ትንቢተ ኤርምያስ 41
41
በጎዶልያስ ላይ ዓመጽ መደረጉ
1 #
2ነገ. 25፥25። በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና ከንጉሡ ዋና ዋና ሹማምንት አንዱ የሆነው የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ፤ በዚያም በምጽጳ በአንድ ላይ እንጀራ እየበሉ ሳሉ፥ 2የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ። 3እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፥ በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ወታደሮች ሁሉ ገደላቸው።
4ከጎዶልያስ መገደል በኋላ ማንም ሳያውቅ በሁለተኛው ቀን 5ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ተልትለው፥ በጌታ ቤት ለማቅረብ የእህል ቁርባንና ዕጣን በእጃቸው ይዘው፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ። 6የናታንያም ልጅ እስማኤል ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ፤ በተገናኛቸውም ጊዜ፦ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው። 7ወደ ከተማይቱም መካከል በመጡ ጊዜ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰዎች ገደሉአቸው፥ በጉድጓድም መካከል ጣሉአቸው። 8በመካከላቸውም እስማኤልን፦ “በእርሻ ውስጥ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን” የሚሉት ዐሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም። 9እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ለመመከት የሠራው ምሽግ ነበረ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት። 10እስማኤልም በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ትሩፍ ሁሉ፥ የንጉሡን ሴቶች ልጆች የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረከ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ለመሄድ ተነሣ።
11የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ከእርሱም ጋር የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ በሰሙ ጊዜ፥ 12ሰዎቻቸውንም ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ለመዋጋት ሄዱ፤ በገባዖንም ባለው ታላቅ ኲሬ አጠገብ አገኙት። 13ከእስማኤልም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆችን ሁሉ ባዩ ጊዜ ደስ አላቸው። 14እስማኤልም ከምጽጳ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ዘወር ብለው ተመለሱ፥ ወደ ቃሬያም ልጅ ወደ ዮሐናን ሄዱ። 15የናታንያ ልጅ እስማኤል ግን ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ ወደ አሞንም ልጆች ሄደ።
16የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ እርሱና ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ከምጽጳ ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ትሩፍ ሁሉ፥ እንዲሁም ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ወታደሮች፥ ሴቶችንም፥ ልጆችንም፥ ጃንደረቦችንም፥ ወሰዱ፤ 17ተነሥተውም ወደ ግብጽ ለመሄድ በማቀድ በቤተልሔም አጠገብ ባለው በጌሮት ከመዓም ተቀመጡ፤ 18ምክንያቱም የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን በመፍራታቸው ነው።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 41: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ