የማቴዎስ ወንጌል 21
21
ኢየሱስ በክብር ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ገባ
(ማር. 11፥1-11፤ ሉቃ. 19፥28-40፤ ዮሐ. 12፥12-19)
1ወደ ኢየሩሳሌምም በቀረቡ ጊዜ ወደ ደብረዘይት ወደ ቤተ ፋጌ መጡ፥ ያንጊዜ ኢየሱስ ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ 2እንዲህም አላቸው “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፤ በዚያን ጊዜ የታሰረች አህያ ከነውርንጫዋ ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ። 3ማንም ምንም ቢላችሁ ‘ጌታ ይፈልጋቸዋል’ በሉ፤ ወዲያውም ይልካቸዋል።” 4ይህም በነቢዩ እንዲህ የብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፦ 5#ዘካ. 9፥9።“ለጽዮን ልጅ
“እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል
በውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፥ በሉአት።”
6ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ። 7አህያይቱንና ውርንጫዋን አመጡለት፤ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠባቸው። 8እጅግ ብዙ ሕዝብም ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፤ ሌሎች ደግሞ የዛፍ ቅርንጫፍ እየቆረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። 9#መዝ. 118፥25፤26።ከፊቱ ይሄዱ የነበሩትና ይከተሉት የነበሩት ሕዝብ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር። 10ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ “ይህ ማን ነው?” ብሎ መላው ከተማ ተናወጠ። 11ሕዝቡም “ይህ በገሊላ ከምትገኘው ከናዝሬት የመጣው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” አሉ።
ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገበያዩትን እንዳባረረ
(ማር. 11፥15-19፤ ሉቃ. 19፥45-48፤ ዮሐ. 2፥13-22)
12ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ጠረጴዛዎችና የርግብ ሻጮችን ወንበሮች ገለበጠ፤ 13#ኢሳ. 56፥7፤ ኤር. 7፥11።“‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የዘራፊዎች ዋሻ አደረጋችሁት” አላቸው።
14በመቅደስም ዕውሮችና አንካሶች ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው። 15ነገር ግን ሊቃነ ካህናትና ጻፎች ያደረገውን ድንቅ ነገርና በመቅደስም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ!” እያሉ የሚጮኹትን ልጆች ባዩ ጊዜ፥ ተቆጡ፤ 16#መዝ. 8፥2።“እነዚህ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስም “አዎን እሰማለሁ፤ ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው። 17ትቶአቸውም ከከተማ ወጥቶ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ በዚያም አደረ።
ኢየሱስ የበለስዋን ዛፍ እንደረገመ
(ማር. 11፥12-14፤20-24)
18በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ራበው። 19በመንገድ ዳር የበለስ ዛፍ አይቶ ወደ እርሷ መጣ፤ ነገር ግን ከቅጠል በስተቀር ምንም አላገኘባትም፤ “እንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስዋ ዛፍም ወዲያውኑ ደረቀች። 20ደቀ መዛሙርቱም ይህንን አይተው በመደነቅ “የበለስዋ ዛፍ ወዲያውኑ እንዴት ደረቀች?” አሉ። 21#ማቴ. 17፥20፤ 1ቆሮ. 13፥2።ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ፥ በበለሲቱ ዛፍ እንደተደረገው ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት ይሆናል፤ 22አምናችሁ በጸሎት የምትጠይቁትን ነገር ሁሉ ትቀበላላችሁ።”
የኢየሱስ ሥልጣን ጥያቄ እንደ ቀረበበት
(ማር. 11፥27-33፤ ሉቃ. 20፥1-8)
23ወደ መቅደስ ገብቶ በማስተማር ላይ ሳለ ሊቃነ ካህናትና የሕዝብ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጥተው “እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉት። 24ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “እኔም ደግሞ አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተ ከነገራችሁኝ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ፤ 25የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነበር? ከሰማይ ወይስ ከሰዎች?” እርስ በርሳቸው እንዲህ ሲሉ ተነጋገሩ “‘ከሰማይ’ ብንል ‘ታዲያ ለምን አላመናችሁትም?’ ይለናል፤ 26‘ከሰዎች’ ነው ብንል፥ ዮሐንስን ሁሉም እንደ ነቢይ ስለሚያዩት ሕዝቡን እንፈራለን” አሉ። 27ለኢየሱስም “አናውቅም” ብለው መለሱለት። እርሱም “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
ስለ ሁለቱ ወንድማማቾች ምሳሌ
28“ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፤ ወደ መጀመሪያውም ሄዶ ‘ልጄ ሆይ! ዛሬ ወደ ወይኔ አትክልት ሥፍራ ሂድና ሥራ’ አለው። 29እርሱም ‘አልሄድም’ አለ፤ ቆይቶ ግን ተጸጸተና ሄደ። 30ወደ ሁለተኛውም ሄዶ እንዲሁ አለው እርሱም ‘እሺ ጌታዬ’ ብሎ መለሰለት፤ ነገር ግን አልሄደም። 31ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?” እነርሱም “የመጀመሪያው” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ዘማውያን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል። 32#ሉቃ. 3፥12፤ 7፥29፤30።ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበር፥ አላመናችሁትም፤ ቀራጮችና ዘማውያን ግን አመኑት፤ በመጨረሻም ይህንን አይታችሁ እንኳ ልታምኑት ንስሐ አልገባችሁም።
የወይኑ አትክልት ገበሬዎች ምሳሌ
(ማር. 12፥1-12፤ ሉቃ. 20፥9-19)
33 #
ኢሳ. 5፥1፤2። “ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ የወይን አትክልት የተከለ አንድ የእርሻ ባለቤት ነበረ፤ እርሱም ቅጥር ቀጠረለት፤ መጭመቂያም ማሰለት፤ ግንብም ሠራለት፤ እርሻውንም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። 34የሚያፈራበት ወራት በደረሰ ጊዜ፥ ፍሬውን እንዲቀበሉለት ባርያዎቹን ወደ ገበሬዎቹ ላከ። 35ገበሬዎቹም ባርያዎቹን ይዘው አንዱን ደበደቡት፤ አንዱን ገደሉት፤ ሌላውን ደግሞ በድንጋይ ወገሩት። 36እርሱም ከፊተኞቹ የሚበዙ ሌሎች ባርያዎችን ላከ፤ እነርሱንም እንዲሁ አደረጉባቸው። 37በመጨረሻም ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ ብሎ ልጁን ላከባቸው። 38ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ። 39ይዘውም ከወይኑ አትክልት ሥፍራ አውጥተው ገደሉት። 40እንግዲህ የወይኑ አትክልት ሥፍራ ጌታ በሚመጣ ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ላይ ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል?” 41እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ሁኔታ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ሥፍራ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል” አሉት።
42 #
መዝ. 118፥22፤23። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው
“‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤
ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’
የሚለውን ከቶ በመጽሕፍት አላነበባችሁምን? 43ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች። 44በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይሰባበራል፤ ድንጋዩ በላዩ ላይ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ያደቅቀዋል።”
45ሊቃነ ካህናትና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ ስለ እነርሱ እንደ ተናገረ አወቁ። 46ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ሕዝቡ እንደ ነቢይ ያዩት ስለ ነበር ፈሩ።
Currently Selected:
የማቴዎስ ወንጌል 21: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ