ትንቢተ ሕዝቅኤል 43
43
መለኮታዊው ክብር ወደ መቅደሱ መመለሱ
1ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ። 2#ሕዝ. 10፥3፤4፤18፤19፤ 11፥22፤23፤ ራእ. 1፥15።እነሆ፥ የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ መጣ፤ ድምፁም እንደ ብዙ ውኆች ድምጽ ነበር፥ ከክብሩ የተነሣ ምድር ታበራ ነበር። 3ያየሁትም ራእይ ከተማይቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፤ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንዳየሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ። 4የጌታ ክብር በሩ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው ቤት ገባ። 5መንፈስም አነሣኝ፥ ወደ ውስጠኛውም አደባባይ አስገባኝ፤ እነሆ፥ የጌታ ክብር ቤቱን ሞላው።
6ከቤቱ ውስጥ ሆኖ የሚናገረኝን ሰማሁ፥ በአጠገቤም ሰው ቆሞ ነበር። 7እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ ማሳረፊያ ይህ ነው። የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ዳግመኛ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም። 8መድረካቸውን በመድረኬ አጠገብ፥ መቃናቸውን በመቃኔ አጠገብ በማድረጋቸው፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ግንብ ብቻ ቀረ፥ በሠሩት ርኩሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ፥ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው። 9አሁንም ዝሙታቸውንና የነገሥታቶቻቸውን ሬሳ ከእኔ ዘንድ ያርቁ፥ እኔም ለዘለዓለም በመካከላቸው እኖራለሁ።
10አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ በኃጢአታቸው እንዲያፍሩ ለእስራኤል ቤት ስለ ቤቱ ንገራቸው፥ ንድፉንም ይለኩ። 11በሠሩት ሥራ ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ፥ የቤቱን ንድፉንና አሠራሩን፥ መውጫውንና መግቢያውን፥ አጠቃላይ ንድፉን፥ ሥርዓቱን ሁሉ፥ ንድፉን ሁሉ፥ ሕጉን ሁሉ አሳውቃቸው፤ ንድፉን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ እንዲያዩትና እንዲያደርጉትም በፊታቸው ጻፈው። 12የቤቱ ሕግ ይህ ነው፤ በተራራው ራስ ላይ በዙሪያው ያለው ስፍራ ሁሉ የተቀደስ ይሆናል። እነሆ፥ የቤቱ ሕግ ይህ ነው።
ስለ መሠዊያው
13 #
ዘፀ. 27፥1፤2፤ 2ዜ.መ. 4፥1። የመሠዊያውም ልክ በክንድ ይህ ነው፤ ክንዱም አንድ ክንድ ከስንዝር ነው። መሠረቱ ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፥ ዙሪያውም አንድ ስንዝር ጠርዝ አለው፤ ይህም የመሠዊያው ከፍታ ነው። 14መሬት ላይ ካለው መሠረት ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፤ ከትንሹ እርከን ጀምሮ እስከ ትልቁ እርከን ድረስ አራት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው። 15የመሠዊያው ምድጃው አራት ክንድ ነው፤ ከመሠዊያው ምድጃ በላይ አራት ቀንዶች አሉ። 16የመሠዊያው ምድጃ ርዝመት ዐሥራ ሁለት ክንድ፥ ወርዱም ዐሥራ ሁለት ክንድ ነው፥ አራቱም ማዕዘን እኩል ነው። 17የእርከኑም ርዝመት ዐሥራ አራት ክንድ ወርዱም ዐሥራ አራት ክንድ ነው፥ አራቱም ማዕዘን እኩል ነው፤ በዙሪያውም ያለው ጠርዝ ግማሽ ክንድ ነው፥ የመሠረቱም ዙሪያ አንድ ክንድ ነው፤ ደረጃዎቹ ወደ ምሥራቅ ይመለከታሉ።
18 #
ዘፀ. 29፥35-37፤ 1መቃ. 4፥52-56። እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መሠዊያው#43፥18 መሠዊያው የሚለው በዕብራይስጡ የለም። ተሰርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕት በላዩ በሚያቀርቡበት ደምንም በላዩ በሚረጩበት ቀን የመሠዊያው ሥርዓት ይህ ነው። 19ሊያገለግሉኝ ወደ እኔ ለሚቀርቡ ለካህናት፥ ከሳዶቅ ዘር ለሆኑ ለሌዋውያን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትሰጣቸዋለህ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 20ከደሙ ትወስዳለህ፥ በአራቱ ቀንዶቹ፥ በእርከኑ፥ በአራቱ ማዕዘን ላይ፥ በዙሪያውም ባለው ጠርዝ ላይ ታደርጋለህ፤ እንዲሁ ታነጻዋለህ ታጠራዋለህም። 21ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፥ ከመቅደሱ ውጭ ባለው ቤት በተወሰነው ስፍራ ይቃጠላል። 22በሁለተኛውም ቀን ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ነውር የሌለበትን አውራ ፍየል ታቀርባለህ፤ በወይፈኑም እንዳነጹት እንዲሁ መሠዊያውን ያነጹበታል። 23ማንጻቱንም ከፈጸምህ በኋላ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈንና ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ታቀርባለህ። 24በጌታ ፊት ታቀርባቸዋለህ፥ ካህናቱም በላያቸው ላይ ጨው ይነስንሱባቸው፥ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡአቸዋል። 25ሰባት ቀን በየዕለቱ ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን አውራ ፍየልን ታቀርባለህ፥ ነውር የሌለባቸውን ከመንጋው አንድ ወይፈን ከመንጋው አንድ አውራ በግ ያቀርባሉ። 26ሰባት ቀን ለመሠዊያው ያስተሰርያሉ ያነጹታልም፥ እጃቸውን ይሞላሉ። 27ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀንና ከዚያም በኋላ፥ ካህናቱ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና የሰላም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 43: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ