ኦሪት ዘፍጥረት 30
30
1ራሔልም ለያዕቆብ ልጆችን እንዳልወለደች ባየች ጊዜ በእኅትዋ ቀናችባት፥ ያዕቆብንም፦ ልጆች ስጠኝ፥ ይህስ ካልሆነ እሞታለሁ አለችው። 2ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት። 3እርሷም ባርያዬ ባላ እነሆ አለች፥ ድረስባት፥ በእኔም ጭን ላይ ትውለድ፥ የእርሷም ልጆች ለእኔ ደግሞ ይሁኑልኝ አለች። 4ባርያዋን ባላንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ለእርሱ ሰጠችው፥ ያዕቆብም ደረሰባት። 5ባላም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት። 6ራሔልም፦ እግዚአብሔር ፈረደልኝ፥ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ አለች፥ ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። 7የራሔልም ባርያ ባላ ደግማ ፀነሰች፥ ለያዕቆብም ሁለተኛ ወንድ ልጅን ወለደች። 8ራሔልም፦ ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች፥ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።
9ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባርያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆንውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው። 10የልያ ባርያ ዘለፋም ወንድ ልጅን ለያዕቆብ ወለደች። 11ልያም፦ ጉድ አለች፥ ስሙንም ጋድ ብላ ጠራችው። 12የልያ ባርያ ዘለፋም ዳግመኛ ለያዕቆብ ወንድ ልጅን ወለደች። 13ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፥ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፥ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው።
14ሮቤልም ስንዴ በሚታጨድበት ወራት ወጣ፥ በእርሻም እንኮይ አገኘ፥ ለእናቱ ለልያም አመጣላት። ራሔልም ልያን፦ 15“የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። እርሷም፦ “ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም፦ “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ” አለች። 16ያዕቆብም ሲመሽ ከዱር ገባ፥ ልያም ልትቀበለው ወጣች እንዲህም አለችው፦ “ወደ እኔ ትገባለህ፥ በልጄ እንኮይ በእርግጥ ተከራይቼሃለሁና።” በዚያችም ሌሊት ከእርሷ ጋር ተኛ። 17እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። 18ልያም፦ “ባርያዬን ለባሌ ስለ ሰጠሁ እግዚአብሔር ዋጋዬን ሰጠኝ” አለች፥ ስሙንም ይሳኮር ብላ ጠራችው። 19ልያም ደግማ ፀነሰች፥ ስድስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። 20ልያም፦ “እግዚአብሔር መልካም ስጦታን ሰጠኝ፥ እንግዲህስ ባሌ ከእኔ ጋር ይኖራል፥ ስድስት ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፥ ስሙንም ዛብሎን ብላ ጠራችው። 21ከዚያም በኋላ ሴት ልጅን ወለደች፥ ስምዋንም ዲና አለቻት። 22እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፥ እግዚአብሔርም ተለመናት፥ ማኅፀንዋንም ከፈተላት፥ 23ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ “እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ” አለች፥ 24ስሙንም፦ “እግዚአብሔር ሁለተኛ ወንድ ልጅን ይጨምርልኝ” ስትል ዮሴፍ ብላ ጠራችው።
ያዕቆብ እንዴት እንደ ከበረ
25ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ። 26ስለ እነርሱ የተገዛሁላቸውን ሚስቶችንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፥ የተገዛሁልህን መገዛት ታውቃለህና።” 27ላባም፦ “በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚህ ተቀመጥ፥ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና” አለው። 28“ደመወዝህን ንገረኝ፥ እርሱንም እሰጥሃለሁ” አለ። 29እርሱም አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህ፥ ከብትህንም እንዴት እንደ ጠበቅሁልህ አንተ ታውቃለህ። 30ከእኔ መምጣት በፊት የነበረህ ጥቂት ነበርና፥ ዛሬም እጅግ በዛ፥ ወደ አንተ በመምጣቴም እግዚአብሔር ባረክህ፥ አሁንም እኔ ደግሞ ለቤቴ የምሠራው መቼ ነው?” 31እርሱም፦ “የምሰጥህ ምንድነው?” አለ። ያዕቆብም አለው፦ “ምንም አትስጠኝ፥ ይህንም ነገር ብታደርግልኝ እንደገና በጎችህን አበላለሁ እጠብቃለሁም። 32ዛሬ በመንጎችህ በኩል አልፋለሁ፥ በዚያም ከበጎችህ መካከል ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለበቱን ጥቁሩንም በግ ሁሉ፥ ከፍየሎቹም ነቁጣና ዝንጉርጉር ያለበቱን እለያለሁ፥ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ። 33ስለዚህም በፊትህ ያለውን ደመወዜን ለመመልከት በመጣህ ጊዜ ወደ ፊት ጻድቅነቴ ይመሰክርልኛል፥ ከፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ የሌለበት ከበግ ጠቦቶችም ጥቁር ያልሆኑ ሁሉ፥ እርሱ በእኔ ዘንድ ቢገኝ እንደ ተሰረቀ ይቆጠርብኝ።” 34ላባም፦ “እነሆ እንደ ቃልህ ይሁን” አለ። 35በዚያም ቀን ከተባዕቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው። 36በእርሱና በያዕቆብ መካከልም የሦስት ቀን መንገድ ያህል አራቃቸው፥ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን በጎች ይጠብቅ ነበር።
37ያዕቆብም ልብን ለውዝ ኤርሞን ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለውን ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው። 38የላጣቸውንም በትሮች በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ በበጎች ፊት አኖራቸው፥ በጎቹ ውኃ ሊጠጡ በመጡ ጊዜ ይጎመጁ ነበር። 39በጎቹም በትሮቹን አይተው ከመጎምጀታቸው የተነሣ ፀነሱ፥ በጎቹም ሽመልመሌ መሳይና ዝንጉርጉር ነቁጣም ያለበቱን ወለዱ። 40ያዕቆብም ጠቦቶቹን ለየ፥ ሽመልመሌ መሳይና ጥቁር ያለባቸውን በጎቹንም ሁሉ በላባ በጎች ፊት ለፊት አኖረ፥ መንጎቹንም ለብቻቸው አቆማቸው፥ ወደ ላባም በጎች አልጨመራቸውም። 41እንዲህም ሆነ፥ የበረቱት በጎች በጎመጁ ጊዜ፥ በጎቹ በትሮቹን አይተው በበትሮቹ አምሳል ይፀንሱ ዘንድ ያዕቆብ በትሮቹን በውኃ ማጠጫው ገንዳ ውስጥ ከበጎቹ ፊት አደረገ፥ 42በደከሙ በጎችም ፊት በትሩን አያደርገውም ነበር፥ የደከሙትም ለላባ፥ የበረቱትም ለያዕቆብ ሆኑ። 43ያ ሰውም እጅግ ባለ ጠጋ ሆነ፥ ብዙም ከብት ሴቶችም ወንዶችም ባርያዎች ግመሎችም አህዮችም ሆኑለት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 30: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ