ኦሪት ዘሌዋውያን 3

3
የአንድነት ቁርባን
1 # ዘሌ. 7፥11-36። “ቁርባኑም የአንድነት መሥዋዕት ቢሆን፥ ከበሬ መንጋ ተባት ወይም እንስት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለበትን በጌታ ፊት ያቅርብ።#ዘሌ. 22፥21። 2#ዘሌ. 1፥4።እጁንም ለቁርባን ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። 3#ዘሌ. 3፥9-10፤ 14—16፤ 4፥8-9፤ 6፥5፤ 7፥3-4፤ 8፥16፤ 25፤ 16፥25፤ 17፥6፤ ዘፀ. 29፥13፤ 22፤ ሕዝ. 44፥15።ከሰላሙም መሥዋዕት ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ የሚያቀርበው፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ 4ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶች ጋር ወስዶ ነው። 5#ዘሌ. 1፥9።የአሮንም ልጆች ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በእንጨቱ ላይ ያቃጥሉታል፤ ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ነው።
6“ለጌታም ለአንድነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቁርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል። 7ለቁርባኑ ጠቦትን ቢያቀርብ በጌታ ፊት ያቀርበዋል፤ 8እጁንም ለቁርባን ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፥ በመገናኛውም ድንኳን ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። 9ከሰላሙም መሥዋዕት ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ የሚያቀርበው፤ ስቡን፥ እስከ ጀርባውም ድረስ የተቈረጠ ላቱን ሁሉ፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ 10ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶች ጋር ወስዶ ነው። 11#ዘሌ. 9፥19።ካህኑም ለጌታ በእሳት ላይ የሚቀርብ ማዕድ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
12“ቁርባኑም ፍየል ቢሆን በጌታ ፊት ያቀርበዋል፤ 13እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፥ በመገናኛውም ድንኳን ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። 14ከእርሱም ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ ከቁርባኑ የሚያቀርበው፤ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ 15ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶች ጋር ወስዶ ነው። 16ካህኑም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ማዕድ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ስቡ ሁሉ ለጌታ ነው። 17#ዘሌ. 17፥10።በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለልጅ ልጃችሁ ፈጽሞ ማንኛውንም ስብና ደም እንዳትበሉ የዘለዓለም ሥርዓት ነው።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ