ኦሪት ዘኍልቊ 34
34
የምድሪቱ ድንበር
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ወደ ከነዓን ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ ርስት እንዲሆናችሁ በዕጣ የምትደርሳችሁ ምድር፥ በተከለለው ድንበርዋ የከነዓን ምድር ይህች ናት፤ 3የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምያስን ዳርቻ እያዋሰነ የሚያልፈው ይሆናል፤ የደቡቡም ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤ 4ድንበራችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ይሻገራል፤ በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ያለው መጨረሻው ይሆናል፤ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል፤ 5ድንበሩም ከዓጽሞን ወደ ግብጽ ወንዝ ይዞራል፥ ባሕሩም ማብቂያው ይሆናል።
6“ለምዕራብም ድንበር ታላቁ ባሕርና ዳርቻው ድንበራችሁ ይሆናል፤ ይህ የምዕራብ ድንበራችሁ ይሆናል።
7“የሰሜንም ድንበራችሁ ይህ ይሆናል፤ ከታላቁ ባሕር ወደ ሖር ተራራ የወሰን ምልክት ታደርጋላችሁ። 8ከሖርም ተራራ ወደ ሐማት መግቢያ የወሰን ምልክት ታደርጋላችሁ የድንበራችሁም መጨረሻ በጽዳድ ይሆናል፤ 9ድንበሩም ወደ ዚፍሮን ይዘረጋል መጨረሻውም ሐጸርዔናን ይሆናል፤ ይህ የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል።
10“የምሥራቁም ድንበራችሁን ከሐጸርዔናን ወደ ሴፋማ የወሰን ምልክት ታደርጋላችሁ፤ 11ድንበሩም ከሴፋማ በዐይን ምሥራቅ ወዳለው ወደ ሪብላ ይወርዳል፤ እስከ ኪኔሬት የባሕር ወሽመጥ በምሥራቅ በኩል ይደርሳል፤ 12ድንበሩም ወደ ዮርዳኖስ ይወርዳል፥ መጨረሻውም በጨው ባሕር ይሆናል። ምድራችሁ እንደ ድንበርዋ በዙሪያዋ ይህች ናት።”
13 #
ዘኍ. 26፥52-56። #
ኢያ. 14፥1-5። ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “ጌታ ለዘጠኝ ነገድ ተኩል እንዲሰጥ ያዘዘው በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤ 14የሮቤልም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የጋድም ልጆች ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን ወርሰዋል። 15እነዚህ ሁለቱ ነገድና የአንዱ ነገድ እኩሌታ ርስታቸውን በዮርዳኖስ ማዶ በኢያሪኮ አንጻር በስተ ምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል ወረሱ።”
የእስራኤል ነገድ አለቆች
16ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 17“ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፋፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ። 18ምድሪቱንም ርስት አድርገው ለመከፋፈል ከየነገዱ አንድ አንድ አለቃ ትወስዳላችሁ። 19የሰዎቹም ስም ይህ ነው፤ ከይሁዳ ነገድ የዮፎኒ ልጅ ካሌብ፥ 20ከስምዖን ልጆች ነገድ የዓሚሁድ ልጅ ሰላሚኤል፥ 21ከብንያም ነገድ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፥ 22ከዳን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የዮግሊ ልጅ ቡቂ፥ 23ከዮሴፍም ልጆች ከምናሴ ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሱፊድ ልጅ አኒኤል፥ 24ከኤፍሬም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፥ 25ከዛብሎን ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የፈርናክ ልጅ ኤሊሳፈን፥ 26ከይሳኮር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሖዛ ልጅ ፈልጢኤል፥ 27ከአሴር ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የሴሌሚ ልጅ አሒሁድ፥ 28ከንፍታሌም ልጆች ነገድ አንድ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ፈዳሄል። 29ጌታ በከነዓን ምድር ለእስራኤል ልጆች ርስታቸውን እንዲያከፋፍሉ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቊ 34: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ