መጽሐፈ ኢያሱ 20
20
የመማፀኛ ከተሞች
1 #
ዘፀ. 21፥12-14፤ ዘኍ. 35፥9-15፤ ዘዳ. 4፥41-43፤ 19፥1-10። ጌታም ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘በሙሴ አማካይነት የነገርኋችሁን መማፀኛ ከተሞችን ለዩ፤ 3እነዚህም ከተሞች በስሕተት ሳያውቅም ሰውን የገደለ ገዳይ እንዲሸሽባቸው ከደም ተበቃዩ መማፀኛ ይሆኑላችኋል። 4ከእነዚህም ከተሞች ወደ አንዲቱ ይሸሻል፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ቆሞ በከተማይቱ ሽማግሌዎች ጆሮ ነገሩን ይናገራል፤ እነርሱም ወደ ከተማይቱ ይቀበሉታል፥ የሚቀመጥበትም ስፍራ ይሰጡታል ከእነርሱም ጋር ይቀመጣል። 5ደም ተበቃዩ ቢያሳድደው፥ አስቀድሞ ሳይጠላው ባልንጀራውን ሳያውቅ ስለ ገደለው ነፍሰ ገዳዩን በእጁ አሳልፈው አይስጡት። 6በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ፤ ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመለሳል፥ ወደ ከተማውም ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣበትም ከተማ ይገባል።’ ”
7 #
ኢያ. 15፥13፤ 19፥37፤ 21፥21። በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ። 8#ኢያ. 21፥27፤36።በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ራሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ። 9በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢያሱ 20: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ