ትንቢተ ሆሴዕ 5
5
በእስራኤልና በይሁዳ ላይ ፍርድ መምጣቱ
1ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! አድምጡ፤ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው። 2ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፤ እኔ ግን እነርሱን ሁሉ እገሥጻለሁ። 3እኔ ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረም፤ አሁን ግን ኤፍሬም ሆይ! አመንዝረሃል፥ እስራኤልም ረክሶአል። 4ሥራቸው ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አልፈቀደላቸውም፤ የአመንዝራ መንፈስ በውስጣቸው አለና፤ ጌታንም አላውቁምና። 5የእስራኤልም ትዕቢት በራሱ ላይ መስክሮአል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኃጢአታቸው ተሰናክለዋል፤ ይሁዳም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ተሰናክሎአል። 6ጌታንም ለመሻት በጎቻቸውንና በሬዎቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም። 7ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና ጌታን አታልለዋል፤ አሁን ደግሞ እነርሱን ከርስታቸው ጋር የወሩ መባቻ ይበላቸዋል።
8በጊብዓ ቀንደ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ “ብንያም ሆይ! ከአንተ ጋር ነን እያላችሁ በቤትአዌን ላይ የማስጠንቀቂያውን ነጋሪት ድምፅ አሰሙ።” 9ኤፍሬም በተግሣጽ ቀን ባድማ ይሆናል፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል እርግጥ የሆነውን ነገር አሳውቂያለሁ። 10የይሁዳ አለቆች ድምበርን እንደሚያፈርሱ ሰዎች ሆነዋል፤ እኔም መዓቴን እንደ ውኃ በእነርሱ ላይ አወርድባቸዋለሁ። 11ኤፍሬም ትእዛዝን መከተል ፈጽሞ አልወደደምና የተጨቆነና በፍርድ የተጐዳ ሆኖአል። 12እኔም ለኤፍሬም እንደ ብል፥ ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ ሆኜአለሁ። 13ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም። 14እኔም ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔ ራሴ ነጥቄ እሄዳለሁ እወስዳለሁም፥ ሊያድንም የሚችል ማንም የለም። 15በደላቸውንም ተቀብለው ፊቴን እስኪሹ ድረስ ወደ ስፍራዬ ተመልሼ እሄዳለሁ፤ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 5: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ