የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የማቴዎስ ወንጌል 22

22
የሰርጉ ድግስ ምሳሌ
(ሉቃ. 14፥15-24)
1ኢየሱስ አሁንም በምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ 2“መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ የደገሰ ንጉሥን ትመስላለች። 3የታደሙትንም ወደ ሰርጉ እንዲጠሩ ባርያዎቹን ላከ፤ እነርሱ ግን ሊመጡ አልፈለጉም። 4ሌሎች ባርያዎችን ደግሞ ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ግብዣ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ። 5እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥ ሌላው ወደ ንግዱ ሄደ፤ 6የቀሩትም ባርያዎቹን ይዘው ሰደቡአቸው፤ ገደሉአቸውም። 7ንጉሡም ተቆጣ፤ ወታደሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ። 8በዚያን ጊዜ ባርያዎቹን እንዲህ አላቸው ‘ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ የታደሙት ግን የተገቡ አልሆኑም፤ 9ስለዚህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሄዳችሁ ያገኛችሁትን ሁሉ ወደ ሰርጉ ጥሩ።’ 10እነዚያም ባርያዎች ወደ መንገድ ወጥተው ያገኙትን ሁሉ ክፉዎችንና በጎዎችን ሰበሰቡ፤ የሰርጉም ቤት በተጋባዦች ተሞላ።
11“ንጉሡም ተጋባዦቹን ለማየት በገባ ጊዜ፥ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ አንድ ሰው በዚያ አየ። 12‘ወዳጄ ሆይ! የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ?’ አለው እርሱም ዝም አለ። 13#ማቴ. 8፥12፤ 25፥30፤ ሉቃ. 13፥28።በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ። 14የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።”
ግብር ስለ መክፈል
(ማር. 12፥13-17ሉቃ. 20፥23-26)
15ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያን ሄዱና እንዴት አድርገው በንግግሩ እንደሚያጠምዱት ተማከሩ። 16ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ላኩበት፤ እነርሱም እንዱህ አሉት “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደሆንህ የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አታይምና፤ 17ምን ይመስልሃል? እስቲ ንገረን፥ ለቄሣር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?” 18ኢየሱስም ክፋታቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው “እናንተ ግብዞች፥ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? 19ለግብር የሚከፈለውን ብር አሳዩኝ።” እነርሱም ዲናር አመጡለት። 20እርሱም “ይህ መልክና ጽሑፉ የማን ነው?” አላቸው። 21እነርሱም “የቄሣር ነው” አሉት። እርሱም “እንግዲያውስ የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” አላቸው። 22ይህንንም ሰምተው ተደነቁ፤ ትተውትም ሄዱ።
ስለ ሙታን ትንሣኤ የቀረበ ጥያቄ
(ማር. 12፥18-27ሉቃ. 20፥27-40)
23 # የሐዋ. 23፥8። በዚያን ቀን የሙታን ትንሣኤ የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤ 24#ዘዳ. 25፥5።“መምህር ሆይ! ሙሴ ‘አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ ሚስቱን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካ፤’ ብሏል። 25ሰባት ወንድማማቾች በእኛ ዘንድ ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አግብቶ ሞተ፤ ዘርም ስለሌለው ሚስቱን ለወንድሙ ተወለት፤ 26እንዲሁ ደግሞ ሁለተኛው፥ ሦስተኛው፥ እስከ ሰባተኛው ድረስ እንዲህ ሆነ። 27ከሁሉም በኋላ ሴትዮዋ ሞተች። 28ታዲያ በሙታን ትንሣኤ ቀን ከሰባቱ ለየትኛው ሚስት ትሆናለች? ሁሉም አግብተዋታልና።”
29ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ስታችኋል፥ ምክንያቱም መጻሕፍትን ወይም የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና። 30#ጥበ. 5፥5።በሙታን ትንሣኤ ጊዜ እንደ መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም ወይም አይጋቡም። 31ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ እንዲህ ተብሎ የተነገረውን አላነበባችሁምን? 32#ዘፀ. 3፥6።‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤’ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም።” 33ሕዝቡም ይህንን ሰምተው በትምህርቱ ተገረሙ።
ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ
(ማር. 12፥28-34ሉቃ. 10፥25-28)
34ፈሪሳውያንም ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። 35ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ፈልጎ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ 36“መምህር ሆይ! ከሕግ ማንኛይቱ ትእዛዝ ትበልጣለች?” 37#ዘዳ. 6፥5።እርሱም እንዲህ አለው “‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ፥ በፍጹም ሐሳብህ#22፥37 አእምሮ የሚለውን ቃል ይጠቀማል። ውደድ።’ 38ታላቂቱና የመጀመሪያይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። 39#ዘሌ. 19፥18።ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርሷም ‘ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤’ የምትለው ናት። 40#ሉቃ. 10፥25-28።በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕግና ነቢያት ሁሉ ተንጠልጥለዋል።”
ስለ መሢሕ የቀረበ ጥያቄ
(ማር. 12፥35-37ሉቃ. 20፥41-44)
41ፈሪሳውያን ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦ 42“ስለ ክርስቶስ ምን ትላላችሁ? የማንስ ልጅ ነው?” እነርሱም “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት። 43እርሱም እንዲህ አላቸው፥ ታዲያ ዳዊት በመንፈስ ተመርቶ እንዴት ጌታ ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦ 44#መዝ. 110፥1። ጌታ ጌታዬን “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው፤
45“ዳዊት ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ሊሆን ይችላል?” 46አንድም ቃል እንኳ ሊመልስለት የቻለ ማንም አልነበረም፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ አንድስ እንኳ አልነበረም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ