የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍልቊ 33

33
እስራኤላውያ ከግብጽ ያደረጉት ጉዞ
1በሙሴና በአሮን ልጅ እየተመሩ በየሠራዊታቸው ሆነው ከግብጽ በወጡ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ያደረጉት ጉዞ ይህ ነበረ። 2ሙሴም በጌታ ትእዛዝ የጉዞአቸው መነሻ የሆኑትን ስፍራዎቻቸውን ጻፈ፤ እንደ መነሻ ስፍራዎቻቸው ጉዞአቸው እንዲህ ነበረ። 3በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዓሥራ አምስተኛው ቀን ከራዓምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በማግስቱ የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ። 4በዚያም ጊዜ ግብፃውያን ጌታ የገደላቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ላይ ደግሞ ጌታ ፈረደባቸው።
5የእስራኤልም ልጆች ከራዓምሴ ተጉዘው በሱኮት ሰፈሩ። 6ከሱኮትም ተጉዘው በምድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤታም ሰፈሩ። 7ከኤታምም ተጉዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። 8ከፊሀሒሮትም ተጉዘው ባሕሩን በመሻገር ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ። 9ከማራም ተጉዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም ዐሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ። 10ከኤሊምም ተጉዘው በኤርትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ። 11ከኤርትራም ባሕር ተጉዘው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። 12ከሲን ምድረ በዳም ተጉዘው በራፋቃ ሰፈሩ። 13ከራፋቃም ተጉዘው በኤሉስ ሰፈሩ። 14ከኤሉስም ተጉዘው በራፊዲም ሰፈሩ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። 15ከራፊዲምም ተጉዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። 16ከሲናም ምድረ በዳ ተጉዘው በኬብሮን-ሐታማ ሰፈሩ። 17ከኬብሮን-ሐታማም ተጉዘው በሐጼሮት ሰፈሩ። 18ከሐጼሮትም ተጉዘው በሪትማ ሰፈሩ። 19ከሪትማም ተጉዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ። 20ከሬሞን ዘፋሬስም ተጉዘው በልብና ሰፈሩ። 21ከልብናም ተጉዘው በሪሳ ሰፈሩ። 22ከሪሳም ተጉዘው በቀሄላታ ሰፈሩ። 23ከቀሄላታም ተጉዘው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ። 24ከሻፍር ተራራም ተጉዘው በሐራዳ ሰፈሩ። 25ከሐራዳም ተጉዘው በመቅሄሎት ሰፈሩ። 26ከመቅሄሎትም ተጉዘው በታሐት ሰፈሩ። 27ከታሐትም ተጉዘው በታራ ሰፈሩ። 28ከታራም ተጉዘው በሚትቃ ሰፈሩ። 29ከሚትቃም ተጉዘው በሐሽሞና ሰፈሩ። 30ከሐሽሞናም ተጉዘው በሞሴሮት ሰፈሩ። 31ከሞሴሮትም ተጉዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። 32ከብኔያዕቃንም ተጉዘው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ። 33ከሖርሃጊድጋድም ተጉዘው በዮጥባታ ሰፈሩ። 34ከዮጥባታም ተጉዘው በዔብሮና ሰፈሩ። 35ከዔብሮናም ተጉዘው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። 36ከዔጽዮንጋብርም ተጉዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት። 37ከቃዴስም ተጉዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።
38 # ዘኍ. 20፥22-28፤ ዘዳ. 10፥6፤ 32፥50። ካህኑም አሮን በጌታ ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። 39አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር።
40 # ዘኍ. 21፥1። በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደመጡ ሰማ።
41እነርሱም ከሖር ተራራ ተጉዘው በሴልሞና ሰፈሩ። 42ከሴልሞናም ተጉዘው በፉኖን ሰፈሩ። 43ከፋኖንም ተጉዘው በአቦት ሰፈሩ። 44ከአቦትም ተጉዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በዒዬዓባሪም ሰፈሩ። 45በዒዬዓባሪም ተጉዘው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። 46ከዲቦንጋድም ተጉዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። 47ከዓልሞንዲብላታይምም ተጉዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። 48ከዓብሪምም ተራሮች ተጉዘው በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ባለው በሞዓብ ሜዳ ሰፈሩ። 49በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ።
ከነዓንን ለመያዝ የተሰጠ ምሪት
50ጌታም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 51“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ወደ ከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ 52የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ 53ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም። 54#ዘኍ. 26፥54-56።ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣው እንደ ወጣለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። 55የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ ስንጥር ለጎናችሁም እንደ እሾህ ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል። 56እኔም በእነርሱ ላይ ለማድረግ ያሰብሁትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ