መጽሐፈ ኢያሱ 2
2
ወደ ኢያሪኮ የተላኩት ሰላዮች
1 #
ዘዳ. 1፥22፤ ማቴ. 1፥5፤ ያዕ. 2፥25። የነዌም ልጅ ኢያሱ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር እንዲህ ብሎ ላከ፦ “ሄዱ፥ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ።” ሄዱም፤ ረዓብም ወደሚሉአት አመንዝራ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ። 2ለኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “እነሆ፥ ሰዎች ከእስራኤል ልጆች አገሩን ሊሰልሉ ወደዚህ በሌሊት ገቡ።” 3የኢያሪኮም ንጉሥ እንዲህ ብሎ ወደ ረዓብ ላከ፦ “አገሩን ሁሉ ሊሰልሉ መጥተዋልና ወደ አንቺ የመጡትን ወደ ቤትሽም የገቡትን ሰዎች አውጪ።” 4#ኢያ. 6፥17፤ ዕብ. 11፥31።ሴቲቱም ሁለቱን ሰዎች ወስዳ ሸሸገቻቸው፤ እርሷም እንዲህ አለች፦ “አዎን፥ ሰዎቹ ወደ እኔ መጥተዋል፥ ከወዴት እንደ ሆኑ ግን አላወቅሁም፤ 5በሩ በሚዘጋበት ጊዜ ሲመሻሽ ሰዎቹ ወጥተው ሄደዋል፤ ወዴት እንደ ሄዱ ግን አላውቅም፤ ፈጥናችሁ አሳድዱአቸው፥ ትደርሱባቸዋላችሁ።” 6እርሷ ግን ወደ ሰገነቱ አውጥታቸው ነበር፤ በዚያም በረበረበችው በተልባ እግር ውስጥ ሸሽጋቸው ነበር። 7ሰዎቹም ወደ ዮርዳኖስ መሻገሪያ እስከሚወስደው መንገድ ድረስ አሳደዱአቸው፤ አሳዳጆችም ከወጡ በኋላ በሩ ተዘጋ።
8እነርሱም ከመተኛታቸው በፊት ሴቲቱ ወደ እነርሱ ወደ ሰገነቱ ወጣች። 9#ዘፀ. 15፥15-16፤ 23፥27።ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ “ጌታ ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ ከእናንተም የተነሣ በፍርሃት መዋጣችንን፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ በፍርሃት እንደ ቀለጡ አወቅሁ። 10#ኢያ. 4፥23፤ ዘፀ. 14፥21፤ ዘኍ. 21፥23-26፤33-35።ከግብጽ ምድር በወጣችሁ ጊዜ ጌታ የኤርትራን ባሕር በፊታችሁ እንዳደረቀ፥ በዮርዳኖስም ማዶ በነበሩት እናንተም ፈጽማችሁ ባጠፋችኋቸው በሁለቱ በአሞራውያን ነገሥታት፥ በሴዎንና በዐግ ያደረጋችሁትን ሰምተናል። 11#ኢያ. 5፥1፤ ዘዳ. 4፥39፤ ሮሜ 10፥9። ይህንንም ነገር ሰምተን ልባችን ቀለጠ፤ ጌታ አምላካችሁም በላይ በሰማይ በታችም በምድር እርሱ አምላክ ነውና ከእናንተ የተነሣ ከእግዲህ ወዲያ ሰው ሁሉ ሐሞተ ቢስ ሆኖአል። 12#ኢያ. 2፥18፤ 6፥23፤25።አሁንም፥ እባካችሁ፥ በጌታ ማሉልኝ፥ በእውነትም ምልክት ስጡኝ፥ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደሠራሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት ሥሩ፥ 13#መሳ. 1፥22-26።አባቴንና እናቴንም ወንድሞቼንና እኅቶቼንም ያላቸውንም ሁሉ አድኑ፥ ነፍሳችንንም ከሞት ታደጉ።” 14ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፦ “ይህን ነገራችንን ለማንም ባትናገሩ ነፍሳችን በነፍሳችሁ ፋንታ ለሞት ይሆናል፤ ጌታም ምድሪቱን በሰጠን ጊዜ ለአንቺ ቸርነትንና ታማኝነትን እናደርጋለን።”
15ቤትዋም የከተማውን ቅጥር ተጠግቶ የተሠራ ነበረና፥ እርሷም በቅጥሩ ውስጥ ተቀምጣ ነበር፤ እነርሱንም በመስኮቱ በኩል በገመድ አወረደቻቸው። 16እርሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” 17ሰዎቹም እንዲህ አሉአት፦ “እኛ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ንጹሐን እንሆናለን። 18እነሆ፥ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው፤ አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የአባትሽንም ቤተሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብስቢ። 19ከቤትሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚወጣ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፥ እኛም ንጹሐን እንሆናለን፤ ነገር ግን ከአንቺ ጋር በቤቱ ውስጥ ያለውን ማንም ሰው እጁን ቢጭንበት ደሙ በእኛ ራስ ላይ ይሆናል። 20ይህንን ነገራችንን ግን ብትናገሪ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ነጻ እንሆናለን።” 21እርሷም እንዲህ አለች፦ “እንደ ቃላችሁ ይሁን፤” ከዚያም በኋላ በደኅና አሰናበተቻቸው እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።
22እነርሱም ሄደው ወደ ተራራው ደረሱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተቀመጡ፤ አሳዳጆቹም በመንገዱ ሁሉ ፈልገው አላገኙአቸውም። 23ሁለቱም ሰዎች ተመለሱ፥ ከተራራውም ወርደው ተሻገሩ፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ መጡ፤ የደረሰባቸውንም ሁሉ አወሩለት። 24ኢያሱንም እንዲህ አሉት፦ “በእውነት ጌታ አገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ ከእኛም የተነሣ በአገሩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ በፍርሃት ቀልጠዋል።#2፥24 ተሸብረዋል፤”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ