መጽሐፈ መሳፍንት 14
14
የሳምሶን ጋብቻ
1ሶምሶን ወደ ቲምና ወረደ፤ እዚያም አንዲት ወጣት ፍልስጥኤማዊት አየ። 2እንደተመለሰም አባቱንና እናቱን፥ “በቲምና አንዲት ወጣት ፍልስጥኤማዊት አይቻለሁና አሁኑኑ አጋቡኝ” አላቸው። 3#ዘፍ. 24፥3-4፤ 26፥34-35፤ 28፥1-2፤6-9።አባቱና እናቱም፥ “ከዘመዶችህ ወይም ከሕዝባችን ሁሉ መካከል ለአንተ የምትሆን ሴት መች ታጣችና ነው ወዳልተገረዙት አሕዛብ ዘንድ ሚስት ፍለጋ የሄድከው?” አሉት። ሳምሶንም አባቱን፥ “ልቤን የማረከችው እርሷ ናትና እርሷን አጋባኝ” አለው። 4#1ሳሙ. 10፥14-16፤ ሉቃ. 2፥41-51።በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።#2ነገ. 5፥7።
5ከዚያም ሳምሶን ከአባቱና ከእናንቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ፤ በዚያም ከአንድ የወይን አትክልት ቦታ እንደ ደረሱ፥ ድንገት አንድ የአንበሳ ደቦል እያገሣ መጣበት። 6#መሳ. 3፥10፤ 6፥34፤ 11፥29፤ 13፥25፤ 14፥19፤ 15፥14፤ 1ሳሙ. 11፥6።በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ስለዚህ የፍየል ጠቦት እንደሚገነጣጠል አንበሳውን ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጠለው፤ ያደርገውን ግን ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም ነበር።#1ሳሙ. 17፥34-36፤ 2ሳሙ. 23፥20። 7ወደ ሴቲቱም ወረደ፤ ከእርሷም ጋር ተነጋገረ፤ እጅግም ወደዳት። 8ከጥቂት ቀን በኋላም ሊያገባት ተመለሰ፤ የአንበሳውንም በድን ለማየት ከመንገድ ዘወር አለ፤ በበድኑም ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮ ተመለከተ፤ ማርም ነበረበት፤ 9በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።
10የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በወጣቶች የተለመደ በነበረው መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ። 11እርሱም ለፍልስጥኤማውያን በታየ ጊዜ፥ ሠላሳ አጃቢዎች ሰጡት።
የሳምሶን እንቈቅልሽ
12ሳምሶን እንዲህ አላቸው፤ “እንድ እንቈቅልሽ እነግራችኋለሁ፤ ታዲያ ፍቺውን በሰርጉ በዓል ሰባት ቀኖች ውስጥ ከሰጣችሁኝ፥ ሠላሳ የቀጭን ፈትል በፍታ ቀሚስና ሠላሳ የክት ልብስ እሰጣችኋለሁ። 13እንቈቅልሹን ካልፈታችሁልኝ ግን ሠላሳ የቀጭን ፈትል በፍታ ቀሚስና ሠላሳውን የክት ልብስ እናንተ ትሰጡኛላችሁ።” እነርሱም፥ “በል እንቈቅልሽህን ንገረንና እንስማው” አሉት። 14ሳምሶንም፥ “ከበላተኛው መብል፥ ከብርቱም ጣፋጭ ነገር ወጣ” አላቸው። እነርሱም እስከ ሦስት ቀን ድረስ እንቈቅልሹን መፍታት አልቻሉም ነበር።
15 #
መሳ. 16፥5። በአራተኛው ቀን የሳምሶንን ሚስት፥ “የእንቈቅልሹን ፍች እንዲነግረን ባልሽን እስቲ አግባቢልን፤ ያለዚያ አንቺንም የአባትሽንም ቤተሰብ በእሳት እናቃጥላችኋለን፤ ጠርታችሁ የጋበዛችሁን ልትዘርፉን ነው እንዴ?” አሏት።#መሳ. 16፥6። 16#መሳ. 16፥15።ከዚያ የሳምሶን ሚስት ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ከፊቱ በመቅረብ፥ “ለካስ ትጠላኛለህ በእርግጥ አትወደኝም” አለችው። እርሱም፥ “ይህን ለአባቴም ሆነ ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት። 17#መሳ. 16፥16-18።ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የእንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች። 18በሰባተኛው ቀን ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት የከተማው ሰዎች፥
“ከማር የጣፈጠ ምን ተገኝቶ?
ከአንበሳስ ወዲያ ብርቱ ከየት መጥቶ” አሉት።
ሳምሶንም መልሶ፥
“በጊደሬ ባላረሳችሁ፥
እንቈቅልሼንም ባልፈታችሁ” አላቸው።
19 #
መሳ. 3፥10፤ 6፥34፤ 11፥29፤ 13፥25፤ 14፥6፤ 15፥14፤ 1ሳሙ. 11፥6። ከዚያም የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቁጣ እንደነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ። 20#መሳ. 15፥2፤ 6።የሳምሶንም ሚስት ለሚዜው ተዳረች።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 14: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ