የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢያሱ 21

21
ለሌዋውያን የተሰጡ ከተሞች
1 # ዘፀ. 6፥16-19፤ ዘኍ. 3፥17-20። የሌዋውያን አባቶች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ፥ ወደ እስራኤልም ልጆች ነገዶች አለቆች ቀረቡ፤ 2#ዘኍ. 35፥1-8።በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፦ “ጌታ በሙሴ አማካይነት የምንቀመጥባቸውን ከተሞችና ለከብቶቻችን መሰማሪያቸውን እንዲሰጠን አዝዞአል።” 3የእስራኤልም ልጆች እንደ ጌታ ትእዛዝ ከርስታቸው እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን ሰጡ።
4ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።
5 # ዘፍ. 46፥11። ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።
6ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።
7ለሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ወሰዱ።
8ጌታም በሙሴ አማካይነት እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። 9#1ዜ.መ. 6፥39-66።ከይሁዳም ልጆች ነገድ ከስምዖንም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡ። 10የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። 11በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ በዙሪያዋም ያለውን መሰማሪያ ሰጡአቸው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ። 12#ኢያ. 14፥14፤ 15፥13።የከተማይቱን እርሻ ግን መንደሮችዋንም ለዮፎኔ ልጅ ለካሌብ ርስት አድርገው ሰጡት።
13ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንና መሰማሪያዋን፥ ልብናንና መሰማሪያዋን፥ 14የቲርንና መሰማሪያዋን፥ ኤሽትሞዓንና መሰማሪያዋን፥ 15ሖሎንንና መሰማሪያዋን፥ ዳቤርንና መሰማሪያዋን፥ 16ዓይንንና መሰማሪያዋን፥ ዮጣንና መሰማሪያዋን፥ ቤት-ሳሜስንና መሰማሪያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። 17ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማሪያዋን፥ ናሲብንና መሰማሪያዋን፥ 18#ኤር. 1፥1።አናቶትንና መሰማሪያዋን፥ አልሞንና መሰማሪያዋን፤ አራት ከተሞችን ሰጡ። 19የአሮን ልጆች የካህናት ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸው ጋር ዐሥራ ሦስት ከተሞች ናቸው።
20 # 1ዜ.መ. 6፥51-55። ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች የሌዋውያን ለሆኑ የቀዓት ወገኖች የዕጣቸው ከተሞች ከኤፍሬም ነገድ ደረሱአቸው። 21እነዚህንም ከተሞች ሰጡአቸው፤ በኤፍሬም ተራራማ አገር ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ሴኬምንና መሰማሪያዋን፥ ጌዝርንና መሰማሪያዋን፥ 22ቂብጻይምንና መሰማሪያዋን፥ ቤት-ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 23ከዳንም ነገድ ኤልተቄንና መሰማሪያዋን፥ ገባቶንንና መሰማሪያዋን፥ 24ኤሎንንና መሰማሪያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 25ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋት-ሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 26የቀሩት የቀዓት ልጆች ወገኖች ከተሞች ሁሉ ከመሰማሪያቸው ጋር ዐሥር ናቸው።
27 # 1ዜ.መ. 6፥56-61። ለሌዋውያንም ወገኖች ለጌድሶን ልጆች ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ በባሳን ውስጥ የሆነቸውን ጎላንንና መሰማሪያዋን፥ በኤሽትራንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 28ከይሳኮርም ነገድ ቂሶንንና መሰማሪያዋን፥ ዳብራትንና መሰማሪያዋን፥ 29የርሙትንና መሰማሪያዋን፥ ዐይን-ጋኒምንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 30ከአሴርም ነገድ ሚሽአልንና መሰማሪያዋን፥ ዓብዶንንና መሰማሪያዋን፥ 31ሔልቃትንና መሰማሪያዋን፥ ረዓብንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 32ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞት-ዶንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። 33የጌድሶን ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው ዐሥራ ሦስት ከተሞች ከመሰማሪያቸው ጋር ነበሩ።
34 # 1ዜ.መ. 6፥62-66። ከሌዋውያንም ለቀሩት ለሜራሪ ልጆች ወገን ከዛብሎን ነገድ ዮቅንዓምንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንና መሰማሪያዋን፥ 35ዲሞናንና መሰማሪያዋን፥ ነህላልንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 36ከሮቤልም ነገድ ቦሶርንና መሰማሪያዋን፥ ያሀጽንና መሰማሪያዋን፥ 37ቅዴሞትንና መሰማሪያዋን፥ ሜፍዓትንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 38ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንና መሰማሪያዋን፥ 39ሐሴቦንንና መሰማሪያዋን፥ ኢያዜርንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡ። 40ከሌዋውያን ወገኖች የቀሩት የሜራሪ ልጆች ከተሞች ሁሉ በየወገኖቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ ዕጣቸውም ዐሥራ ሁለት ከተማ ነበረ።
41 # ዘኍ. 35፥7። በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ። 42እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው መሰማሪያዎች ነበራቸው፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ።
43 # ዘፍ. 12፥7፤ 13፥15፤ 15፥18፤ 26፥3፤ 28፥4፤ 13። ጌታም ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም። 44ጌታም ለአባቶቻቸው እንደ ማለላቸው በዙሪያቸው ካሉት አሳረፋቸው፤ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ ማንም ሰው ሊቋቋማቸው አልቻለም፤ ጌታም ጠላቶቻቸውን ሁሉ በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው። 45#ኢያ. 23፥14-15።ጌታ ለእስራኤል ቤት ከተናገረው መልካም ነገር ሁሉ ተፈጸመ እንጂ ምንም አልቀረም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ