የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ገላትያ ሰዎች መግቢያ

መግቢያ
ስለ ኢየሱስ አዳኝነት የሚናገረው የወንጌል ቃል በየቦታው እየተሰበከ፥ አይሁድ ያልሆኑ ሰዎች እየተቀበሉት በሄዱ መጠን፥ “ክርስቲያን እና የእግዚአብሔር ሕዝብ አባል ለመሆን የኦሪትን ሕግ መፈጸም ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? መገረዝ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም?” የሚሉት ጥያቄዎች አብረው ተነሡ፤ በሮም ስር በትንሿ እስያ የሮም ግዛት በሆነችው በገላትያ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት መካከል “ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዲጸድቅ በኢየሱስ ማመን ብቻ ሳይሆን በሙሴም አማካይነት የተሰጠውን ሕግ መፈጸም አለበት” በማለት ጳውሎስን የሚቃወሙ ሰዎች ነበሩ።
ጳውሎስ ይህን የገላትያን መልእክት የጻፈው በዚህ ትምህርት ግራ የተጋቡትን ሰዎች ወደ ትክክለኛው እምነትና የክርስትና ሕይወት ለመምራት ነው፤ ጳውሎስ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ መሆኑን በማረጋገጥ ይጀምራል፤ ለሐዋርያነት የጠራው እግዚአብሔር እንጂ ሰው እንዳልሆነና የእርሱም ተልእኮ አይሁድ ወዳልሆኑ ሰዎች እንደሆነ በመዘርዘር ያስረዳል፤ በመጨረሻዎቹ ምዕራፎች ውስጥ ክርስቲያናዊ ሕይወት በኢየሱስ በማመን ከሚገኘው ፍቅር የሚመነጭ መሆኑን ያስረዳል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ (1፥1-10)
የጳውሎስ ሐዋርያዊ ሥልጣን (1፥11—2፥21)
በወንጌል የሚገኘው የእግዚአብሔር ጸጋና ነጻነት (3፥1—4፥31)
በወንጌል ላይ የተመሠረተ ክርስቲያናዊ ሕይወት (5፥1—6፥10)
መደምደሚያ (6፥11-18)
ምዕራፍ

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ