህ ሦስት ሰዎች በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች። 17ወይም በዚያች ምድር ላይ ሰይፍ አምጥቼ፦ በምድሪቱ ላይ ሰይፍ ይለፍ ብል፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ባጠፋ፥ 18እነዚህ ሦስት ሰዎች በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም። 19ወይም በዚያች ምድር ላይ ቸነፈር ብሰድድ፥ ቁጣዬን በደም ባፈስስባትና ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ ባጠፋ፥ 20ኖኅ፥ ዳንኤልና ኢዮብ በውስጧ ቢኖሩ፥ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በጽድቃቸው ነፍሳቸውን ያድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም።
21 #
ራእ. 6፥8። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥ 22ነገር ግን እነሆ፥ የሚያመልጡና ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን የሚያወጡ ይቀሩላታል፥ እነሆ ወደ እናንተ ይመጣሉ፥ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ፥ በኢየሩሳሌም ላይ ስላመጣሁት ክፉ ነገር፥ ስላመጣሁባትም ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ። 23መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል፥ ያደረግሁትም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 14: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ