የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘሌዋውያን 2

2
የእህል ቁርባን
1 # ዘሌ. 5፥11-13፤ 6፥7-16፤ 7፥9-14፤ 24፥5-9፤ ዘኍ. 15፥1-21፤ ዘፍ. 4፥3-5። “ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤#ዘፀ. 30፥1-10፤ ዘሌ. 16፥11-13፤ ምሳ. 27፥9። 2#ዘሌ. 1፥9።ወደ አሮንም ልጆች ወደ ካህናቱ ያመጣዋል። ከመልካም ዱቄቱና ከዘይቱ አንድ እፍኝ ሙሉና ዕጣኑን ሁሉ ከወሰደ በኋላ ካህኑ ለመታሰቢያ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። 3#ዘሌ. 6፥9፤ 7፥9-10።ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።#ዘሌ. 6፥10፤ 18፤ 22፤ 10፥12፤ 17፤ 24፥9።
4 # 1ዜ.መ. 23፥29። “በምድጃ የተጋገረውን የእህል ቁርባን ስታቀርብ በዘይት ተለውሶ እርሾ ያልገባበት፥ የመልካም ዱቄት የቂጣ እንጐቻ ወይም እርሾ ያልነካው በዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ይሁን። 5#ዘሌ. 6፥14።ቁርባንህም በምጣድ የተጋገረ የእህል ቁርባን ቢሆን፥ እርሾ ያልገባበት፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት ቂጣ ይሁን። 6ቈራርሰህም ዘይት ታፈስበታለህ፤ የእህል ቁርባን ነው። 7ቁርባንህም በመጥበሻ የተጋገረ የእህል ቁርባን ቢሆን፥ ዘይት የገባበት ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን። 8ከእዚህም ነገረሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ጌታ ታመጣለህ፤ ለካህኑም ይሰጣል፥ እርሱም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል። 9ካህኑም ከእህሉ ቁርባን መታሰቢያውን አንሥቶ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። 10ከእህሉም ቁርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለጌታ በእሳት ከቀረበው የቁርባን ክፍል በመሆኑ እጅግ የተቀደሰ ነው።
11 # ማቴ. 16፥12፤ ማር. 8፥15፤ ሉቃ. 12፥1፤ 1ቆሮ. 5፥7፤ ገላ. 5፥9። “ማንኛውም እርሾ ያለበትን ነገርና ማርን፥ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ አታቃጥሉትምና ለጌታ የምታቀርቡት የእህል ቁርባን ሁሉ በእርሾ የተዘጋጀ አይሁን። 12#ዘኍ. 18፥12-13፤ 27፤ 15፥20-21።እነዚህንም የበኵራት ቁርባን አድርጋችሁ ለጌታ ታቀርባላችሁ፤ እንደ መዓዛው ያማረ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም። 13#ዘኍ. 18፥19፤ ዕዝ. 6፥9፤ 7፥22፤ ሕዝ. 43፥24።የምታቀርበውን የእህል ቁርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም የቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቁርባንህ እንዳታጐድል፤ በቁርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።
14“ከበኵራትም የእህል ቁርባን ለጌታ የምታቀርብ ከሆነ፥ በእሳት የተጠበሰና የተፈተገ የእህል እሸትን የበኵራትህ የእህል ቁርባን አድርገህ ታቀርባለህ። 15ዘይትም ታፈስበታለህ፥ ዕጣንም ትጨምርበታለህ፤ የእህል ቁርባን ነው። 16ካህኑም ከተፈተገው እህል ከዘይቱም ወስዶ፥ ከዕጣኑ ሁሉ ጋር መታሰቢያውን ያቃጥላል፤ ይህ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ነው።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ