ትንቢተ ሕዝቅኤል 27
27
ስለ ጢሮስ የወጣ ሙሾ
1የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ጢሮስ ሙሾ አውርድ፥ 3በባሕር መግቢያ ለምትኖረውና፥ በብዙ ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር ለምትነግደው ጢሮስ እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ፥ አንቺ፦ “በውበት ፍጹም ነኝ” ብለሻል። 4ዳርቻሽ በባሕር ልብ#27፥4 በባሕር መሀል ነው፤ ሠሪዎችሽ ውበትሽን ፍጹም አደረጉ። 5ሳንቃዎችሽን ሁሉ ከሴኒር በመጣ ጥድ ሠሩ፤ ደቀልንም ሊሰሩልሽ ከሊባኖስ ዝግባ ወሰዱ። 6በባሻን ባሉጦች#27፥6 ባሉጥ፦ ወርካ የሚመስል ዛፍ። መቅዘፊያሽን ሠሩ፤ በዝሆን ጥርስ ከታሻበ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍ ወለልሽን ሠርተዋል። 7ዓላማ ሆኖ እንዲያገለግልሽ፥ ሸራሽ ከግብጽ በፍታና ከወርቀ ዘቦ ተሠርቶአል፥ መደረቢያሽም ከኤሊሻ ደሴቶች የመጣ ሰማያዊና የወይን ጠጅ ነበር። 8የሲዶናና የአርቫድ ነዋሪዎች ቀዛፊዎችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የነበሩት ባለሙያዎችሽ#27፥8 አንዳንድ ትርጉሞች ጥበበኞችሽ ይላሉ። የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ። 9በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፤ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው ከአንቺ ጋር ለመለዋወጥ#27፥9 ዕቃ በመለዋወጥ መገበያየት። በአንቺ ውስጥ ነበሩ። 10ፋርስ፥ ሉድና ፉጥ በሠራዊትሽ ውስጥ ወታደሮችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቁርም በአንቺ ውስጥ ሰቀሉ፤ ውበትን ሰጡሽ። 11የአርቫድ ልጆችና ሠራዊቶችሽ በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ነበሩ፥ ጋማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ፤ ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፥ ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።
12ከሀብትሽ ብዛት የተነሣ ተርሴስ ነጋዴሽ ነበረች፥ በብርና በብረት በቆርቆሮና በእርሳስ ዕቃሽን ለወጡ። 13ያቫን፥ ቱባልና ሜሼክ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር፤ ዕቃሽን በሰዎች ነፍስና በናስ ዕቃ ይለውጡ ነበር። 14የቶጋርማ ቤትም ዕቃዎችሽን በፈረሶች፥ በፈረሰኞችና በበቅሎዎች ለወጡ። 15የድዳን ልጆችም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ይለውጡ ዘንድ የዝሆን ጥርስና ዞጲ አመጡልሽ። 16ከምርትሽ ብዛት የተነሣ አራም#27፥16 አንዳንድ ትርጉሞች ሶርያ ይላሉ፥ ዕብራይስጡ ግን አራም ይለዋል። ነጋዴሽ ነበረች፤ ዕቃዎችሽን በበሉር፥ በወይን ጠጅ፥ በወርቀ ዘቦ፥ በጥሩ በፍታም በዛጐልም በቀይ ዕንቁም ይቀይሩ ነበር። 17ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ዕቃዎችሽን በሚኒት ስንዴ፥ ጣፋጭ ዳቦ፥ ማር፥ ዘይትና በለሳን ይለውጡ ነበር። 18በሁሉም ነገር ሀብታም ስለ ነበርሽ፥ ከንብረትሽ ብዛት የተነሣ፥ ደማስቆ በሔልቦን የወይን ጠጅ፥ ነጭ የበግ ጠጉር፥ ነጋዴሽ ነበረች። 19ከኡዛል ቭዳንና ያቫን ዕቃዎችሽን ይለውጡ ነበር፤ የተሠራ ብረትና ብርጉድ ቀረፋም ሸቀጥሽ ነበረ። 20ድዳን ለግልቢያ በሚሆን ኮርቻ ነጋዴሽ ነበረች። 21ዓረብና የቄዳር ልዑላን ሁሉ የእጅሽ ነጋዴዎች ነበሩ፤ በጠቦቶች፥ በአውራ በጎችና በፍየሎች በእነዚህ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር። 22የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች እነዚህ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ምርጥ በሆኑ ቅመማ ቅመሞች ሁሉ፥ በክበረ ድንጋይ ሁሉና በወርቅ ሸቀጥሽን ይለውጡ ነበር። 23ሐራን፥ ካኔ፥ ዔድን፥ የሳባ ነጋዴዎች፥ አሦርና ኪልማድ ነጋዴዎችሽ ነበሩ። 24እነዚህ በገበያሽ ውስጥ በአማረ ልብስ፥ በሰማያዊ ካባ፥ በወርቀ ዘቦ፥ በዝግባ በተሠራች በገመድም በታሰረች በግምጃም በተሞላች ሳጥን ይነግዱ ነበር። 25#ራእ. 18፥11-19።የተርሴስ መርከቦች ሸቀጥሽን የሚያጓጉዙልሽ ነበሩ፤ አንቺም ተሞልተሽ ነበር፥ በባሕርም ልብ ውስጥ እጅግ ከበርሽ።
26ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ውኆች አመጡሽ፤ የምሥራቅ ነፋስ በባሕር ልብ ሰበረሽ። 27ሀብትሽ፥ ሸቀጥሽ፥ ንግድሽ፥ መርከበኞችሽ፥ መርከብ መሪዎችሽ፥ ሰባራሽን የሚጠግኑ፥ ሸቀጥሽን የሚነግዱ፥ በአንቺ ውስጥ ያሉ ወታደሮችሽ ሁሉ፥ በውስጥሽ ካሉት ጉባኤ ሁሉ ጋር በውድቀትሽ ቀን ወደ ባሕር ልብ ይወድቃሉ። 28ከመርከብ መሪዎች ጩኸት ድምፅ የተነሣ መሰማሪያዎች ይንቀጠቀጣሉ። 29መቅዘፊያውን የያዙት ሁሉ፥ መርከበኞች፥ የባሕር መርከብ መሪዎችም ሁሉ ከመርከቦቻቸው ይወርዳሉ፤ በመሬትም ላይ ይቆማሉ፥ 30ድምፃቸውንም በአንቺ ላይ ያሰማሉ፥ ምርር ብለው ይጮኻሉ፤ በራሳቸውም ላይ አቧራ ይነሰንሳሉ፤ በአመድም ላይ ይንከባበላሉ፤ 31ስለ አንቺ ጠጉራቸውን ይላጫሉ፥ ማቅም ይታጠቃሉ፤ በነፍስ ምሬትም ስለ አንቺ መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ። 32በልቅሶአቸውም ስለ አንቺ ሙሾን ያነሡልሻል፥ እንዲህም እያሉ በአንቺ ላይ ያሞሻሉ፦ በባሕር መካከል ጠፍቶ የቀረ እንደ ጢሮስ ማን ነው? 33ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ ሕዝቦችን አጥግበሻል፤ በተትረፈረፈ በሀብትሽና በሸቀጣ ሸቀጥሽ የምድርን ነገሥታት አበልጽገሻል። 34በጥልቅ ውኆች ውስጥ፥ በባሕር በተሰበርሽ ጊዜ ግን ሸቀጣ ሸቀጥሽና በመካከልሽ ያሉ ጉባኤሽ#27፥34 በውስጥሽ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሁሉ ወድቀዋል። 35በደሴቶች የሚኖሩ ሁሉ በአንቺ ደንግጠዋል፥ ነገሥታቶቻቸውም እጅግ ፈርተዋል፥ ፊታቸውም ተለውጦአል። 36ከሕዝቦች መካከል ያሉ ነጋዴዎች አፏጩብሽ፤ አስደንጋጭ ሆነሻል፥ ለዘለዓለምም አትገኚም።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 27: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ