ኦሪት ዘፍጥረት 29
29
ያዕቆብ ወደ ላባ ቤት መድረሱ
1ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ። 2በሜዳውም እነሆ ጉድጓድን አየ፥ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፥ ከዚያ ጉድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፥ በጉድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። 3መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፥ ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጉድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር። 4ያዕቆብም፦ “ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንት የወዴት ናችሁ?” አላቸው። እነርሱም፦ “እኛ የካራን ነን” አሉት። 5“የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?” አላቸው። እነርሱም፦ “እናውቀዋለን” አሉት። 6እርሱ፦ “ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፦ “አዎን ደኅና ነው፥ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች” አሉት። 7እርሱም፦ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚከማቹበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፥ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው” አላቸው። 8እነርሱም አሉ፦ “መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም፥ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።” 9እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረሰች፥ እርሷ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና። 10ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የአጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ፥ ቀረበ ከጉድጓዱም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ። 11ያዕቆብም ራሔልን ሳማት፥ ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። 12ያዕቆብም የአባትዋ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት፥ እርሷም ሮጣ ሄዳ ለአባትዋ ይህን ነገር ነገረችው።
13ላባም የእኅቱን ልጅ የያዕቆብን ወሬ በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው። 14ላባም፦ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።”
የያዕቆብ ሁለቱ ጋብቻ
15ላባም ያዕቆብን፦ “ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ደመወዝህ ምንድነው? ንገረኝ” አለው። 16ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፥ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱ ስም ራሔል ነበረ። 17ልያም ዓይነ ልም ነበረች፥ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ። 18ያዕቆብም ራሔልን ወደደ፥ እንዲህም አለ፦ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ።” 19ላባም፦ “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጣት ይሻላል፥ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለ። 20ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፥ እርሷንም ይወድዳት ስለ ነበረ በእርሱ ዘንድ እንደ ጥቂት ቀን ሆነለት።
21ያዕቆብም ላባን፦ “ወደ እርሷ እገባ ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈጽሞአልና” አለው። 22ላባም የዚያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፥ ሰርግም አደረገ። 23በመሸም ጊዜ ልጁን ልያን ወስዶ ለያዕቆብ አገባለት፥ ያዕቆብም ወደ እርሷ ገባ። 24ላባም ለልጁ ለልያ ባርያይቱን ዘለፋን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። 25በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ሆና ተገኘች፥ ላባንም፦ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለግልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው። 26ላባም እንዲህ አለ፦ “በአገራችን ታላቂቱ ሳለች፥ ታናሺቱን እንስጥ ዘንድ ወግ አይደለም፥ 27ይህችንም ሳምንት ፈጽም፥ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርሷን ደግሞ እሰጥሃለሁ።” 28ያዕቆብም እንዲህ አደረገ፥ ይህችንም ሳምንት ፈጸመ፥ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ሰጠው። 29ላባም ለልጁ ለራሔል ባርያይቱን ባላን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። 30ያዕቆብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔልንም ከልያ ይልቅ ወደዳት፥ ሌላ ሰባት ዓመትም ተገዛለት።
የያዕቆብ ልጆች
31እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን ባየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት፥ ራሔል ግን መካን ነበረች። 32ልያም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና። 33ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ደገመኝ አለች፥ ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው። 34ደግሞም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ አሁንም ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፥ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና አለች፥ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። 35ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፥ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 29: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ